avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
29.03.2026 17:02
ኢዜማ መንግሥት ለመመሥረት የሚያበቃ ዕጩ ያስመዘገብኩ ብቸኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ብሆንም፣ የምጠብቀውን ውጤት መጥኛለሁ አለ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ፣ መጋቢት 19፣ 2018 እያካሔደ ባለው የበይነመረብ ስብሰባ፣ መሪው አቶ ኢዮብ መሣፍንት ኢዜማ 299 ዕጩዎችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ዕጩ አድርጎ በማቅረብ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ሆኖ ወደ ውድድሩ መግባቱን ገልጸዋል። ሆኖም፣ ባለፈው የ2013 ምርጫ፣ ፓርቲው የተጋነነ ውጤት ጠብቆ እንደነበር አስታውሰው፣ ከዚያ ስህተታችን በመማር በዘንድሮው ምርጫ ግን የተመጠነ ውጤት እንደሚጠብቁ ("managed expectation" እንዳላቸው) ገልጸዋል።

አቶ ኢዮብ አክለውም፣ በዚህ ምርጫ ኢዜማ በፓርላማ መንግሥት መመሥረት የሚያስችል ድምፅ ባያገኝም፣ ያለውን የውክልና ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ፣ በፓርላማ ትልቁ ተቃዋሚ ፓርቲ ለመሆን አልሞ እንደሚንቀሳቀስ ጠቁመዋል። አቶ ኢዮብ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ሒደትን በአጭር ርቀት ሳይሆን በረዥም ርቀት ሩጫ እንደሚመሰል ተናግረዋል። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection
7
😁 4
4 5.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram