በጋምቤላ ክልል ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ወቅት “በጥፋት ድርጊቶች ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸው ተረጋግጧል” ከተባሉ 272 የፖሊስ አባላት ውስጥ የ62ቱ ጉዳይ በህግ እየታየ መሆኑን አንድ የክልሉ ከፍተኛ ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።
ከዚህ ክስተት ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ 642 የፖሊስ እና የአድማ ብተና አባላትን ከስራ ማሰናበቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ በክልሉ ፖሊሶች ላይ ይህን እርምጃ የወሰደው፤ ሁሉንም ያካተተ የተሃድሶ ስልጠና እና ግምገማ ካደረገ በኋላ መሆኑን ገልጿል። በጋምቤላ ክልል ከተከሰተው የጸጥታ ችግር በኋላ በክልሉ ያሉ የመደበኛ ፖሊስ አባላት እና የአድማ ብተና ፖሊሶች የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ የተደረገው፤ በመከላከያ ሰራዊት ዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ማሰልጠኛ ነበር።
ወደ ማሰልጠኛ ተቋሙ ላልገቡ ቀሪ የፖሊስ አባላት፤ ኮሚሽኑ “አካላዊ የግምገማ መድረክ” በማዘጋጀት “ሂስ እና ግለሂስ” እንዲያካሄዱ አድርጓል።
ይህንን ተከትሎ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ፤ በሰራዊቱ መተዳደሪያ ደንብ እና የፖሊስ የስነ ምግባር መመሪያ መሰረት “ዝርዝር ግምገማ” ማድረጉ ዛሬ አርብ መጋቢት 18፤ 2018 በተሰራጨ መረጃ ላይ ተመልክቷል።
የዲስፕሊን ኮሚቴው ባካሄደው ግምገማ፤ በፖሊስ አባላቱ የተፈጸሙ “ጥፋቶችን” መለየቱም ተጠቁሟል። “የጥፋት ድርጊት ፈጽመዋል” ተብለው ከተጠረጠሩ የፖሊስ አባላት መካከል 17ቱ በጋምቤላ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ እና ማስረጃ እየተሰበሰበባቸው እንደሆነ አንድ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17717/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram