avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
17.04.2026 19:41
በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ከታቀዱ ተማሪዎች መካከል 6.3 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑት አለመመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ለፓርላማ በላከው ሪፖርት አስታወቀ።

በአማራ፣ በትግራይ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙትን ጨምሮ 2,672 ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ የመማር ማስተማር ስራ አለመጀመራቸው፤ ተማሪዎቹ በትምህርት ገበታቸው ላይ ላለመገኘታቸው በሪፖርቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተላከው ባለ 108 ገጽ ሪፖርት፤ የትምህርት ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም የዳሰሰ ነው።

የትምህርት ተደራሽነትን ማሳደግ በሚያትተው የሪፖርቱ ክፍል፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 33.5 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እንደነበር ሰፍሯል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በእቅድ ከያዘው የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት 19 በመቶውን ያህል ማሳካት እንዳልቻለ በሪፖርቱ ገልጿል።

በዚህም መሰረት ዘንድሮ በትምህርት ገበታ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ታቅዶ ከነበረው ውስጥ 6,380,932 ተማሪዎች መመዘገብ አለመቻላቸው ተጠቁሟል። 

ተማሪዎቹ በትምህርት ገበታቸው ላይ ላለመገኘታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሪፖርቱ በምክንያትነት የጠቀሰው፤ 2,672 በላይ ትምህርት ቤቶች በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ ችግሮች ሳቢያ ምክንያት ስራ አለመጀመራቸውን ነው። ሆኖም ሪፖርቱ “ሰው ሰራሽ” እና “የተፈጥሮ” ያላቸውን ችግሮች አላብራራም። 

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17753/

@EthiopiaInsiderNews
8
👍 2
😱 2
🙏 1
3 1.8K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
16.04.2026 20:08
የ“አዲስ ስታንዳርድ” የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው ጋዜጠኛ ሚሊዮን በየነ በትላንትናው ዕለት ረፋድ ላይ “ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች” ከተወሰደ በኋላ እስከ ዛሬ ድረስ የደረሰበት እንዳልታወቀ ተቋሙ አስታወቀ።

ጋዜጠኛው ስለሚገኝበት ቦታ እና ሁኔታ ለተቋሙም ሆነ ለቤተሰቦቹ ያስታወቀ አካል ባለመኖሩ “ከፍተኛ ስጋት” እንደፈጠረባቸው የመገናኛ ብዙሃኑ ዋና አዘጋጅ አቶ ዮናስ ከድር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

በጋዜጠኝነት ከ20 ዓመት በላይ ልምድ ያለው ሚሊዮን “አዲስ ስታንዳርድን” የዛሬ አራት ዓመት ከመቀላቀሉ በፊት፤ በቀድሞው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ውስጥ በዚሁ ሙያ አገልግሏል።

በበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃኑ በተለያዩ የአርታኢነት ደረጃዎች ሲሰራ የቆየው ሚሊዮን፤ ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ ከሚገኘው የተቋሙ ዋና ቢሮ ሲቪል በለበሱ ሰዎች የተወሰደው ትላንት ረቡዕ ሚያዝያ 7፤ 2018 ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ40 ገደማ ላይ እንደሆነ አቶ ዮናስ ገልጸዋል።

ማንነታቸው ያልታወቀው እነዚሁ ግለሰቦች ወደ ቢሮው በመግባት ጋዜጠኛውን “ለጥያቄ እንፈልግሃለን” በማለት ይዘውት ሲወጡ፤ በደህንነት ካሜራ (CCTV) መታየታቸውን ዋና አዘጋጁ ተናግረዋል።

ግለሰቦቹ የጋዜጠኛውን “ስልክ ሲቀበሉ” እና “ላፕቶፕ በእጁ ይዞ ሲሄድ” በደህንነት ካሜራው መመልከታቸውንም አቶ ዮናስ አስረድተዋል።

የ“አዲስ ስታንዳርድ” አሳታሚ የሆነው ጃኬን አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ትላንት ባወጣው መግለጫ፤ ግለሰቦቹ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የነበረው “በታቀደ እና በተደራጀ መልኩ” እንደነበርም ድርጅቱ አክሏል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17749/

@EthiopiaInsiderNews
11
😢 5
👍 2
4 3K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
16.04.2026 08:29
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ብዙ ሰዎች ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ “በደንብ የሚገባቸው አይመስለኝም” ሲሉ ተናገሩ።

እርሳቸው የሚያስቧትን የበለጸገች ኢትዮጵያ “እንደሚያዩ” “ጥርጥር እንደሌላቸው” የገለጹት አብይ፤ ነገር ግን በተሟላ ደረጃ የስራቸውን ትሩፋት “የሚቋደሱ” እና “የሚዝናኑባት” ላይሆኑ እንደሚችሉ ግምታቸውን አጋርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተስፋ እና ግምታቸውን የገለጹት፤ ከብሔራዊው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት እና ላለፉት ሁለት ቀናት በተላለፈ ቃለ ምልልሳቸው ላይ ነው።

በኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ሁኔታ ላይ ባተኮረው በዚህ ቃለ ምልልስ ማገባደጃ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ራዕይ በተመለከተ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
 
አብይ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ በሚቀጥለው 10 ዓመታት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ “አውራ ሀገር” እንደምትሆን “ምንም ጥርጥር የለውም” ብለዋል።

“እኔ የምናስባትን ኢትዮጵያ እንደማይ ጥርጥር የለኝም። አያታለሁ። ልጆቼ ደግሞ ይኖሯታል” ያሉት አብይ፤ የእርሳቸው “የህይወት ጉዞ” ለዚህ “መሰረት መጣል” እንደሆነ አስረድተዋል። 

“የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ እና ልፋቶቻችን፣ ሪፎርሞቻችን፣ ስራዎቻችን respond እንዲያደርጉ ማድረግ የሚያስችል አስቻይ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለ በደንብ እገነዘባለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የየዕለቱ ስራቸውን የሚያከናውኑት ይህንኑ “አምነው እና “አስበው” እንደሆነ አስገንዝበዋል።

እርሳቸው ይህ እምነት ቢኖራቸውም “ብዙ ሰዎች” ግን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ “በደንብ የሚገባቸው አይመስለኝም” ሲሉም ተደምጠዋል። 

🔴ቀሪውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17739/

@EthiopiaInsiderNews
😁 29
15
👎 10
4 3.5K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
15.04.2026 23:57
ዘንድሮ የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት መታቀዱ፤ የመሰረተ ልማት ባልተሟላባቸው አካባቢዎች ባሉ ተማሪዎች ውጤት ላይ “ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ” ሊኖረው እንደሚችል የፓርላማ አባላት ስጋታቸውን ገለጹ።

ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ 122 ሺህ የመፈተኛ ኮምፒውተሮች መዘጋጀታቸውን እና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል የተለያዩ የመንግስት አካላትን የያዘ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ገልጿል።

ይህ የተገለጸው የትምህርት ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ረቡዕ ሚያዝያ 7፤ 2018 ባቀረበበት ወቅት ነው።

የተቋሙን የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው በንባብ ያቀረቡት፤ በሚኒስቴሩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እሸቱ ገላዬ ናቸው።

አቶ እሸቱ በዚሁ ሪፖርታቸው የዘንድሮውን ሀገር አቀፍ ፈተና “መቶ በመቶ በበይነ መረብ (online) ለመስጠት” ከክልል ፕሬዝዳንቶች እና ከትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ ስራዎችን ሲከናወኑ መቆየታቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። ይህ የሚኒስቴሩ እቅድ በፓርላማ የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ አባላት ጥያቄ ቀርቦበታል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄዎች በንባብ ያቀረቡት አቶ ታደሰ ጌጡ፤ ፈተናው በዚህ መልክ መሰጠቱ የኮምፒውተር፣ የመብራት እና የኔትወርክ መሰረተ ልማት ባልተሟላባቸው ትምህርት ቤቶች የሚፈተኑ ተማሪዎች ውጤት ላይ “ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ” ሊኖረው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። ይህን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ምን መፍትሔ እንዳለውም ማብራሪያ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17729/

@EthiopiaInsiderNews
6
😁 2
7 3.5K
avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
04.04.2026 20:01
የመራጮች ምዝገባ በሁለት ሳምንት ተራዘመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአንድ ወር ሲያካሄድ የቆየውን የመራጮች ምዘገባ በሁለት ሳምንት አራዘመ። ቦርዱ ጊዜውን ያራዘመው፤ በዲጂታል እገዛ ሲከናወን በቆየው ምዝገባ በተፈጠሩ ተግዳሮቶች እና በትራንስፖርት አቅርቦት ችግር የባከነውን ጊዜ ለማካካስ እንደሆን አስታውቋል።

ምርጫ ቦርድ ባለፈው ህዳር ወር ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ፤ የመራጮች ምዝገባ ለማከናወን አቅዶ የነበረው ከየካቲት 7 እስከ መጋቢት 7፤ 2018 ነበር። ሆኖም ቦርዱ በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ያቀዳቸውን ስራዎች "አከናውኖ መጨረስ ባለመቻሉ"፤ የመራጮች ምዝገባ መጀመሪያው በሁለት ሳምንት እንዲገፋ አድርጓል።

በቦርዱ ውሳኔ መሰረት የካቲት 26 የተጀመረው የመራጮች ምዝገባ እንዲጠናቀቅ ቀነ ገደብ የተቀመጠለት ከአንድ ወር በኋላ ነበር። ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ አራት ቀናት በፊት በጠቅላላ የተመዘገበው መራጭ ብዛት 36.9 ሚሊዮን መሆኑን ምርጫ ቦርድ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ መጋቢት 24 ባሰራጨው መረጃ አመልክቷል። (ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
14
😁 14
6 6.8K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
02.04.2026 21:38
ቪዲዮ፦ በአዲስ አበባ በሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ተቋማት ሰራተኞች እና ኃላፊዎች ላይ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሚኖራቸው “የዳኝነት ስልጣን” በፓርላማ አከራከረ። ለኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣኑን የሰጠው፤ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 24፤ 2018 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የተሻሻለው የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ነው።

በኢትዮጵያ እስካሁን በስራ ላይ የቆየው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ በ1954 ዓ.ም የወጣ ነበር። ከ60 ዓመት በላይ በስራ ላይ የቆየውን ይህን ህግ የሚያሻሻል አዋጅ፤ በዛሬው የፓርላማ ስብሰባ በሁለት ተቃውሞ፤ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

አዋጁ ከመጽደቁ አስቀድሞ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) ወክለው የፓርላማ አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እና ዶ/ር አበባው ደሳለኝ “አወዛጋቢ” ባሏቸው አንቀጾች ላይ ጥያቄዎች አንስተዋል።

ጥያቄ ካስነሱ ድንጋጌዎች መካከል “የኦሮሚያ ክልል የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከስራ ኃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ በሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ላይ፤ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ይኖራቸዋል” የሚለው ይገኝበታል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴በዚህ ድንጋጌ ላይ የቀረበውን ጥያቄ እና ምላሽ ሙሉ ቪዲዮ ለመመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ ➡️ https://youtu.be/AMv-OdFuMMQ

@EthiopiaInsiderNews
15
👍 2
11 7.1K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
01.04.2026 19:32
ኢትዮጵያ በዘንድሮው በጀት ዓመት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 6.76 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህ የገንዘብ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ2.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ እድገት ያለው መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 23፤ 2018 የስምንት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በዚሁ ስብሰባ ላይ፤ የዘንድሮው የስምንት ወራት ገቢ በኢትዮጵያ ታሪክ “ተገኝቶ የማይታወቅ” መሆኑን ተናግረዋል።

ሆኖም የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ፤ የስምንት ወራቱ የወጪ ንግድ አፈጻጸም በ2018 ይደረስበታል ተብሎ ከታቀደው የሶስት ዓመቱ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ የሆነበትን ምክንያት ማብራሪያ እንዲሰጥበት ጠይቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክትትል የሚያደርግባቸው የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ሰብሎች እና የእንስሳት መኖ የወጪ ንግድ አፈጻጸምም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ዝቅ ያለበትን ምክንያት እንዲገለጽም ቋሚ ኮሚቴው በተመሳሳይ ጥያቄ አቅርቧል።

🔴ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17721/

🔴 የዛሬውን የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ስብሰባን በቪዲዮ ለመመልከት ➡️ https://youtu.be/ub0NqeoHMeU

@EthiopiaInsiderNews
9
6 6.7K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
01.04.2026 18:05
ቪዲዮ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 23፤ 2018 የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውን የስምንት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት፤ የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ዘለግ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ ችግሩ በሰርጡ መዘጋት ብቻ የተገደበ እንዳልሆነ ገልጸው፤ አምራች ሀገራት በጦርነት እና ቀውስ ውስጥ በመሆናቸው “የነዳጅ የማምረት ሥራ መቆሙን” እና “የማጣራት ስራ” በእጅጉ ማሽቆልቆሉን ገልጸዋል። ይህ ሁኔታ የዓለም ነዳጅ ዋጋ በአንድ ጊዜ “በሶስት እጥፍ እንዲያሻቅብ” ማድረጉንም አመልክተዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት ሳቢያ ኢትዮጵያ በመደበኛ ግዢ ስርዓት ወደ ሀገር ውስጥ ልታስገባው በነበረው 180 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነዳጅ የማስተላለፍ ሂደት ላይ መስተጓጎል መግጠሙን ዶ/ር ካሳሁን ተናግረዋል።

የቤንዚን አቅርቦት ከ80 እስከ 100 በመቶ እየተሸፈነ በመሆኑ “እጥረት እንደሌለ” የገለጹት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ፤ በነጭ ናፍጣ እና በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ ግን አቅርቦቱ በሚፈልገው ልክ መሆን እንዳልቻለ አስረድተዋል። በነጭ ናፍጣ እና በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ 50 በመቶ አቅርቦት ለማረጋገጥ ጥረት መደረጉን ዶ/ር ካሳሁን ጠቁመዋል።

የነዳጅ አቅርቦቱ እንዴት መቀዳደም መኖር እንዳለበት “ልዩ ውሳኔ መተላለፉን” እና ይህንኑ ክትትል የሚያደርግ የሁኔታዎች ልዩ መከታተያ ክፍል (situation room) መቋቋሙን አብራርተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ስለ ነዳጅ አቅርቦት የሰጡትን ማብራሪያ ይህን ሊንክ https://youtu.be/s6SUNZthg4o ተጭነው ይመልከቱ።

@EthiopiaInsiderNews
5
6 5.3K
avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
29.03.2026 17:02
ስለ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ማኒፌስቶ አመራሮቹ ምን ይላሉ?

ትላንት፣ ቅዳሜ፣ መጋቢት 19፣ 2018 ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያዘጋጀውን የቃል ኪዳን ሰነድ ወይም ማኒፌስቶ ይፋ አድርጓል። "ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" አመራሮቹን ስለ ማኒፌስቶው ይዘት አነጋግራ የተሰጣትን መልስ በዚህ መልኩ አቅርባዋለች። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
https://www.youtube.com/watch?v=NFdId2QiDzo

#ምርጫ2018 #EthiopiaElection @EthioElections
YouTube
ስለ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ማኒፌስቶ አመራሮቹ ምን ይላሉ?
ትላንት ቅዳሜ፣ መጋቢት 19፣ 2018 ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያዘጋጀውን የቃል ኪዳን ሰነድ ወይም ማኒፌስቶ ይፋ አድርጓል። "ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" አመራሮቹን ስለ ማኒፌስቶው ይዘት አነጋግራ የተሰጣትን መልስ በዚህ መልኩ አቅርባዋለች።
6
👍 3
2 6.7K
avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
29.03.2026 17:02
ኢዜማ መንግሥት ለመመሥረት የሚያበቃ ዕጩ ያስመዘገብኩ ብቸኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ብሆንም፣ የምጠብቀውን ውጤት መጥኛለሁ አለ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ፣ መጋቢት 19፣ 2018 እያካሔደ ባለው የበይነመረብ ስብሰባ፣ መሪው አቶ ኢዮብ መሣፍንት ኢዜማ 299 ዕጩዎችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ዕጩ አድርጎ በማቅረብ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ሆኖ ወደ ውድድሩ መግባቱን ገልጸዋል። ሆኖም፣ ባለፈው የ2013 ምርጫ፣ ፓርቲው የተጋነነ ውጤት ጠብቆ እንደነበር አስታውሰው፣ ከዚያ ስህተታችን በመማር በዘንድሮው ምርጫ ግን የተመጠነ ውጤት እንደሚጠብቁ ("managed expectation" እንዳላቸው) ገልጸዋል።

አቶ ኢዮብ አክለውም፣ በዚህ ምርጫ ኢዜማ በፓርላማ መንግሥት መመሥረት የሚያስችል ድምፅ ባያገኝም፣ ያለውን የውክልና ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ፣ በፓርላማ ትልቁ ተቃዋሚ ፓርቲ ለመሆን አልሞ እንደሚንቀሳቀስ ጠቁመዋል። አቶ ኢዮብ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ሒደትን በአጭር ርቀት ሳይሆን በረዥም ርቀት ሩጫ እንደሚመሰል ተናግረዋል። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
7
😁 4
4 5.6K
avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
28.03.2026 14:57
ትበብር ለኢትዮጵያ አንድነት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥን የተከተለ የፌደራል ሥርዓት እንደሚከተልና የቤትና የቦታ ግብርን እንደሚቀንስ ይፋ ባደረገው ማኒፌስቶ ገልጿል።

ትብብሩ በ7 ኛው አገራዊ ምርጫ የሚወዳደርበትን ማኒፌስቶ ዛሬ መጋቢት 19/2018 ዓ.ም አስተዋውቋል።

የፌደራል አወቃቀሩን በተመለከተ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥን የህዝብ አሰፋፈርን፣ ኢኮኖሚ እድገትን፣ አስተዳደራዊ የልማት አመችነትን እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊ ትስስሮችን መሠረት ያደረገ ፌደራላዊ የመንግስት አወቃቀር እንዲኖር እንደሚያደርግም ትብብሩ አስታውቋል።

ከመኖሪያ ቤቶች ጋር ተያይዞም በሽያጭ ታክስ የቤትና የቦታ ግብር መጠኑን እንደሚቀንስ በማኒፌስቶው አብራርቷል። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
14
👍 4
👏 2
😁 2
4 6.4K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
27.03.2026 22:28
በጋምቤላ ክልል ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ወቅት “በጥፋት ድርጊቶች ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸው ተረጋግጧል” ከተባሉ 272 የፖሊስ አባላት ውስጥ የ62ቱ ጉዳይ በህግ እየታየ መሆኑን አንድ የክልሉ ከፍተኛ ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

ከዚህ ክስተት ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ 642 የፖሊስ እና የአድማ ብተና አባላትን ከስራ ማሰናበቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በክልሉ ፖሊሶች ላይ ይህን እርምጃ የወሰደው፤ ሁሉንም ያካተተ የተሃድሶ ስልጠና እና ግምገማ ካደረገ በኋላ መሆኑን ገልጿል። በጋምቤላ ክልል ከተከሰተው የጸጥታ ችግር በኋላ በክልሉ ያሉ የመደበኛ ፖሊስ አባላት እና የአድማ ብተና ፖሊሶች የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ የተደረገው፤ በመከላከያ ሰራዊት ዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ማሰልጠኛ ነበር።

ወደ ማሰልጠኛ ተቋሙ ላልገቡ ቀሪ የፖሊስ አባላት፤ ኮሚሽኑ “አካላዊ የግምገማ መድረክ” በማዘጋጀት “ሂስ እና ግለሂስ” እንዲያካሄዱ አድርጓል።

ይህንን ተከትሎ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ፤ በሰራዊቱ መተዳደሪያ ደንብ እና የፖሊስ የስነ ምግባር መመሪያ መሰረት “ዝርዝር ግምገማ” ማድረጉ ዛሬ አርብ መጋቢት 18፤ 2018 በተሰራጨ መረጃ ላይ ተመልክቷል።

የዲስፕሊን ኮሚቴው ባካሄደው ግምገማ፤ በፖሊስ አባላቱ የተፈጸሙ “ጥፋቶችን” መለየቱም ተጠቁሟል። “የጥፋት ድርጊት ፈጽመዋል” ተብለው ከተጠረጠሩ የፖሊስ አባላት መካከል 17ቱ በጋምቤላ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ እና ማስረጃ እየተሰበሰበባቸው እንደሆነ አንድ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️https://ethiopiainsider.com/2026/17717/

@EthiopiaInsiderNews
9
👍 2
10 5.6K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
27.03.2026 19:55
ቪዲዮ፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዛሬ አርብ መጋቢት 18፤ 2018 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል “በፖለቲካ አመለካከታቸው እና በማንነታቸው ምክንያት ለእስር ተዳርገዋል” የተባሉ ሰዎችን ማስፈታት የተመለከተው ይገኝበታል። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት፤ ከሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን 11 ኮሚሽነሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አጎ ናቸው።

“በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን እስረኞችን ማስፈታት” በተደጋጋሚ የሚቀርብ ጥያቄ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነር ሙሉጌታ፤ ጉዳዩ “ጥንቃቄ የሚጠይቅ” መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። “አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ሰዎች በቁጥጥር ስር በሚገቡበት ጊዜ አንደኛው ወንጀል የፈጸመ ሰው ይኖራል። ያለ አግባብም ደግሞ በጥርጣሬ የሚያዝ ሰው ይኖራል። በዚህ መነሻ በአጠቃላይ እስር ላይ ያሉ ሰዎች ‘በህገወጥ መንገድ የታሰሩ ናቸው’ ብሎ መወሰን ወይም ያንን መፍረድ የተሳሳተ ሊሆን ይችላል” ብለዋል ኮሚሽነሩ።

“እስረኞችን ማስፈታት የኮሚሽኑ ስራ አይደለም” ያሉት ሙሉጌታ፤ እንዲያም ሆኖ ተቋሙ “ለስራው መሳካት” ሲል ስለታሰሩ ሰዎች “ለመንግስት ማሳሰቢያ ሰጥቶ እንዲፈቱ ማድረግን” በበጎ ጎኑ እንደሚመለከተው አስረድተዋል። “ወንጀል የፈጸሙ፣ ሰው የገደሉ፣ በተለያዩ ምክንያቶች የታሰሩ ሰዎችን እናስፈታለን ብንል ተመልሶ ሀገርን ወደማተራመስ ይገባል። ወንጀለኞች እንዲነግሱ የማድረግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል እርሱ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል” ሲሉም ኮሚሽነሩ አሳስበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴 የኮሚሽነር ሙሉጌታን ሙሉ ቃል ይህን ሊንክ ይጫኑ➡️ https://youtu.be/b3sGiN6EzsI

@EthiopiaInsiderNews
15
😁 6
5.4K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
27.03.2026 13:33
ከትግራይ ክልል ለሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎች የሚሰበሰቡበት መርሃ ግብር በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። በመርሃ ግብሩ የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ ላይ 400 ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኮሚሽኑ ገልጿል።

ከተሳታፊዎቹ ውስጥ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እንደሚገኙበት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናግረዋል። ፕሮፌሰር መስፍን በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የትግራይ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደትን በክልሉ ለማካሄድ ብዙ ጥረቶች ቢደረጉም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ህወሓት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ አመልክተዋል።

ኮሚሽነሩ ከአንድ ወር በፊት ከፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በነበራቸው ስብሰባ፤ “በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ሀገራዊ ምክክር ማካሄድ ቅንጦት ነው” የሚል ምላሽ ከህወሓት እንደሰጣቸው ተናግረው ነበር። ፕሮፌሰር መስፍን በዛሬው መግለጫቸው “የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አሁንም በሩን ዘግቶብናል ብለን አንጠብቅም” ሲሉ ተደምጠዋል።

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የትግራይ አጀንዳ ማሰባሰብ መድረክም በአዲስ አበባ ለማካሄድ ቢወስንም፤ ቀጣይ ስራዎችን ለማከናወን በክልሉ ውስጥ ተንቀሳቅሶ መስራቱን እንደሚቀጥል አክለዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራዎቹን ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች አከናውኖ አጠናቅቋል።

በመጪው ሳምንት በአዲስ አበባ በሚካሄደው መድረክ፤ የትግራይ ተወላጆች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የምክክር ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን የሚያቀርቡ ይሆናል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@EthiopiaInsiderNews
7
😁 7
🔥 1
6 5.3K
avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
26.03.2026 17:11
ህዳሴ ፓርቲ በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዕጩዎችን ያቀረበ ፓርቲ ሆነ

"ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ያቀረቧቸውን ዕጩዎች ቁጥር የተመለከተች ሲሆን፣ ህዳሴ ፓርቲ ለከተማው ምክር ቤት 142 እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23 ዕጩዎችን በማቅረብ በድምሩ 165 ዕጩዎችን በማስመዝገብ ከፍተኛ ተወዳዳሪዎችን ያቀረበ ፓርቲ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። በመከተልም፣ ብልጽግና ፓርቲ ለከተማው ምክር ቤት 134 እና ለፓርላማ 20፣ በድምሩ 154 እንዲሁም ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለከተማው ምክር ቤት 132 እና ለፓርላማ 22፣ በድምሩ 152 ዕጩዎችን በማቅረብ በተወዳዳሪዎች ብዛት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።

ህዳሴ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ለ23ቱም የአዲስ አበባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች የሚወዳደሩ ሙሉ ዕጩዎችን ያቀረቡ ብቸኛዎቹ ፓርቲዎች ሆነዋል። ይሁን እንጂ አንድም የፖለቲካ ፓርቲ ለሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሙሉ 158 መቀመጫዎች የሚሆኑ ዕጩዎች አላቀረበም።

ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እና የፓርላማ መቀመጫዎች ዕጩ ያቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብዛት 21 ሲሆን፣ ለአዲስ አበባ የፓርላማ ወንበሮች የሚወዳደሩ ሦስት እና ለከተማው ምክር ቤት የሚወዳደሩ 7 የግል ዕጩዎች መኖራቸው ተመላክቷል። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection @EthioElections
12
😁 7
7 6.1K
avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
26.03.2026 15:28
ኢዜማ በ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘገባ የተሰማውን ቅሬታ አቀረበ

“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትላንት ሐሙስ፣ መጋቢት 16፤ “ገዢው ፓርቲ የኢዜማ መሪና ምክትላቸው ለፓርላማ በሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ” በሚል ርዕስ ለንባብ ላበቃው ዜና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰማውን ቅሬታ ለዝግጅት ክፍሉ በደብዳቤ አድርሷል።

ኢዜማ ዘገባውን “በተሳሳተና የጋዜጠኝነት ስነምግባርን ባልተከተለ መልኩ አንባቢያን የተሳሳተ ግምት እንዲወስዱ በሚያደርግ” መንገድ ተዘጋጅቷል ያለ ሲሆን፣ ሚዲያው “በፓርቲው ላይ የያዘውን የተዛባ አቋም በግልፅ የሚያሳይ እና ከአንድ ለእውነት እቆማለሁ ብሎ ከተነሳ ሚዲያ የማይጠበቅ እንዲሁም የጋዜጠኝነትን ስነምግባር ያልተከተለ ዘገባ ከፍተኛ ቅሬታ ተሰምቶናል።” ብሏል።

ሙሉውን የፓርቲውን የቅሬታ ድብዳቤ እዚህ ያንብቡ፤ https://ethioelections.com/2026/03/17436/
😁 15
5
👎 2
3 5.2K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
25.03.2026 11:41
ገዢው ፓርቲ የኢዜማ መሪና ምክትላቸው ለፓርላማ በሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ

የአዲስ አበባ ከተማ ካሉት 23 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች መካከል ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በሦስት የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ። ብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎቹን ካላቀረበባቸው የምርጫ ክልሎች ሁለቱ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ እና ምክትላቸው የሚወዳደሩባቸው ናቸው።

ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ግንቦት ወር 24፣ 2018 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ፤ አዲስ አበባን በመወከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለከተማይቱ ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎቹን የማስተዋወቂያ መድረክ ያካሄደው ከአንድ ሳምንት በፊት መጋቢት 3፤ 2018 ነበር። በከተማ ደረጃ ከተካሄደው ከዚህ መድረክ በኋላ የፓርቲው ዕጩዎች በየሚወዳደሩባቸው ክፍለ ከተሞች በመገኘት በተመሳሳይ መርሃ ግብሮች ሲሳተፉ ቆይተዋል።

ገዢው ፓርቲ ለዘንድሮ ምርጫ የአዲስ አበባ የፓርላማ መቀመጫ ካቀረባቸው 20 ዕጩዎች መካከል 16ቱ በስድስተኛው ዙር ምርጫ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ያልነበሩ መሆናቸውን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ፓርቲው ካሰራጫቸው መረጃዎች ተገንዝባለች። ከእነዚህ አዲስ የፓርላማ ተወዳዳሪዎች መካከል አምስቱ ሚኒስትሮች ሲሆኑ ሦስቱ ደግሞ ሚኒስትር ዴኤታዎች ናቸው።

ከሚኒስትሮቹ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተመራጮች መካከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ይገኙበታል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethioelections.com/2026/03/17427/

@EthiopiaInsiderNews
16
😁 12
👍 1
11 6.8K
avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
23.03.2026 17:20
ብልፅግና፣ ኢዜማና ትብብር ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የእጩዎች ቁጥር ያስመዘገቡ ሦስት ፓርቲዎች ሆኑ

“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተው ድምር ፖለቲካ ፓርቲዎች ያስመዘገቧቸው ዕጩዎች ቁጥር እንደሚያሳየው ብልፅግና ፓርቲ 2950፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) 1256፣ እና ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት (ትብብር ለኢትዮጵያ) 1032 ዕጩዎችን ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች በማስመዝገብ ከፍተኛ የዕጩዎች ቁጥር ያስመዘገቡ ሦስት ፓርቲዎች ሆነዋል።

547 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 2919 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች፣ በድምሩ 3466 መኖራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ የሚያሳይ ሲሆን፣ አንድም ፓርቲ ሁሉም ምክር ቤት መቀመጫዎችን ወክሎ የሚወዳደር ዕጩ አላቀረበም። ከፍተኛ የዕጩዎች ቁጥር ያቀረበው ብልፅግና ፓርቲም ያቀረባቸው ዕጩዎች ብዛት በ516 ዕጩዎች ያንሳል። የልዩነቱን ምንጭ ዝርዝሩ እንደደረሰን እናቀርባለን።

#ምርጫ2018 #EthiopiaElection @EthioElections
👍 7
3
👎 3
😁 3
13 7K
avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
23.03.2026 13:41
የኢንተርኔት ተደራሽነት መቆራረጥ በዲጂታል የሞርጫ ምዝገባ ሂደት ላይ ችግር እንደፈጠረበት እና በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ ማኑዋል ምዝገባ ሊመለስ እንደሚችል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላት ወርቅ ኃይሉ የኔትወርክና የሲስተም መቆራረጥ በዲጂታል የምርጫ ምዝገባ ላይ ችግር እየፈጠረብን ነው በማለት ዛሬ፣ መጋቢት 14፣ 2018 በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች ስምና መለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተል ለመወሰን በተዘጋጅ ሥነ ሥርዓት መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

የኔትወርክ ተደራሽነትና ችግርና መቆራረጥን ለመፍታት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ንግግር መጀመራቸውን የገለፁት ወይዘሮ ሜላት ወርቅ፣ ይሁን እንጂ የምዝገባ መዘግየት እንዳይፈጠር "ኔትዎርክ በሚያስቸግርባቸው አካባቢዎች ከዲጂታል ውጭ በሆነ በተለመደው አካሄደ ምዝገባውን ለማከናወን እንገደዳለን" ብለዋል።

የምዝገባ ሂደቱን በተመለከተ እስካሁን ከ47 ሺህ 7 መቶ 54 የምርጫ ጣቢያዎች በተደረገ ምዝገባ ከ18 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ቦርዱ አስታውቋል።

የዕጩ ተፎካካሪ ግለሰቦችንና ፓርቲዎችን ስም በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፋቸውንም ቦርዱ ገልጿል ።

በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች ስምና የመለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተል ለመወሰን የዕጣ ማውጣት ሥነሥርዓት በዛሬው ዕለት እንደሚከናወን ታውቋል። [ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
8
😁 6
8 6.2K
avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
19.03.2026 21:29
በሽብር ወንጀል ተጠርጥራ ሶስት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ ያለችው ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፤ ባጋጠማት የጤና እክል ምክንያት በራሷ ወጪ ፍራሽ ለመግዛት እንዲፈቀድላት ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቀረበች። ጋዜጠኛዋ ጥያቄዋን በዛሬው ዕለት በጠበቃዋ በኩል ያቀረበችው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።

የተከሳሿ ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት፤ ጋዜጠኛ ገነት ባለፉት ሁለት ዓመታት በኩላሊት ህመም ውስጥ ቆይታለች። ደንበኛቸው በቅርብ ጊዜ ባደረገችው ምርመራ በሁለቱም ኩላሊቶቿ ላይ “ጠጠር” መገኘቱን የገለጹት ጠበቃው፤ በህመሟ ምክንያት “ለመቀመጥ እና መተኛት” መቸገሯን አስረድተዋል።

ጋዜጠኛ ገነት በታሰረችበት ማረሚያ ቤት የሚገኘው ፍራሽ “ቶሎ የሚጎደጉድ” በመሆኑ ህመሟን ሊያስታግስላት እንዳልቻለም አቶ ሰለሞን ገልጸዋል። በሀኪም ትዕዛዝ መሰረት ማረሚያ ቤቱ “ተስማሚ እና በቀላሉ የማይጎረጉድ ፍራሽ እንዲያቀርብ” ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠበቃው አክለዋል።

ሆኖም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለሁሉም ታራሚዎች እያቀረበ ካለው ውጪ የተለየ ፍራሽ እንደማያቀርብ ምላሽ መስጠቱን ጠበቃው ተናግረዋል። ይህን ምላሽ መሰረት በማድረግ ጋዜጠኛ ገነት በራሷ ወጪ ፍራሽ ለመግዛት ከማረሚያ ቤቱ ፈቃድ ብትጠየቅም፤ ተቋሙ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልደረሰው በቀር ጥያቄውን እንደማያስተናግድ ማሳወቁን አቶ ገዛኸኝ አብራርተዋል።

የማረሚያ ቤቱን ምላሽ በመንተራስም ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 10፤ 2018 ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ፣ አንደኛ የህገ መንግስት እና ሕገ መንግስት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት አቤቱታ ማስገባታቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17697/

@EthiopiaInsiderNews
😢 15
13
😭 4
🙏 2
😁 1
😱 1
10 9.2K

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram