avatar
EthioTube
@ethiotube
19.04.2026 00:33
የመንግሥት ሠራተኞች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ጋምቤላ ከተማ ከንቲባ አሳሰቡ

በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችና ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ ቱት ጆክ አሳስበዋል። ከንቲባው በቀጣይ ለሚካሄደው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ “ይበጀናል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ከወዲሁ የምርጫ ካርዳቸውን እንዲወስዱ” ማሳሰቢያ መስጠታቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መዘገቡን ተመልክተናል።

ምርጫ ቦርድ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ “በመራጭነት መመዝገብን እንደግዴታ የሚያደርግ ተጽዕኖ አጥብቆ እንደሚቃወም” መግለጹ አይዘነጋም። ቦርዱ ይህንን ቢልም የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ግን የመንግሥት ሠራተኞች እና ነዋሪዎች ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ማሳሰቢያቸውን አስተላልፈዋል።

ምርጫ ቦርድ “በዚህ የቅድመ ምርጫ ወቅት ቤት ለቤት በመዘዋወር ካርድ ውሰዱ የሚል ሕግን የሚተላለፍ ተግባር” እየተፈጸመ መሆን መናገሩ አይዘነጋም። ቦርዱ አክሎም “መራጭነትን ከማኀበራዊ አገልግሎት ጋር ማገናኘት እና ከደመወዝ መቁረጥ ጋር በማያያዝ በዜጎች ላይ ተጽዕኖ እየደረሰ ነው” በማለት ድርጊቱን ተችቷል።

የኢፌድሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 38 በምርጫ መሳተፍ መብት እንጂ ግዴታ አለመሆኑን ይገልፃል። አንቀጹ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ “በማናቸውም የመንግሥት ደረጃ በየጊዜው በሚካሔድ ምርጫ የመምረጥ እና የመመረጥ” መብት አለው ሲል ይደነግጋል።

#Ethiopia #Gambella #EthiopianElection #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1 1.5K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram