avatar
EthioTube
@ethiotube
19.04.2026 17:57
“እኛ ንስር ነን ቁራ አይደለንም፤ ቁራ የቆሸሸ ቦታ የሚውል በመጮኽ በማልቀስ አካባቢን የሚበክል የአዋፍ ዝርያ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

“ጩኸቱን፣ ለቅሶውን ለቁራዎች እንተወዋለን”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “እኛ ንስር እንጂ ቁራ አይደለንም” ሲሉ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሁለቱ የአዕዋፋት ዝርያ ሲያብራሩ፤ “ቁራ የቆሸሸ ቦታ የሚውል በመጮኽ በማልቀስ አካባቢን የሚበክል የአዋፍ ዝርያ ነው” ብለዋል።

ይህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት የተሰማው፤ በዚህ ሳምንት የተለቀቀው የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ዐዲሱ “ኢቶሪካ” አልበም በበርካታ ሰዎች ዘንድ እየተደመጠና መነጋገሪያ በሆነበት ወቅት ነው። 18 ሙዚቃዎችን የያዘው የቴዲ በተለቀቁ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር እይታን ማግኘት ችለዋል።

ዐቢይ በኦሮሚያ ክልል የተገነባውን በሐሮ ደንዲ ሎጅ በዛሬው እለት ሲያስመርቁ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሀገሪቱ እየተገነቡ ያሉት የልማት ሥራዎች “ለማራከስ እንደሚሞከረው አይደለም” ብለዋል።

የዓለም ባንክ እና አይ. ኤም. ኤፍ (IMF) በዛሬው ዕለት በዋሽንግተን እያደረጉት ያለውን ዓመታዊ ስብሰባን በመጥቀስ፤ በዚህ ዓመት “በአፍሪካ ውስጥ ቁጥር አንድ ከፍተኛ እድገት ያላት ኢትዮጵያ ናት” ሲሉ ተቋማቱ መናገራቸውን ገልጸዋል።

ዐቢይ አክለውም “እኛ እንደንስር ወደ ከፍታ ነው የምንበረው ብለዋል። “ንስር በባሕሪው አርቆ የሚያይ፣ብዙ ከለሮች የሚያይ በከፍታ የሚበር፣በከፍታ የሚመላለስ፣ በከፍተኛ ርቀት ዐይቶ፣ አልሞ፣አድኖ መብላት የሚችል የብዙ ጀግንነት የብዙ ብቃት መለኪያ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

#Ethiopia #AbiyAhmed #TeddyAfro
5 5 1.6K

Обсуждение 5

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram