avatar
EthioTube
@ethiotube
26.04.2026 14:22
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ ወይኖች ቀበሌ ሮቢት ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት አይቸው ገዳም ገላጋይ የተባለው የወይኖች ቀበሌ የኩፍትየ ጎጥ ነዋሪ የሆነውን የተስፋ ስዩም አስረሴን ከ20000 በላይ የሚያወጣ በግ ሰርቆ በማረድ ላይ እያለ በደረሰው የህብረተሰብ ጥቆማ እጅ ተፈንጅ መያዙን የሮቢት ከተማ ፓሊስና የቀበሌው አሰተዳደር መረጃውን ለተቋማችን አሳውቆናል። በሌባው ላይ ውሳኔ ለመስጠት መረጃው እየተጣራ ይገኛል።

ሚያዚያ 18, 2018 ዓ.ም

የላይ አርማጭሆ ወረዳ ኮምንኬሽን ጽ/ቤ

#Ethiopia #Gonder #LayArmachiho #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
2 4 1.4K
avatar
EthioTube
@ethiotube
26.04.2026 13:29
ትግስታችን - ታሪክ ራሱን ደገመ 🤩

​ኢትዮጵያዊቷ ትግስት አሰፋ የለንደን ማራቶን ክብሯን በማስጠበቅ፣ በሴቶች ብቻ ሩጫ የራሷን የዓለም ክብረ ወሰን በ2:15:41 በድጋሚ ሰብራለች 👑

​ባለፈው ዓመት እዚሁ ያስመዘገበችውን ሰዓት በ9 ሰከንድ አሻሽላዋለች 😤

​💚💛❤️

#TigistAssefa #Athletics #LondonMarathon #Ethiopia #Sport
1.6K
avatar
EthioTube
@ethiotube
25.04.2026 18:37
መድፈኞቹ ወደ መሪነታቸው ተመለሱ

አርሰናል 1-0 ኒውካስል

የአርሰናል ወይስ የሲቲ? ዋንጫው የማን ነው?

#PremierLeague #Arsenal #ManchesterCity
1.6K
avatar
EthioTube
@ethiotube
25.04.2026 16:46
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ብልፅግና ፓርቲን በይፋ መቀላቀላቸውን አስታወቁ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገዢውን ብልፅግና ፓርቲ በይፋ ተቀላቅለዋል።

ዳንኤል 2013 ዓ.ም. በተደረገው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በግል ተወዳድረው ፓርላማ መግባታቸው ይታወሳል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ጥያቄ የቀረበላቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ

“ለሌሎች ዕድል ለመስጠት" ሲሉ በምርጫው ላለመሳተፍ አቅደው እንደነበር ተናግረዋል። ሆኖም ግን "አሁን ሌሎች ዕድል ማግኘታቸውን ስላረጋገጥኩ የብልጽግና ዕጩ ሆኜ ልወዳደር ነው” ሲሉ ዲያቆን ዳንኤል ለ“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

የብልጽግና ፓርቲን ከመቼ ጀምሮ እንደተቀላቀሉ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም መልስ ከመስጠት መቆጠባቸው ተገልጿል።

#Ethiopia #ProsperityParty #DanielKibret #EthiopianElection #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
2 1.6K
avatar
EthioTube
@ethiotube
25.04.2026 02:45
🔔 በዲሲ እና አካባቢዋ የምትገኙ እንዳያመልጣችሁ! 🔔

Your Ethiopian Professionals Network - YEP 15 አመት ሞላው!
ቅዳሜ በፎልስ ቸርች፣ ቨርጂኒ ይከበራል!

ተጋባዥ እንግዶች፦
👉 ዶ/ር ገቢሳ ኤጄታ
👉 ዲናው መንግስቱ
👉 ዶ/ር ሎዛ ታደሰ
👉 ኮሜዲያን ቢኒያም ብዙነህ
👉 ዶ/ር እናውጋው መሓሪ
👉 ዶ/ር ኤባ ት

ዛሬውኑ ትኬት ይግዙ!
onecau.se/yep15yeargala  ​

#Ethiopia​ #EthiopianProfessionals​ #YEP15​

#ማስታወቂያ | #Ad
42
avatar
EthioTube
@ethiotube
24.04.2026 19:17
የአርቲስት ቴዲ አፍሮ ስቱዲዮ በታጠቁ አካላት ተዘረፈ

"ቴዲ አፍሮ እስካሁን በደኅና ሁኔታ ላይ ይገኛል" ተብሏል

የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ስቱዲዮ በታጠቁ አካላት መዘረፉን የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ዘግቧል።

ዘረፋው የተፈፀመው ትላንት ሚያዚያ15/2018
ዓ.ም. ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኘው የአርቲስቱ ስቱዲዮ ውስጥ ነው።

መሣሪያ የታጠቁ እና በተሽከርካሪ የመጡ አካላት የስቱዲዮን ጠባቂዎች በመደብደብ አርቲስቱ ለሙዚቃ ሥራው የሚጠቀምባቸውን ንብረቶች መውሰዳቸውን ዘገባው አመልክቷል።

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን «ኢቶሪካ» የተሰኘው የሙዚቃ አልበሙ ከመውጣቱ በፊት ጀምሮ የሥነልቡና ጫና ሊያደርሱ የሚችሉ ወከባዎች በአካባቢው እየተፈጸሙ ቢሆንም፣ እንቅስቃሴው ቢገታም እስካሁን በደኅና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ዶቼ ቬለ ከምንጮቼ አገኘሁት ባለው መረጃ ገልጿል።

ቴዲ አዲሱን አልበም ለአድማጮች ካደረሰ በኋላ የቅርብ ወዳጁ እንዲሁም ቃልአቀባዩ እና ምክትል ማናጀሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

#Ethiopia #EthiopianMusic #TeddyAfro #AddisAbaba #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
2 1 588
avatar
EthioTube
@ethiotube
23.04.2026 09:21
በሕገ ወጦች ተይዘናል በማለት ከቤተሰቦቻቸው 300 ሺህ ብር ለማስላክ የሞከሩ ታዳጊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሕገ ወጦች ተይዘናል በማለት ቤተሰቦቻቸው 300 ሺህ ብር እንዲልኩላቸው የጠየቁ ታዳጊዎች ከእነ ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ

ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው የካ አባዶ አካባቢ ነው፡፡

የ15 እና የ16 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት ታዳጊዎቹ ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ/ም ለትምህርት ብለው እንደወጡ ሳይመለሱ እንደቀሩ ፖሊስ ገልጿል።

በልጆቹ መጥፋት ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀው በነበሩበት ወቅት ታዳጊዎቹ ስልክ በመደወል 300 ሺህ ብር ካልተላከላቸው የያዟቸው ግለሰቦች ጉዳት ሊያደርሱባቸው መሆኑን እንደተናገሩ ተመላክቷል

የወንጀሉ ጉዳይ ሪፖርት የደረሰው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል እና ፍለጋ ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ታዳጊዎቹን ከሁለት ወንዶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ታዳጊዎቹ ከሁለት ወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ እንደነበር ያረጋገጠ ሲሆን አራቱን ታዳጊዎች እና ለታዳጊዎቹ የመኝታ ክፍል ያከራየን ግለሰብ ይዞ ምርመራው መቀጠሉን ገልጿል፡፡

ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ አስበው እና ተነጋግረው ድርጊቱን አቀነባብረው እንደፈፀሙት ታዳጊዎቹ ለፖሊስ ከሰጡት ቃል መረዳት ተችሏል፡፡

ሆቴል ቤቶች ሆኑ የመኝታ ክፍል የሚያከራዩ ተቋማት ለህፃናት ሆነ ለታዳጊዎች የመኝታ ክፍል ማከራየትና አልኮል መጠጥ መሸጥ እንደሌለባቸው ፖሊስ አሳስቧል።

ቤተሰብም ልጆቻቸው የት እና ከእነ ማን ጋር እንደሚውሉ የማረጋገጥ ልምድ ሊያደብር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

#Ethiopia #AddisAbaba
1 2 986
avatar
EthioTube
@ethiotube
22.04.2026 09:21
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቴዲ አፍሮን ጠንከር ባለ ቃላት ከወቀሱት በኋላ የአርቲስቱ ባልደረባዎች መታሰራቸው ተሰምቷል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው እሁድ ቴዲ አፍሮን በቁራ መስለው “ቁራ የቆሸሸ ቦታ የሚውል በመጮኽ በማልቀስ አካባቢን የሚበክል ነው” በማለት ጠንከር ባለ ቃላት ከወቀሱት በኋላ የአርቲስቱ ሁለት ባልደረባዎች መታሰራቸው ተሰምቷል።

የቴዲ አፍሮ ምክትል ማናጀርና ቃል አቀባይ ማህሌት ሰለሞን እንዲሁም የቅርብ ወዳጁ ነው የሚባለው የሱፍ ያሲን በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

ትላንትት ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር የዋሉትን የአርቲስቱን ባልደረቦች አስመልክቶ እስካሁን ድረስ የፌደራል ፓሊስ ሆነ የአዲስ አበባ ፓሊስ ያወጡት ይፋዊ መግለጫ የለም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኦሮሚያ ክልል የተገነባውን ሐሮ ደንዲ ሎጅ ባስመረቁበት ዕለት "እኛ ንስር ነን ቁራ አይደለንም" ሲሉ አርቲስት ቴዲ አፍሮን መተቸታቸው ይታወሳል። ይህን ንግግራቸውን ተከትሎ የአርቲስቱ አድናቂዎች ከፍተኛ ስጋታቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል።

#Ethiopia #TeddyAfro #AbiyAhmed #EthiopianMusic #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
8 5 1.2K
avatar
EthioTube
@ethiotube
22.04.2026 01:16
ህወሓት ከስድስት ዓመት በፊት በተካሔደው ምርጫ የተመረጠውን ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ የወሰነውን ውሳኔ ጄነራል ታደሠ ወረደ ተቃወሙት

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግራይ ክልል በ 2012 ዓ.ም. በተካሔደው ምርጫ የተመረጠውን የክልሉን ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ የወሰነውን ውሳኔ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሠ ወረደ ተቃወሙት።

ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከጦርነቱ በፊት የነበረው መንግስት ወደ ቦታው እንዲመለስ ያስተላለፈው ውሳኔ “የፕሪቶሪያውን ስምምነት ውድቅ የሚያደርግ ነው” በማለት ተችተውታል።

ጄነራል ታደሠ በመግለጫቸው “በትግራይ ውስጥ በአሉባልታ የሚመጣ መፍትሔ የለም” ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባሰራጨው መረጃ አሳውቋል። የፌደራል መንግሥት የታደሠ ወረደን የሥልጣን ዘመን ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ማድረጉ በህወሓት ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።

ህወሓት ይህን ውሳኔ “እኔን ያላካተተ የተናጠል ውሳኔ ነው” ሲል የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን መራዘም እንደማይቀበለው መግለጹ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ከስድስት ዓመት በፊት በተደረገ ምርጫ የተመረጠን ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ ወስኗል። በ2012 ዓ.ም. የተካሔደው ምርጫ በክልሉ ለተከሰተው ጦርነት አንድ መንስዔ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል።

የዛሬው የጄኔራል ታደሠ መግለጫ የሚመሩት ካቤኔ እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በመደበኛ ሥራቸው እንደሚቀጥሉ በማሳወቅ የህወሓት ውሳኔ ተፈፃሚ እንደማይሆን ያመላከተ ሆኗል።

#Ethiopia #Tigray #TPLF #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1.2K
avatar
EthioTube
@ethiotube
20.04.2026 20:51
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የእንጨት አካፋይ ወድቆ ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ገለፁ

አምባሳደር ሬድዋን፤ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የኮፕ32 ዓለም አቀፍ ስብሰባ በሚመለከት ‎ብሔራዊ ኮሚቴው ከሰሞኑ ባካሔደው ውይይት ላይ ሲካፈሉ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ሬድዋን ከግንባራቸው ከፍ ብሎ ጭንቅላታቸው ላይ የሚታይ ጠባሳን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ አስተያየቶች ሲሰጡ ቆይቷል።

አምባሳደሩ ስላጋጠማቸው ክስተት በፌስቡክ ገፃቸው በሰጡት ማብራሪያ "ከሁለት ሳምንት በፊት በሀገራዊ ጉዳይ የሚመክር ስብሰባ አስተናግደን ለምሳ እንዳረፍን ንፋስ ለመከላከል የተጋረደ የእንጨት አካፋይ
( Partition Wall ) ሚዛን ስቶ ሲወድቅ አናቴ ጋርና ትንሽ ገባ ብሎ አገኘኝ" ብለዋል። በዚህ አደጋ ጭንቅላታቸው ላይ መሰንጠቅ እንዳጋጠመ ተናግረዋል።

"ስንጥቁ መሰፋት ስለነበረበት ሐኪሞች በከፊል[ፀጉሬን] ላጩት። እኔ ደሞ ሙሉውን ቢሆን ይሻላል ብዬ እስከሚደርቅ አነሳሁት። እንደልጅነቴ ተመልጬ ሳየው አልጠላሁትም" በማለት መነጋገሪያ ስለነበረው ገፅታቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሬድዋን፤ ሕክምናቸውን እዚሁ አዲስ አበባ በሚገኝ አሚን ሆስፒታል መከታተላቸውን ገልፀው ወደ ውጭ ሀገር አልወጣሁም" ሲሉ አስታውቀዋል።

#Ethiopia #RedwanHussain #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1.4K
avatar
EthioTube
@ethiotube
19.04.2026 22:38
የአርሰናል የዋንጫ እድል አበቃለት?

#PremierLeague #Arsenal #ManchesterCity #EPL #Football
1.4K
avatar
EthioTube
@ethiotube
19.04.2026 17:57
“እኛ ንስር ነን ቁራ አይደለንም፤ ቁራ የቆሸሸ ቦታ የሚውል በመጮኽ በማልቀስ አካባቢን የሚበክል የአዋፍ ዝርያ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

“ጩኸቱን፣ ለቅሶውን ለቁራዎች እንተወዋለን”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “እኛ ንስር እንጂ ቁራ አይደለንም” ሲሉ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሁለቱ የአዕዋፋት ዝርያ ሲያብራሩ፤ “ቁራ የቆሸሸ ቦታ የሚውል በመጮኽ በማልቀስ አካባቢን የሚበክል የአዋፍ ዝርያ ነው” ብለዋል።

ይህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት የተሰማው፤ በዚህ ሳምንት የተለቀቀው የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ዐዲሱ “ኢቶሪካ” አልበም በበርካታ ሰዎች ዘንድ እየተደመጠና መነጋገሪያ በሆነበት ወቅት ነው። 18 ሙዚቃዎችን የያዘው የቴዲ በተለቀቁ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር እይታን ማግኘት ችለዋል።

ዐቢይ በኦሮሚያ ክልል የተገነባውን በሐሮ ደንዲ ሎጅ በዛሬው እለት ሲያስመርቁ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሀገሪቱ እየተገነቡ ያሉት የልማት ሥራዎች “ለማራከስ እንደሚሞከረው አይደለም” ብለዋል።

የዓለም ባንክ እና አይ. ኤም. ኤፍ (IMF) በዛሬው ዕለት በዋሽንግተን እያደረጉት ያለውን ዓመታዊ ስብሰባን በመጥቀስ፤ በዚህ ዓመት “በአፍሪካ ውስጥ ቁጥር አንድ ከፍተኛ እድገት ያላት ኢትዮጵያ ናት” ሲሉ ተቋማቱ መናገራቸውን ገልጸዋል።

ዐቢይ አክለውም “እኛ እንደንስር ወደ ከፍታ ነው የምንበረው ብለዋል። “ንስር በባሕሪው አርቆ የሚያይ፣ብዙ ከለሮች የሚያይ በከፍታ የሚበር፣በከፍታ የሚመላለስ፣ በከፍተኛ ርቀት ዐይቶ፣ አልሞ፣አድኖ መብላት የሚችል የብዙ ጀግንነት የብዙ ብቃት መለኪያ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

#Ethiopia #AbiyAhmed #TeddyAfro
5 5 1.6K
avatar
EthioTube
@ethiotube
19.04.2026 02:16
ቀያይ ሰይጣኖቹ በቸልሲ ሜዳ ድል ቀናቸው

ቸልሲ 0-1 ማንችስተር ዩናይትድ

ዘንድሮ ዩናይትድ ስንተኛ ደረጃ ይጨርሳል?

#PremierLeague #ManchesterUnited #Chelsea #EPL #Football
1 1.3K
avatar
EthioTube
@ethiotube
19.04.2026 00:33
የመንግሥት ሠራተኞች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ጋምቤላ ከተማ ከንቲባ አሳሰቡ

በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችና ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ቱት ጆክ አሳስበዋል። ከንቲባው በቀጣይ ለሚካሄደው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ “ይበጀናል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ከወዲሁ የምርጫ ካርዳቸውን እንዲወስዱ” ማሳሰቢያ መስጠታቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መዘገቡን ተመልክተናል።

ምርጫ ቦርድ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ “በመራጭነት መመዝገብን እንደግዴታ የሚያደርግ ተጽዕኖ አጥብቆ እንደሚቃወም” መግለጹ አይዘነጋም። ቦርዱ ይህንን ቢልም የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ግን የመንግሥት ሠራተኞች እና ነዋሪዎች ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ማሳሰቢያቸውን አስተላልፈዋል።

ምርጫ ቦርድ “በዚህ የቅድመ ምርጫ ወቅት ቤት ለቤት በመዘዋወር ካርድ ውሰዱ የሚል ሕግን የሚተላለፍ ተግባር” እየተፈጸመ መሆን መናገሩ አይዘነጋም። ቦርዱ አክሎም “መራጭነትን ከማኀበራዊ አገልግሎት ጋር ማገናኘት እና ከደመወዝ መቁረጥ ጋር በማያያዝ በዜጎች ላይ ተጽዕኖ እየደረሰ ነው” በማለት ድርጊቱን ተችቷል።

የኢፌድሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 38 በምርጫ መሳተፍ መብት እንጂ ግዴታ አለመሆኑን ይገልፃል። አንቀጹ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ “በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በየጊዜው በሚካሔድ ምርጫ የመምረጥ እና የመመረጥ” መብት አለው ሲል ይደነግጋል።

#Ethiopia #Gambella #EthiopianElection #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1 1.5K
avatar
EthioTube
@ethiotube
16.04.2026 23:29
ሀገራዊ ጉዳዮችን የሚያነሳውና 9 አመታት የተጠበቀው አዲሱ የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አልበም

"ኢቶሪካ" የተሰኘው የቴዲ አልበም 18 ሙዚቃዎችን በውስጡ አካትቷል። አልበሙ በተለቀቀ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ "ጀንበር" የተሰኘው ዘፈኑ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ እይታን ማግኘት ችሏል።

ቴዲ በሙዚቃዎቹ እንደተለመደው ኢትዮጵያዊነትን አቀንቅኗል፤ አንድነትን ከፍ የሚያደርግ ደማቅ መልዕክቱንም አስተላልፏል።

ቴዲ አፍሮ በአዲሱ አልበም፤ ከሌላው የሙዚቃ ሥራዎቹ በተለየ መልኩ በማንነታቸው ምክንያት በግፍ ለተገደሉ ዜጎች መታሰቢያ ያደረገ ሙዚቃ አቅርቧል።

ይህ "የአዞ እምባ" የተሰኘ መጠሪያ የሰጠው ሙዚቃው፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በማንነታቸው ብቻ ተለይተው በግፍ ለተገደሉ ንፁሃን ወገኖች እና ከቄያቸው ለተፈናቀሉ ፣ የአካልና የሥነልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን መታሰቢያነት ይሁንልኝ ብሏል።

"ዳስ ጣል (አንሳው)" በሚለው ሌላኛው ዘፈኑ ደግሞ:

"በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር
መሃል ገቡና አቆሙን ከዳር"

ሲል የሀገሪቱን ፓለቲካ እና የፓለቲከኞች አካሔድ ታዝቧል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞቿ ዋጋ ከፍለው ለትውልድ ያሻገሯት መሆኗን በዚህኛው ዘፈኑ ገልጿል።

ይሁንና ይቺን ሀገር ተረክበን፣ በብሔር ተከፋፍለን ስለምን ኢትዮጵያዊነት ወደ ዳር እንገፋዋለን ? ሲል እንዲህ ይጠይቃል:

"ባቆዩት ሀገር ጀግኖች በአንድነት በአርበኝነት
እንዴት ይገፋ ኢትዮጵያዊነት"

በተመሳሳይ መልኩ "ስምምነን" በተሰኘው የጉራጊኛ ሙዚቃው:

"ተበትነን ብናይ ረብ የለን እንደብናኝ" ይለናል ቴዲ መከፋፈል ልክ እንደ ብናኝ የሚያሳንስ መሆኑን ለማመልከት።

"ይሆናል ወይ እቃ ድስት ያለክዳን"
እኛስ አለን እንዴ ሀገር ከሌለን"
እንዴት ስለለየን ፍረደ ገምድል ዳኛ
ዓባይ እየሞላ እንጎላለን እኛ" ብሏል
6 1 1.6K
avatar
EthioTube
@ethiotube
16.04.2026 03:14
ትናንት እና ዛሬ በተካሄዱ ጨዋታዎች ፒኤስጂ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ባየርን ሙኒክ እና አርሰናል ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ዘንድሮ ዋንጫው የማን ነው?

#UCL #ChampionsLeague #Football #BayernMunich #Arsenal #PSG #SportingCP
1.8K

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram