በሽብር ወንጀል ተጠርጥራ ሶስት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ ያለችው ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፤ ባጋጠማት የጤና እክል ምክንያት በራሷ ወጪ ፍራሽ ለመግዛት እንዲፈቀድላት ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቀረበች። ጋዜጠኛዋ ጥያቄዋን በዛሬው ዕለት በጠበቃዋ በኩል ያቀረበችው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
የተከሳሿ ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት፤ ጋዜጠኛ ገነት ባለፉት ሁለት ዓመታት በኩላሊት ህመም ውስጥ ቆይታለች። ደንበኛቸው በቅርብ ጊዜ ባደረገችው ምርመራ በሁለቱም ኩላሊቶቿ ላይ “ጠጠር” መገኘቱን የገለጹት ጠበቃው፤ በህመሟ ምክንያት “ለመቀመጥ እና መተኛት” መቸገሯን አስረድተዋል።
ጋዜጠኛ ገነት በታሰረችበት ማረሚያ ቤት የሚገኘው ፍራሽ “ቶሎ የሚጎደጉድ” በመሆኑ ህመሟን ሊያስታግስላት እንዳልቻለም አቶ ሰለሞን ገልጸዋል። በሀኪም ትዕዛዝ መሰረት ማረሚያ ቤቱ “ተስማሚ እና በቀላሉ የማይጎረጉድ ፍራሽ እንዲያቀርብ” ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠበቃው አክለዋል።
ሆኖም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለሁሉም ታራሚዎች እያቀረበ ካለው ውጪ የተለየ ፍራሽ እንደማያቀርብ ምላሽ መስጠቱን ጠበቃው ተናግረዋል። ይህን ምላሽ መሰረት በማድረግ ጋዜጠኛ ገነት በራሷ ወጪ ፍራሽ ለመግዛት ከማረሚያ ቤቱ ፈቃድ ብትጠየቅም፤ ተቋሙ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልደረሰው በቀር ጥያቄውን እንደማያስተናግድ ማሳወቁን አቶ ገዛኸኝ አብራርተዋል።
የማረሚያ ቤቱን ምላሽ በመንተራስም ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 10፤ 2018 ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ፣ አንደኛ የህገ መንግስት እና ሕገ መንግስት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት አቤቱታ ማስገባታቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17697/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram