ገዢው ፓርቲ የኢዜማ መሪና ምክትላቸው ለፓርላማ በሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ
የአዲስ አበባ ከተማ ካሉት 23 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች መካከል ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በሦስት የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ። ብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎቹን ካላቀረበባቸው የምርጫ ክልሎች ሁለቱ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ እና ምክትላቸው የሚወዳደሩባቸው ናቸው።
ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ግንቦት ወር 24፣ 2018 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ፤ አዲስ አበባን በመወከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለከተማይቱ ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎቹን የማስተዋወቂያ መድረክ ያካሄደው ከአንድ ሳምንት በፊት መጋቢት 3፤ 2018 ነበር። በከተማ ደረጃ ከተካሄደው ከዚህ መድረክ በኋላ የፓርቲው ዕጩዎች በየሚወዳደሩባቸው ክፍለ ከተሞች በመገኘት በተመሳሳይ መርሃ ግብሮች ሲሳተፉ ቆይተዋል።
ገዢው ፓርቲ ለዘንድሮ ምርጫ የአዲስ አበባ የፓርላማ መቀመጫ ካቀረባቸው 20 ዕጩዎች መካከል 16ቱ በስድስተኛው ዙር ምርጫ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ያልነበሩ መሆናቸውን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ፓርቲው ካሰራጫቸው መረጃዎች ተገንዝባለች። ከእነዚህ አዲስ የፓርላማ ተወዳዳሪዎች መካከል አምስቱ ሚኒስትሮች ሲሆኑ ሦስቱ ደግሞ ሚኒስትር ዴኤታዎች ናቸው።
ከሚኒስትሮቹ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተመራጮች መካከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ይገኙበታል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethioelections.com/2026/03/17427/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram