avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
15.05.2026 16:47
ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉኝ የሚሏቸውን ቅሬታዎቻቸውን በማስረጃ አስደግፈው ማቅረብ እንደሚችሉ አስታወቀ።

ቦርዱ ይሄን ያለው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሁናዊ ሂደት ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችንና መፍትሔዎቻቸውን አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተወያየበት መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ የተሳተፉ ፓርቲዎች በተወሠኑ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ፣ ዕጩዎች ላይ የሚደርስ ማዋከብ፣ በታችኛው የመንግሥት መዋቅር ላይ ያሉ አስፈጻሚዎች የደንብ መተላለፍ እና የድምፅ መስጫ ቀን ይራዘም የሚሉ ጥቄዎችን አንስተዋል።

የቦርዱ ሰብሳዋ ሜላትወርቅ ኃይሉ ፓርቲዎች ቅሬታዎቻቸውን በማስረጃ አስደግፈው ቢያቀርቡ ቦርዱ ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ ለሚያደርገው ጥረት አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ሰብሳቢዋ ፓርቲዎች በቦርዱ ለሚጠየቁት መረጃ በወቅቱ መረጃውን ማቅረብ ለሥራው ቅልጥፍና ወሣኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ቦርዱ የዲጂታል አማራጮችንም በመጠቀም ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ ለማቀላጠፍ እንደሚሠራ ተገልጿል።

መረጃው ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
489

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram