Ethiopia Insider Переслано от канала 23.03.2026 13:41 Скопировать Пожаловаться የኢንተርኔት ተደራሽነት መቆራረጥ በዲጂታል የሞርጫ ምዝገባ ሂደት ላይ ችግር እንደፈጠረበት እና በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ ማኑዋል ምዝገባ ሊመለስ እንደሚችል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላት ወርቅ ኃይሉ የኔትወርክና የሲስተም መቆራረጥ በዲጂታል የምርጫ ምዝገባ ላይ ችግር እየፈጠረብን ነው በማለት ዛሬ፣ መጋቢት 14፣ 2018 በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች ስምና መለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተል ለመወሰን በተዘጋጅ ሥነ ሥርዓት መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል። የኔትወርክ ተደራሽነትና ችግርና መቆራረጥን ለመፍታት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ንግግር መጀመራቸውን የገለፁት ወይዘሮ ሜላት ወርቅ፣ ይሁን እንጂ የምዝገባ መዘግየት እንዳይፈጠር "ኔትዎርክ በሚያስቸግርባቸው አካባቢዎች ከዲጂታል ውጭ በሆነ በተለመደው አካሄደ ምዝገባውን ለማከናወን እንገደዳለን" ብለዋል። የምዝገባ ሂደቱን በተመለከተ እስካሁን ከ47 ሺህ 7 መቶ 54 የምርጫ ጣቢያዎች በተደረገ ምዝገባ ከ18 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ቦርዱ አስታውቋል። የዕጩ ተፎካካሪ ግለሰቦችንና ፓርቲዎችን ስም በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፋቸውንም ቦርዱ ገልጿል ። በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች ስምና የመለያ ምልክት አደራደር ቅደም ተከተል ለመወሰን የዕጣ ማውጣት ሥነሥርዓት በዛሬው ዕለት እንደሚከናወን ታውቋል። [ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር] #ምርጫ2018 #EthiopiaElection ❤ 8 😁 6 8 6.2K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram