ቪዲዮ፦ በአዲስ አበባ በሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ተቋማት ሰራተኞች እና ኃላፊዎች ላይ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሚኖራቸው “የዳኝነት ስልጣን” በፓርላማ አከራከረ። ለኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣኑን የሰጠው፤ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 24፤ 2018 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የተሻሻለው የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ነው።
በኢትዮጵያ እስካሁን በስራ ላይ የቆየው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ በ1954 ዓ.ም የወጣ ነበር። ከ60 ዓመት በላይ በስራ ላይ የቆየውን ይህን ህግ የሚያሻሻል አዋጅ፤ በዛሬው የፓርላማ ስብሰባ በሁለት ተቃውሞ፤ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
አዋጁ ከመጽደቁ አስቀድሞ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) ወክለው የፓርላማ አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እና ዶ/ር አበባው ደሳለኝ “አወዛጋቢ” ባሏቸው አንቀጾች ላይ ጥያቄዎች አንስተዋል።
ጥያቄ ካስነሱ ድንጋጌዎች መካከል “የኦሮሚያ ክልል የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከስራ ኃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ በሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ላይ፤ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ይኖራቸዋል” የሚለው ይገኝበታል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴በዚህ ድንጋጌ ላይ የቀረበውን ጥያቄ እና ምላሽ ሙሉ ቪዲዮ ለመመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ ➡️
https://youtu.be/AMv-OdFuMMQ
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram