avatar
EthioTube
@ethiotube
22.04.2026 01:16
ህወሓት ከስድስት ዓመት በፊት በተካሔደው ምርጫ የተመረጠውን ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ የወሰነውን ውሳኔ ጄነራል ታደሠ ወረደ ተቃወሙት

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግራይ ክልል በ 2012 ዓ.ም. በተካሔደው ምርጫ የተመረጠውን የክልሉን ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ የወሰነውን ውሳኔ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሠ ወረደ ተቃወሙት።

ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከጦርነቱ በፊት የነበረው መንግስት ወደ ቦታው እንዲመለስ ያስተላለፈው ውሳኔ “የፕሪቶሪያውን ስምምነት ውድቅ የሚያደርግ ነው” በማለት ተችተውታል።

ጄነራል ታደሠ በመግለጫቸው “በትግራይ ውስጥ በአሉባልታ የሚመጣ መፍትሔ የለም” ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባሰራጨው መረጃ አሳውቋል። የፌደራል መንግሥት የታደሠ ወረደን የሥልጣን ዘመን ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ማድረጉ በህወሓት ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።

ህወሓት ይህን ውሳኔ “እኔን ያላካተተ የተናጠል ውሳኔ ነው” ሲል የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን መራዘም እንደማይቀበለው መግለጹ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ከስድስት ዓመት በፊት በተደረገ ምርጫ የተመረጠን ምክር ቤት ወደ ሥራ እንዲመለስ ወስኗል። በ2012 ዓ.ም. የተካሔደው ምርጫ በክልሉ ለተከሰተው ጦርነት አንድ መንስዔ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል።

የዛሬው የጄኔራል ታደሠ መግለጫ የሚመሩት ካቤኔ እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በመደበኛ ሥራቸው እንደሚቀጥሉ በማሳወቅ የህወሓት ውሳኔ ተፈፃሚ እንደማይሆን ያመላከተ ሆኗል።

#Ethiopia #Tigray #TPLF #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1.2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram