የ“አዲስ ስታንዳርድ” የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው ጋዜጠኛ ሚሊዮን በየነ በትላንትናው ዕለት ረፋድ ላይ “ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች” ከተወሰደ በኋላ እስከ ዛሬ ድረስ የደረሰበት እንዳልታወቀ ተቋሙ አስታወቀ።
ጋዜጠኛው ስለሚገኝበት ቦታ እና ሁኔታ ለተቋሙም ሆነ ለቤተሰቦቹ ያስታወቀ አካል ባለመኖሩ “ከፍተኛ ስጋት” እንደፈጠረባቸው የመገናኛ ብዙሃኑ ዋና አዘጋጅ አቶ ዮናስ ከድር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
በጋዜጠኝነት ከ20 ዓመት በላይ ልምድ ያለው ሚሊዮን “አዲስ ስታንዳርድን” የዛሬ አራት ዓመት ከመቀላቀሉ በፊት፤ በቀድሞው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ውስጥ በዚሁ ሙያ አገልግሏል።
በበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃኑ በተለያዩ የአርታኢነት ደረጃዎች ሲሰራ የቆየው ሚሊዮን፤ ሲኤምሲ ሚካኤል አካባቢ ከሚገኘው የተቋሙ ዋና ቢሮ ሲቪል በለበሱ ሰዎች የተወሰደው ትላንት ረቡዕ ሚያዝያ 7፤ 2018 ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ40 ገደማ ላይ እንደሆነ አቶ ዮናስ ገልጸዋል።
ማንነታቸው ያልታወቀው እነዚሁ ግለሰቦች ወደ ቢሮው በመግባት ጋዜጠኛውን “ለጥያቄ እንፈልግሃለን” በማለት ይዘውት ሲወጡ፤ በደህንነት ካሜራ (CCTV) መታየታቸውን ዋና አዘጋጁ ተናግረዋል።
ግለሰቦቹ የጋዜጠኛውን “ስልክ ሲቀበሉ” እና “ላፕቶፕ በእጁ ይዞ ሲሄድ” በደህንነት ካሜራው መመልከታቸውንም አቶ ዮናስ አስረድተዋል።
የ“አዲስ ስታንዳርድ” አሳታሚ የሆነው ጃኬን አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ትላንት ባወጣው መግለጫ፤ ግለሰቦቹ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የነበረው “በታቀደ እና በተደራጀ መልኩ” እንደነበርም ድርጅቱ አክሏል።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17749/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram