avatar
EthioTube
@ethiotube
16.04.2026 23:29
ሀገራዊ ጉዳዮችን የሚያነሳውና 9 አመታት የተጠበቀው አዲሱ የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አልበም

"ኢቶሪካ" የተሰኘው የቴዲ አልበም 18 ሙዚቃዎችን በውስጡ አካትቷል። አልበሙ በተለቀቀ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ "ጀንበር" የተሰኘው ዘፈኑ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ እይታን ማግኘት ችሏል።

ቴዲ በሙዚቃዎቹ እንደተለመደው ኢትዮጵያዊነትን አቀንቅኗል፤ አንድነትን ከፍ የሚያደርግ ደማቅ መልዕክቱንም አስተላልፏል።

ቴዲ አፍሮ በአዲሱ አልበም፤ ከሌላው የሙዚቃ ሥራዎቹ በተለየ መልኩ በማንነታቸው ምክንያት በግፍ ለተገደሉ ዜጎች መታሰቢያ ያደረገ ሙዚቃ አቅርቧል።

ይህ "የአዞ እምባ" የተሰኘ መጠሪያ የሰጠው ሙዚቃው፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በማንነታቸው ብቻ ተለይተው በግፍ ለተገደሉ ንፁሃን ወገኖች እና ከቄያቸው ለተፈናቀሉ ፣ የአካልና የሥነልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን መታሰቢያነት ይሁንልኝ ብሏል።

"ዳስ ጣል (አንሳው)" በሚለው ሌላኛው ዘፈኑ ደግሞ:

"በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር
መሃል ገቡና አቆሙን ከዳር"

ሲል የሀገሪቱን ፓለቲካ እና የፓለቲከኞች አካሔድ ታዝቧል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞቿ ዋጋ ከፍለው ለትውልድ ያሻገሯት መሆኗን በዚህኛው ዘፈኑ ገልጿል።

ይሁንና ይቺን ሀገር ተረክበን፣ በብሔር ተከፋፍለን ስለምን ኢትዮጵያዊነት ወደ ዳር እንገፋዋለን ? ሲል እንዲህ ይጠይቃል:

"ባቆዩት ሀገር ጀግኖች በአንድነት በአርበኝነት
እንዴት ይገፋ ኢትዮጵያዊነት"

በተመሳሳይ መልኩ "ስምምነን" በተሰኘው የጉራጊኛ ሙዚቃው:

"ተበትነን ብናይ ረብ የለን እንደብናኝ" ይለናል ቴዲ መከፋፈል ልክ እንደ ብናኝ የሚያሳንስ መሆኑን ለማመልከት።

"ይሆናል ወይ እቃ ድስት ያለክዳን"
እኛስ አለን እንዴ ሀገር ከሌለን"
እንዴት ስለለየን ፍረደ ገምድል ዳኛ
ዓባይ እየሞላ እንጎላለን እኛ" ብሏል
6 1 1.6K

Обсуждение 6

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram