avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
15.04.2026 23:57
ዘንድሮ የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት መታቀዱ፤ የመሰረተ ልማት ባልተሟላባቸው አካባቢዎች ባሉ ተማሪዎች ውጤት ላይ “ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ” ሊኖረው እንደሚችል የፓርላማ አባላት ስጋታቸውን ገለጹ።

ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ 122 ሺህ የመፈተኛ ኮምፒውተሮች መዘጋጀታቸውን እና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል የተለያዩ የመንግስት አካላትን የያዘ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ገልጿል።

ይህ የተገለጸው የትምህርት ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ረቡዕ ሚያዝያ 7፤ 2018 ባቀረበበት ወቅት ነው።

የተቋሙን የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው በንባብ ያቀረቡት፤ በሚኒስቴሩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እሸቱ ገላዬ ናቸው።

አቶ እሸቱ በዚሁ ሪፖርታቸው የዘንድሮውን ሀገር አቀፍ ፈተና “መቶ በመቶ በበይነ መረብ (online) ለመስጠት” ከክልል ፕሬዝዳንቶች እና ከትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ ስራዎችን ሲከናወኑ መቆየታቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። ይህ የሚኒስቴሩ እቅድ በፓርላማ የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ አባላት ጥያቄ ቀርቦበታል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄዎች በንባብ ያቀረቡት አቶ ታደሰ ጌጡ፤ ፈተናው በዚህ መልክ መሰጠቱ የኮምፒውተር፣ የመብራት እና የኔትወርክ መሰረተ ልማት ባልተሟላባቸው ትምህርት ቤቶች የሚፈተኑ ተማሪዎች ውጤት ላይ “ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ” ሊኖረው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። ይህን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ምን መፍትሔ እንዳለውም ማብራሪያ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17729/

@EthiopiaInsiderNews
6
😁 2
7 3.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram