avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
01.04.2026 18:05
ቪዲዮ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 23፤ 2018 የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውን የስምንት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት፤ የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ዘለግ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ ችግሩ በሰርጡ መዘጋት ብቻ የተገደበ እንዳልሆነ ገልጸው፤ አምራች ሀገራት በጦርነት እና ቀውስ ውስጥ በመሆናቸው “የነዳጅ የማምረት ሥራ መቆሙን” እና “የማጣራት ስራ” በእጅጉ ማሽቆልቆሉን ገልጸዋል። ይህ ሁኔታ የዓለም ነዳጅ ዋጋ በአንድ ጊዜ “በሶስት እጥፍ እንዲያሻቅብ” ማድረጉንም አመልክተዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት ሳቢያ ኢትዮጵያ በመደበኛ ግዢ ስርዓት ወደ ሀገር ውስጥ ልታስገባው በነበረው 180 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነዳጅ የማስተላለፍ ሂደት ላይ መስተጓጎል መግጠሙን ዶ/ር ካሳሁን ተናግረዋል።

የቤንዚን አቅርቦት ከ80 እስከ 100 በመቶ እየተሸፈነ በመሆኑ “እጥረት እንደሌለ” የገለጹት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ፤ በነጭ ናፍጣ እና በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ ግን አቅርቦቱ በሚፈልገው ልክ መሆን እንዳልቻለ አስረድተዋል። በነጭ ናፍጣ እና በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ 50 በመቶ አቅርቦት ለማረጋገጥ ጥረት መደረጉን ዶ/ር ካሳሁን ጠቁመዋል።

የነዳጅ አቅርቦቱ እንዴት መቀዳደም መኖር እንዳለበት “ልዩ ውሳኔ መተላለፉን” እና ይህንኑ ክትትል የሚያደርግ የሁኔታዎች ልዩ መከታተያ ክፍል (situation room) መቋቋሙን አብራርተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ስለ ነዳጅ አቅርቦት የሰጡትን ማብራሪያ ይህን ሊንክ https://youtu.be/s6SUNZthg4o ተጭነው ይመልከቱ።

@EthiopiaInsiderNews
5
6 5.3K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram