በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ከታቀዱ ተማሪዎች መካከል 6.3 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑት አለመመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ለፓርላማ በላከው ሪፖርት አስታወቀ።
በአማራ፣ በትግራይ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙትን ጨምሮ 2,672 ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ የመማር ማስተማር ስራ አለመጀመራቸው፤ ተማሪዎቹ በትምህርት ገበታቸው ላይ ላለመገኘታቸው በሪፖርቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል።
“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተላከው ባለ 108 ገጽ ሪፖርት፤ የትምህርት ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም የዳሰሰ ነው።
የትምህርት ተደራሽነትን ማሳደግ በሚያትተው የሪፖርቱ ክፍል፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 33.5 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እንደነበር ሰፍሯል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በእቅድ ከያዘው የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት 19 በመቶውን ያህል ማሳካት እንዳልቻለ በሪፖርቱ ገልጿል።
በዚህም መሰረት ዘንድሮ በትምህርት ገበታ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ታቅዶ ከነበረው ውስጥ 6,380,932 ተማሪዎች መመዘገብ አለመቻላቸው ተጠቁሟል።
ተማሪዎቹ በትምህርት ገበታቸው ላይ ላለመገኘታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሪፖርቱ በምክንያትነት የጠቀሰው፤ 2,672 በላይ ትምህርት ቤቶች በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ ችግሮች ሳቢያ ምክንያት ስራ አለመጀመራቸውን ነው። ሆኖም ሪፖርቱ “ሰው ሰራሽ” እና “የተፈጥሮ” ያላቸውን ችግሮች አላብራራም።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17753/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram