ቪዲዮ፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዛሬ አርብ መጋቢት 18፤ 2018 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል “በፖለቲካ አመለካከታቸው እና በማንነታቸው ምክንያት ለእስር ተዳርገዋል” የተባሉ ሰዎችን ማስፈታት የተመለከተው ይገኝበታል። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት፤ ከሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን 11 ኮሚሽነሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አጎ ናቸው።
“በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን እስረኞችን ማስፈታት” በተደጋጋሚ የሚቀርብ ጥያቄ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነር ሙሉጌታ፤ ጉዳዩ “ጥንቃቄ የሚጠይቅ” መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። “አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ሰዎች በቁጥጥር ስር በሚገቡበት ጊዜ አንደኛው ወንጀል የፈጸመ ሰው ይኖራል። ያለ አግባብም ደግሞ በጥርጣሬ የሚያዝ ሰው ይኖራል። በዚህ መነሻ በአጠቃላይ እስር ላይ ያሉ ሰዎች ‘በህገወጥ መንገድ የታሰሩ ናቸው’ ብሎ መወሰን ወይም ያንን መፍረድ የተሳሳተ ሊሆን ይችላል” ብለዋል ኮሚሽነሩ።
“እስረኞችን ማስፈታት የኮሚሽኑ ስራ አይደለም” ያሉት ሙሉጌታ፤ እንዲያም ሆኖ ተቋሙ “ለስራው መሳካት” ሲል ስለታሰሩ ሰዎች “ለመንግስት ማሳሰቢያ ሰጥቶ እንዲፈቱ ማድረግን” በበጎ ጎኑ እንደሚመለከተው አስረድተዋል። “ወንጀል የፈጸሙ፣ ሰው የገደሉ፣ በተለያዩ ምክንያቶች የታሰሩ ሰዎችን እናስፈታለን ብንል ተመልሶ ሀገርን ወደማተራመስ ይገባል። ወንጀለኞች እንዲነግሱ የማድረግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል እርሱ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል” ሲሉም ኮሚሽነሩ አሳስበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴 የኮሚሽነር ሙሉጌታን ሙሉ ቃል ይህን ሊንክ ይጫኑ➡️
https://youtu.be/b3sGiN6EzsI
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram