avatar
EthioTube
@ethiotube
23.04.2026 09:21
በሕገ ወጦች ተይዘናል በማለት ከቤተሰቦቻቸው 300 ሺህ ብር ለማስላክ የሞከሩ ታዳጊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሕገ ወጦች ተይዘናል በማለት ቤተሰቦቻቸው 300 ሺህ ብር እንዲልኩላቸው የጠየቁ ታዳጊዎች ከእነ ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ

ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው የካ አባዶ አካባቢ ነው፡፡

የ15 እና የ16 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት ታዳጊዎቹ ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ/ም ለትምህርት ብለው እንደወጡ ሳይመለሱ እንደቀሩ ፖሊስ ገልጿል።

በልጆቹ መጥፋት ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀው በነበሩበት ወቅት ታዳጊዎቹ ስልክ በመደወል 300 ሺህ ብር ካልተላከላቸው የያዟቸው ግለሰቦች ጉዳት ሊያደርሱባቸው መሆኑን እንደተናገሩ ተመላክቷል

የወንጀሉ ጉዳይ ሪፖርት የደረሰው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል እና ፍለጋ ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ታዳጊዎቹን ከሁለት ወንዶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ታዳጊዎቹ ከሁለት ወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ እንደነበር ያረጋገጠ ሲሆን አራቱን ታዳጊዎች እና ለታዳጊዎቹ የመኝታ ክፍል ያከራየን ግለሰብ ይዞ ምርመራው መቀጠሉን ገልጿል፡፡

ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ አስበው እና ተነጋግረው ድርጊቱን አቀነባብረው እንደፈፀሙት ታዳጊዎቹ ለፖሊስ ከሰጡት ቃል መረዳት ተችሏል፡፡

ሆቴል ቤቶች ሆኑ የመኝታ ክፍል የሚያከራዩ ተቋማት ለህፃናት ሆነ ለታዳጊዎች የመኝታ ክፍል ማከራየትና አልኮል መጠጥ መሸጥ እንደሌለባቸው ፖሊስ አሳስቧል።

ቤተሰብም ልጆቻቸው የት እና ከእነ ማን ጋር እንደሚውሉ የማረጋገጥ ልምድ ሊያደብር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

#Ethiopia #AddisAbaba
1 2 986

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram