avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 21:03
ኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የምሽት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች

✅በ1 ሺህ 234 ወረዳዎች ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ልየታ መከናወኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።

✅በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ፣ ዕጩዎች ላይ የሚደርስ ማዋከብ፣ በታችኛው የመንግሥት መዋቅር ላይ ያሉ አስፈጻሚዎች የደንብ መተላለፍና የድምፅ መስጫ ቀን ይራዘም የሚሉት አስተያየቶች ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች እንደቀረቡለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

✅ከአበዳሪ ተቋማትና ከአጋር አገራት ጋር ሲደረግ የቆየው የዕዳ ሽግሽግ ድርድር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን እና በቀጣይ ጊዜያት መንግስት ወደ ዕዳ ክፍያ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

✅ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአማራ ክልል በደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ከ106 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ200 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
1
1 623

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram