avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
17.05.2026 19:01
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት 3 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳቧን አስታወቀ።

ይህም ከአለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲወዳደር ከ16 በመቶ በላይ እድገት ማስመዝገቡን ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

እንዲሁም በተመሳሳይ ወቅት ከ370 በላይ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃዶችን በመስጠት ከተቀመጠው ዕቅድ በላይ ተፈፃሚ መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም በኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ 2026 ፎረም 7 ግዙፍ ስምምነቶችን በማፅደቅ 13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል እንዲመዘገብ መደረጉ አገሪቱን እንደ ተወዳዳሪ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አድርጕታል ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
2
301
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
17.05.2026 18:09
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጎዴ እየተገነባ የሚገኘው በዓመት 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት ዐቅም ያለው ፋብሪካ ግንባታ በተያዘለት ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ መሆኑን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን በጎዴ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ የገመገሙ ሲሆን በፕሮጀክቱ ስፍራ የሚታየው የሥራ ሂደቱ ፍጥነት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ የኢንዱስትሪ እድገት እና በኢኮኖሚ ራስን የመቻል ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ኢንቨስትመንት መሆኑንም አስረድተዋል።

የማዳበሪያ ፋብሪካው በሚጠናቀቅበት ወቅት የሀገር ውስጥ የማምረት ዐቅምን ያጎለብታል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከውጭ በሚገባ ማዳበሪያ ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አርሶአደሮችን ይደግፋል ብለዋል።

እንዲሁም ለኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ፈጠራም አዳዲስ እድሎችን ይከፍታል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልፀዋል።


#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
3
359
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
17.05.2026 14:35
የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች :-

✅የዓለም ጤና ድርጅት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ኢቱሪ ግዛት የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ አሳሳቢ ዓለም አቀፍ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ነው ሲል አወጀ።

✅ዩክሬን ምሽቱን በሩሲያ መዲና ሞስኮ እና አካባቢው ላይ በፈፀመችው  የድሮን ጥቃት 4 ሰዎች ተገደሉ።

✅በናይጄሪያ ከ50 በላይ ሕጻናት በታጣቂዎች መታገታቸው ተነገረ።

✅የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራን የሰላም ስምምነት በአስቸኳይ ካልደረሰች ከባድ አደጋ ውስጥ ትገባለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

✅አሜሪካ እና እስራኤል በሚቀጥለው ሳምንት በቴህራን ላይ የአየር ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆኑን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።


#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
1 434
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
16.05.2026 16:10
605
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
16.05.2026 16:10
583
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
16.05.2026 16:09
441
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
16.05.2026 16:09
377
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
16.05.2026 15:20
የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች :-

✅የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ራስ ገዟ ታይዋን ነጻነቷን ከማወጅ መቆጠብ አለባት ሲሉ አስጠነቀቁ።

✅የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤል እና ሊባኖስ ከዚህ ቀደም የደረሱትን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማራዘም መስማማታቸውን አስታወቀ።

✅በዴሞክራቲክ ኮንጎ ምስራቃዊው የሀገሪቱ ግዛት በተከሰተ አዲስ የኢቦላ ወረርሽኝ የሞቱ 65 ሰዎች ቁጥር 80 መድረሱ ተነገረ።

✅የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ  በሀገሪቱ  የሚንቀሳቀሰው የአይ ኤስ ቁንጮ አመራር መገደሉን ተናገሩ።

✅ኢራቅ ባለፈው ወር ብቻ 10 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ለሀገራት መላኳን ገለፀች።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
497
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 21:03
ኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የምሽት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች

✅በ1 ሺህ 234 ወረዳዎች ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ልየታ መከናወኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።

✅በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ፣ ዕጩዎች ላይ የሚደርስ ማዋከብ፣ በታችኛው የመንግሥት መዋቅር ላይ ያሉ አስፈጻሚዎች የደንብ መተላለፍና የድምፅ መስጫ ቀን ይራዘም የሚሉት አስተያየቶች ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች እንደቀረቡለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

✅ከአበዳሪ ተቋማትና ከአጋር አገራት ጋር ሲደረግ የቆየው የዕዳ ሽግሽግ ድርድር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን እና በቀጣይ ጊዜያት መንግስት ወደ ዕዳ ክፍያ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

✅ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል በደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ከ106 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ200 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
1
1 623
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 18:12
በ1 ሺህ 234 ወረዳዎች ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የመለየት ስራ መከናወኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ይሄንን ያስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የእስካሁን ተግባራትና ቀጣይ አቅጣጫ የሚገመግም መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በተካሄደበት ወቅት ሲሆን አካታችና አሳታፊ የሆነ የምክክር ተሳታፊዎች የመለየት ስራ የኢትዮጵያን 93 በመቶ የሸፈነ በ1 ሺህ 234 ወረዳዎች መካሄዱንም ጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል ምክክሩን ለማድረግ የሚያስችል መድረክ በአዲስ አበባና በመቐለ ከተማ 22 ጊዜ ቢደረግም ባለው ምቹ ያልሆነ ሁኔታ በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች ምክክር ለማድረግ አለመቻሉን የጠቀሰው ኮሚሽኑ ዋናውን የምክክር ጉባኤ ማካሄድና ስምምነት የተደረሰባቸውን ውጤቶችና ምክረ ሀሳቦች ተፈፃሚነት ማመቻቸት ቀጣይ ስራዎቹ መሆናቸውንም ይፋ አድርጓል

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
👍 1
2 622
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 18:08
ከአበዳሪ ተቋማትና ከአጋር አገራት ጋር ሲደረግ የቆየው የዕዳ ሽግሽግ ድርድር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን እና በቀጣይ ጊዜያት መንግስት ወደ ዕዳ ክፍያ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ9 ወራት አፈጻጸሙን በተመለከተ ባካሄደው መድረክ በቀጣይ ቀሪ የሥራ ጊዜያት መንግስት ወደ ዕዳ ክፍያ እንደሚገባ ጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ አማካኝነት በውጭ ምንዛሪ ክምችት፣ በኤክስፖርት፣ በውስጥ ገቢ አሰባሰብና በመሳሰሉት ረገድ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ገልጿል።


#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
549
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 17:06
የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች :-

✅እስራኤል ዛሬ በጋዛ በፈፀመችው የድሮን ጥቃት ሁለት ፍልስጤማውያን ተገደሉ።

✅የቻይና ጉብኝታቸውን ያጠናቀቁት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቤጂንግ 200 የቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት መስማማቷን ተናገሩ።

✅በዴሞክራቲክ ኮንጎ ምስራቃዊው የሀገሪቱ ግዛት በተከሰተ አዲስ የኢቦላ ወረርሽኝ 65 ሰዎች ሞቱ።

✅የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢራን ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ።

✅አሜሪካ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሚያስተዳድራቸው የድሮን ፋብሪካዎች ውስጥ የሚሰሩ የ6 አመራሮች አድራሻን ለጠቆመ የ15 ሚሊየን ዶላር ወሮታ እከፍላለሁ ብላለች።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
492
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 16:47
ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉኝ የሚሏቸውን ቅሬታዎቻቸውን በማስረጃ አስደግፈው ማቅረብ እንደሚችሉ አስታወቀ።

ቦርዱ ይሄን ያለው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሁናዊ ሂደት ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችንና መፍትሔዎቻቸውን አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተወያየበት መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ የተሳተፉ ፓርቲዎች በተወሠኑ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ፣ ዕጩዎች ላይ የሚደርስ ማዋከብ፣ በታችኛው የመንግሥት መዋቅር ላይ ያሉ አስፈጻሚዎች የደንብ መተላለፍ እና የድምፅ መስጫ ቀን ይራዘም የሚሉ ጥቄዎችን አንስተዋል።

የቦርዱ ሰብሳዋ ሜላትወርቅ ኃይሉ ፓርቲዎች ቅሬታዎቻቸውን በማስረጃ አስደግፈው ቢያቀርቡ ቦርዱ ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ ለሚያደርገው ጥረት አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ሰብሳቢዋ ፓርቲዎች በቦርዱ ለሚጠየቁት መረጃ በወቅቱ መረጃውን ማቅረብ ለሥራው ቅልጥፍና ወሣኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ቦርዱ የዲጂታል አማራጮችንም በመጠቀም ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ ለማቀላጠፍ እንደሚሠራ ተገልጿል።

መረጃው ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
489
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 15:00
የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የእኩለ ቀን የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች ፦

🟢በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ስምምነት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጿል።

🟢ከአበዳሪ ተቋማትና ከአጋር አገራት ጋር ሲደረግ የቆየው የዕዳ ሽግሽግ ድርድርም በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

🟢ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

🟢ከ405 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን አሳውቋል።

🟢ለ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች የሙከራ ፈተና መሰጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስትር አስታውቋል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
614
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 14:17
ለ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች የሙከራ ፈተና መሰጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስትር አስታውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የዘንድሮውን የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በበይነ መረብ ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች የፈተና ሂደቱን ለመለማመድ በዴስክቶፕ ፣ በላፕቶፕ፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከዛሬ ግንቦት 07/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከፈተናው ቀን ድረስ መለማመድ እንደሚችሉም ተመልክቷል።

ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥርና የይለፍ ቃል በማስገባት የሙከራ ፈተናዎችን መፈተን እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤታቸው ማግኘት እንደሚችሉ የተገልጸ ሲሆን መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራሮችና ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ሂደቱን እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
1
482
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 14:08
በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ስምምነት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በህንድ በተጀመረው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ ከስብስባው ጎን ለጎን ከደቡብ አፍሪካው የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ሲሆን ሚኒስትሮቹ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት መስማማታቸው ተገልጿል።
 
ሚኒስትሩ ከዚሁ ስብሰባ ጎን ለጎን ከህንድ አቻቸው ጋር ተወያይተው የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተማምነናል ብለዋል።

የህንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከርና በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ጠቁመዋል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
452
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 14:02
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዳይኖራት በሚለው ውሳኔ መስማማታቸውን ገለፁ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቻይና ያደረጉትን የ2 ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ዛሬ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው በመመለስ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚያ ቀደም ብለው በሰጡት ቃለ መጠይቅ የቻይናው ፕሬዝዳንት ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዲኖራት ሊፈቀድላት አይገባም በሚለው ውሳኔ ተስማምተዋል ብለዋል፡፡

ትራምፕ አክለውም ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን መክፈት እንዳለባት ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ መናገራቸውን ጠቅሰው ሌሎች የሀገራቸው መሪዎች ሊፈቱት ያልቻሉትን በርካታ ችግሮች በሁለት ቀናት የቻይና ጉብኝት መፍታት መቻላቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ስለነበራቸው ንግግር ያሉት ነገር ባይኖርም የቻይና ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ቤጂንግ በኢራን ጦርነት መሰላቸቷን ገልጿል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
416
avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 13:13
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በቤተ እስራኤላዊያን ላይ የሚፈፀም የዘረኝነት ጥቃትን እንደሚያወግዙ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት ወደ እስራኤል ለመግባት ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ ቤተ እስራኤላዊያንን ለማሰብ በተዘጋጀ አንድ የመታሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በቤተ እስራኤላዊው ይማኑ ቢንያም ላይ የተፈፀመው ጥቃትን አውግዘው ገዳዮቹ በፍ/ቤት እንዲጠየቁ ጥሪ አቅርበዋል።

ቤኒያሚን ኔታናያሁ በቤተ እስራኤላዊያን ላይ የሚቃጣ ማናቸውንም ጥቃት እና መድልኦ እንደሚዋጉ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተ እስራኤላዊያንን ከመላው የእስራኤል ማህበረሰብ ጋር የማስተሳሰር ስር ውጤታማ መሆኑን ገልፀው ይሁን እንጂ አንዳንድ ያልተፈቱ ችግሮች እንዳሉ አንስተዋል። ዘገባው የኢየሩሳሌም ፖስት ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
479

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram