ኢትዮጵያ በዘንድሮው በጀት ዓመት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 6.76 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህ የገንዘብ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ2.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ እድገት ያለው መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 23፤ 2018 የስምንት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በዚሁ ስብሰባ ላይ፤ የዘንድሮው የስምንት ወራት ገቢ በኢትዮጵያ ታሪክ “ተገኝቶ የማይታወቅ” መሆኑን ተናግረዋል።
ሆኖም የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ፤ የስምንት ወራቱ የወጪ ንግድ አፈጻጸም በ2018 ይደረስበታል ተብሎ ከታቀደው የሶስት ዓመቱ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ የሆነበትን ምክንያት ማብራሪያ እንዲሰጥበት ጠይቋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክትትል የሚያደርግባቸው የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ሰብሎች እና የእንስሳት መኖ የወጪ ንግድ አፈጻጸምም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ዝቅ ያለበትን ምክንያት እንዲገለጽም ቋሚ ኮሚቴው በተመሳሳይ ጥያቄ አቅርቧል።
🔴ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17721/
🔴 የዛሬውን የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ስብሰባን በቪዲዮ ለመመልከት ➡️
https://youtu.be/ub0NqeoHMeU
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram