avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
12.04.2026 16:08
እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
👍 14
👏 4
🙏 3
1 2.1K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
10.04.2026 15:35
#FakeAccountAlert በኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ሚስጥረስላሴ ታምራት ስም ከተከፈቱ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች እንጠንቀቅ

/ኢትዮጵያ ቼክ/- የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዋና ጸሐፊ የሆኑትን ሚስጥረስላሴ ታምራትን ስም እና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች የተለያዩ መረጃዎችን እያጋሩ መሆናቸዉን ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ ባደረገዉ ማጣራት በርከት ያሉ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች በዋና ጸሐፊዋ ስም መከፈታቸዉን አረጋግጧል።

በሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንቶቹ ከተጋሩ መረጃዎች መካከል 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተገናኘ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ ንግግሮች ይገኙበታል።

ዋና ጸሐፊዋ ከቀናት በፊት በትክክለኛ የፌስቡክ አካውንታቸው ባጋሩት ጽሁፍ “በስሜ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተከፈቱና እኔን የማይገልጹ ጽሁፎች እንዲሁም ፎቶዎች ተቀናብረው እየተለቀቁባቸው መሆኑን ተመልክቻለሁ” ብለዋል።

በተጨማሪም ትክክለኛ አካውንታቸዉ ከ55 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ይህ አካውንት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል፡ https://www.facebook*.com/share/17f9UcAsUC/?mibextid=wwXIfr 

የታዋቂ ግለሰቦችን እና ተቋማትን ስም እና ምስል (አርማ) በመጠቀም የሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና አካዉንቶች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ተገቢዉን ጥንቃቄ እናድርግ።

በተጨማሪም ሀሰተኛ እና ተመሳስለዉ የሚከፈቱ አካውንቶችን፣ ገጾችን እና ቻነሎችን ለመለየት የሚረዱን ጠቋሚ ምልክቶችን ለማየት ይህን በኢትዮጵያ ቼክ የተዘጋጀን አጭር ቪድዮ ይመልከቱ፡ @ethiopiacheck1344

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
18
👍 5
3.7K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
02.04.2026 22:52
#EthiopiaCheck 'መረጃን ከማጋራትዎ በፊት ያስተዉሉ'- ዛሬ እየተከበረ ከሚገኘዉ ዓለም አቀፍ መረጃ ማጣራት ቀን ጀርባ ያለ መልዕክት

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በዛሬዉ እለት ዓለም አቀፍ የመረጃ ማጣራት ቀን (International Fact-Checking Day) በመላዉ አለም እየተከበረ ይገኛል።

ይህ በየዓመቱ እኤአ ሚያዚያ 2 (April 2) የሚከበረዉ ቀን መረጃ አጣሪዎች የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመዋጋት ረገድ ለሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ታስቦ ከ10 ዓመታት በፊት እኤአ በ2016 በየአመቱ እንዲከበር በተወሰነው መሰረት ነበር።

ከዛ ወዲህም በየአመቱ የመረጃ ማጣራትን አስፈላጊነት ግንዛቤን የሚያሳድጉ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ሲከበር ቆይቷል።

ይህ ቀን በሀገራችን ከፍተኛ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት በሚታይበት በተለይ ሰው-ሰራሽ አስተውሎት የሚፈበረኩ ይዘቶች በርካቶችን ለተሳሳተ ግንዛቤ ሲዳርጉ በሚታይበት ወቅትም እየተከበረ ይገኛል።

ስለዚህም ቀኑ መረጃ ማጣራት ክህሎት ለሀገራችን ዜጎች ከመችዉም ጊዜ በላይ አስፈላጊ በሆነበት ወቅት እየተከበረ እንደሚገኝ ልብ ልንለው ይገባል።

በሀገራችን ዉስን መረጃ አጣሪዎች ሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎችን በማጋለጥ ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃን እንዲያገኝ ዉስን እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ ይስተዋላል።

ይሁን እንጂ ሀሰተኛ መረጃን መዋጋት እና ስርጭቱን መግታት ለመረጃ አጣሪዎች ብቻ የሚተዉ ተግባር አይደለም። ሁላችንም ሀሰተኛ መረጃዎችን ከማጋራት በመቆጠብ እንዲሁም የተሰራጩትን በማጋለጥ ሀላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል።

በተጨማሪም የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎትን በማዳበር ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ያለንን ተጋላጭነት መቀነስም ያስፈልጋል።

ይህ ከሆነ የመረጃ ምህዳሩ ጤነኛ እንዲሁም ትክክለኛ መረጃዎች ጎልተዉ የሚታዩበት ይሆናል። ንቁ እና ስለ ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብ እንዲፈጠርም አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ስለዚህ ዛሬ እየተከበረ የሚገኘዉን ዓለም አቀፍ መረጃ ማጣራት ቀን በምናከብርበት ወቅት እነዚህን ነጥቦች ልብ እንበል፡
-ተአማኒ ባልሆኑ የመረጃ ምንጮች የሚጋሩ መረጃዎችን ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ቆም ብለን እናስብ
-የመረጃ ምንጩን ተአማኒነት እናረጋግጥ
-መረጃዉ በማስረጃ የተደገፈ መሆኑን እንመርምር
-መረጃዉ በሌሎች የመረጃ ምንጮች በተለይም ተአማኒ በሆኑ ምንጮች መሰራጨቱን እናረጋግጥ
-የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የራሳችንን አስተዋጽኦ እናድርግ

ኢትዮጵያ ቼክ!

@EthiopiaCheck
25
👍 5
🔥 3
6 6.6K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
28.03.2026 02:47
#FactCheck በኤርትራ ሀይሎች ተመትቶ የወደቀን የኢትዮጵያ ድሮን ያሳያል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው ምስል በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረከ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በርከት ያሉ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች 'ኤርትራ የኢትዮጵያን ድሮን አፋር ክልል አካባቢ መትታ ጣለች' የሚል መረጃ እያጋሩ ይገኛሉ።

አካውንቶቹ እና ገጾቹ መረጃዉን በሰበር መልኩ እያሰራጩ የሚገኙ ሲሆን ተመቶ ወደቀ የተባለውን ድሮን ያሳያል ያሉትን ምስልም እያጋሩ ይገኛሉ።

ይህን በጽሁፍ እና ምስል የተደገፈ መረጃ ካጋሩ ገጾች መካከል 'Esmael Dawed Endrise' የሚል ስም እና ከ68 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እንዲሁም የትክክለኛ የፌስቡክ ገጽነት ማረጋገጫ (verification) ያለው ይገኝበታል።

ገጹ ከምስሉ በተጨማሪ "በኢትዮ ኤርትራ በአፋር አካባቢ ባለ ድንበር Bayraktar TB2.የተሰኘ የበረራ ቁጥሩ AZf 131 የሆነ ቱርክ ሰራሽ ባይራክተር የሚባል ድሮን ዛሬ ወደ ማምሻዉ ላይ መትታ ጥላለች ተባለ" የሚል መልዕክትም በልጥፉ አስፍሯል።

በዚህ ገጽ የተጋራዉን መረጃም ከ70 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰዉ አጋርተዉታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገዉ ማጣራት ምስሉ በኤርትራ ተመቶ የወደቀን የኢትዮጵያን ድሮን እንደማያሳይ አረጋግጧል።

የምስሉን ትክክለኛነት ለማጣራት 'SynthID Detector' የተሰኘዉን የጉግል ድረ-ገጽ የተጠቀምን ሲሆን ምስሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረከ እንደሆነ አረጋግጠናል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚፈበረኩ መሰል ምስሎች ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ በስፋት እየታየ ሲሆን በርካታ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎችን ለተሳሳተ ግንዛቤ ሲያጋልጡም ይታያል።

በመሆኑም ተአማኒ ባልሆኑ የመረጃ ምንጮች የሚሰራጩ አጠራጣሪ መረጃዎችን ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
22
👍 15
😁 6
🥰 1
4 5 8.7K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
20.03.2026 04:00
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ አልፈጥር በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ኢድ ሙባረክ!

ኢትዮጵያ ቼክ።

@EthiopiaCheck
👍 21
9
3 2 9.2K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
20.03.2026 02:41
#FactCheck አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአቡ ዳቢ ከተማ ህክምና ላይ እያሉ 'ያሳያሉ' በሚል እየተጋሩ ያሉ ምስሎች በሰው ሰራሽ አስተዉሎት (AI) የተፈበረኩ ናቸው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በገጠማቸዉ የጤና እክል ምክንያት በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች፣ አቡ ዳቢ ህክምና ላይ መሆናቸዉን የሚጠቁሙ መረጃዎች በስፋት እየተጋሩ ይገኛሉ።

ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ በሚገኝ በአንድ የህክምና ተቋም ዉስጥ ተኝተዉ ሲታከሙ ያሳያሉ የተባሉ ምስሎችም በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋሩ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ቼክ የክልሉ ፕሬዝዳንትን አሁናዊ የጤና ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ባያገኝም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ህክምና ላይ እንዳሉ ስማችን አይጠቀስ ካሉ የመንግስት ምንጮች ሰምተናል።

ይሁንና እንደ ‘SynthID Detector’ እና ‘Hive Moderation’ ያሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ምስሎችን መመርመሪያ መሳሪያዎችን በመጠቀም እንዲሁም ትልቅ ምልከታዎችን በማድረግ እየተጋሩ ያሉ ምስሎችን መርምረናል።

በዚህም መሰረት ፕሬዝዳንቱ አቡ ዳቢ በህክምና ተቋም ዉስጥ ተኝተዉ ህክምና እየተከታተሉ እንደሆነ ያሳያሉ በሚል እየተጋሩ ያሉ ምስሎች ትክክለኛ እንዳልሆኑ አረጋግጧል።

ለምሳሌ ያክል ‘Daily Facts’ እና ‘Daandii Dhugaa’ በተሰኙ የፌስቡክ ገጾች የተጋሩ ምስሎች በጉግል ኤ አይ (Google AI) የተፈበረኩ እንደሆነ ማረጋገጥ ችለናል።

‘ፕሮፍ ፀጊ ነኝ’ የሚል ስም ባለዉ የፌስቡክ ገጽ የተጋራ ምስልም በተመሳሳይ መልኩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ መሆኑን ሃይቭ ሞደሬሽን ድረ-ገጽን በመጠቀም ባደረግነዉ ማጣራት አረጋግጠናል።

ስለሆነም እነዚህ ምስሎች ትክክለኛ ካለመሆናቸው በተጨማሪ ይዘቶቻቸዉ ለተሳሳተ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ መሰል ምስሎችን ከማመናችን እንዲሁም መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
14
👍 10
😁 6
1 7 8.2K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
11.03.2026 04:31
#FactCheck ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሴት የመከላከያ ሚኒስትር እንደሆኑ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቀረበው መረጃ የተሳሳተ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- “ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ብቸኛ የመጀመሪያ ሴት መከላከያ ሚንስትር” የሚል መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል።

ይህ መረጃ ሰሞኑን የተከበረዉን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በማስመልከት የተጋራ ሲሆን መረጃዉን ካጋሩት መካከልም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ (verified) የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል።

በፌስቡክ ገጹ ሌሎች በሀገሪቱ በተለያዩ የስራ መስኮች ቀደምት የሆኑ ሴቶች ዝርዝርም የተጋራ ሲሆን መረጃዉን በርካታ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰዉ አጋርተዉታል።

ይሁን እንጂ “ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ብቸኛ የመጀመሪያ ሴት መከላከያ ሚንስትር” በሚል የተጋራዉ መረጃ በከፊል የተሳሳተ መሆኑን ተመልክተናል።

ኢ/ር አይሻ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት መከላከያ ሚንስትር ቢሆኑም በአፍሪካ ግን የመጀመሪያዋ እንዳልሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙሪያ ባደረገዉ ማጣራት የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ አስቀድመዉ ሴት መከላከያ ሚኒስትሮች ነበሯቸው።

ከነዚህ መካከል ፍሎሜና ማስካሬናስ እኤአ ከ2003-2004 ጊኒ ቢሳውን የመከላከያ ሚንስትር በመሆን አገልግለዋል።

ሴሲል ማኖራሃታ ደግሞ እኤአ ከ2007-2009 የማዳጋስካር መከላከያ ሚንስትር ነበሩ።

በተጨማሪም ኤልሳ ማሪያ ኔቶ ዲ’ኣልቫ ቴሼራ ዲ ባሮስ ፒንቶ እኤአ ከ2008-2010 የሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ መከላከያ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል።

ስለዚህ “ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ብቸኛ የመጀመሪያ ሴት መከላከያ ሚንስትር” በሚል የተጋራዉ መረጃ አሳሳች ሆኖ አግኝተነዋል።

ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም ኢንጂነር አይሻ መሀመድን ጨምሮ በርካታ ሴቶችን የሀገሪቱ 50% የሚሆን የሚንስትርነት ቦታዎች ላይ ስትመደብ አድናቆትን አግኝታ እንደነበር ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ቼክ
😁 41
10
🙏 7
👏 3
4 3 9.3K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
06.03.2026 17:54
#FactCheck ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከህወሓት አመራሮች ጋር ከሰሞኑ ያደረጉትን ውይይት ያሳያል በሚል እየተጋራ ያለው ቪዲዮ የቆየ ነው

ተጨማሪ ያንብቡ:
https://ethiopiacheck.org/%e1%8c%a0%e1%89%85%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ad-%e1%8a%a0%e1%89%a5%e1%8b%ad-%e1%8a%a0%e1%88%85%e1%88%98%e1%8b%b5-tplf/
ኢትዮጵያ ቼክ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከህወሓት አመራሮች ጋር ከሰሞኑ ያደረጉትን ውይይት ያሳያል በሚል እየተጋራ ያለው ቪዲዮ የቆየ ነው - ኢትዮጵያ ቼክ
/ኢትዮጵያ ቼክ/- በርካታ የፌስቡክ እና የኤክስ (የቀድሞ ትዊተር) አካውንቶች ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከሰሞኑ ከህወሓት አመራሮች ጋር ውይይት አደረጉ በሚል በስክሪን ቅጂዉ ላይ የሚታየዉን ቪዲዮ እያጋሩ ይገኛሉ። በዚህ ቪዲዮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)፣ የቀድሞ እና የአሁን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንቶች አቶ ጌታቸዉ ረዳ እና ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም ሌሎች የፌደራል መንግስት እና የህወሓት አመራሮች ሰላምታ ሲለዋወጡ እና ሲወያዩ ይታያሉ።
🙏 8
😁 6
👍 5
1
1 5 10.8K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
05.03.2026 03:00
#FactCheck እጃቸውን የሰጡ የኤርትራ ወታደሮችን ያሳያል ተብለው የተለቀቁት ምስሎች የተሳሳቱ ናቸው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በቅርብ ግዜያት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሀል እየተካረረ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ በርካታ መልእክቶች በፅሁፍ፣ በቪዲዮ፣ በምስል እንዲሁም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በታገዙ ምርቶች በደጋፊዎቻቸው አማካኝነት እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ከነዚህም መሀል 'ፍፁም ተስፋዬ' በሚል ስም የተከፈተ ከ33,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ 318 የኤርትራ ወታደሮች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን መስጠታቸውን በመጥቀስ መረጃ አጋርቷል። በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጀ 58 ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን  211 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል።

በተመሳሳይ መልኩ 'ዲጂታል ኢትዮጵያ' የተባለ ከ26,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅም ምስሉን እና መረጃውን አጋርቷል። በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጃ ደግሞ 67 ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 192 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል።

በተጨማሪም 'Betty Gullele' በሚል ስም የተከፈተ ከ55,000 በላይ ተከታዮች ያለው የፌስቡክ ገፅ መረጃውን አጋርቷል። በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጃ አራት ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 18 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ መከላከያ እጃቸውን የሰጡ የኤርትራ ሰራዊት አባላት እንደማያሳይ አረጋግጧል።

የጉግልን ምስልን በምልሰት መፈለጊያ (Google Lens) በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ የኤርትራ ጦር ከሶስት አመት በፊት ከትግራይ ክልል አካባቢዎች ሲወጣ የሚያሳይ መሆኑን አረጋግጠናል (ማስረጃ https://x.com/i/status/1616523677885169666

https://www.tghat.com/2023/01/21/%E1%88%9D%E1%8B%8D%E1%8D%83%E1%8A%A5-%E1%88%B0%E1%88%AB%E1%8B%8A%E1%89%B5-%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%89%B5%E1%88%AB-%E1%8A%AB%E1%89%A5-%E1%8C%88%E1%88%88-%E1%8A%A8%E1%89%A3%E1%89%A5%E1%89%B3%E1%89%B5/?noamp=mobile)

ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ በሆነ መልክ የሚጋሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ!
22
👍 18
2 3 11.4K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
03.03.2026 05:07
#FactCheck ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ሞት ሀዘናቸዉን እንደገለጹ ተደርጎ የተሰራጨው ስክሪን ቅጂ ሀሰተኛ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ሞት ሀዘናቸዉን እንደገለጹ የሚያሳይ ስክሪን ቅጂ (screenshot) በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል።

ይህ ስክሪን ቅጂ “በወንድሜ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ሞት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ። ኻሚኒ ላለፉት 40 አመታት ኢራንን በለዉጥ ጎዳና የመሩ ብርቱ ሰው ናቸዉ” የሚል መልዕክት ይዟል። በተጨማሪም “ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላ ኢራናዊያን መጽናናትን እመኛለሁ” ይላል።

በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታዮችም የስክሪን ቅጂዉን ትክክለኛነት እንድናጣራ ጥቆማቸዉን አድርሰዉናል።

ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን ስክሪን ቅጂ ትክክለኛነት ለማጣራት በመጀመርያ መልዕክቱ የጠ/ሚሩ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች ላይ እንዳለ ቅኝት አድርጎ እንደዚህ አይነት መልዕክት እንደሌለ ተመልክተናል።

በሁለተኛነት ይዘታቸው የተቀየሩ ፎቶዎችን ለመመርመር የሚረዳውን ‘Fotoforensics’ ድረ-ገጽን ተጠቅመናል።

ይህ ድረ-ገጽ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌስቡክ ስም የሚገኝበት የስክሪን ቅጂዉ ክፍል የተነካካ ወይም በኮፒ ፔስት (Copy and Paste) ይዘቱ የተቀየረ እንደሆነ አሳይቷል።

በሌላ በኩል በስክሪን ቅጂዉ ላይ የሚገኘው ይዘቱ የተለጠፈበትን ጊዜ የሚያሳይ መግለጫ (Time Stamp) የፊደላት ቅርጽ (Font) ስህተት እንዲሁም ከበስተቀኙ የሚገኘው የግላዊነት ቅንብር የአለም ምስል (Public Privacy Setting Globe Icon) ደግሞ የአቀማመጥ ግድፈት (Misalignment) ያለበት መሆኑንም ተመልክተናል።

በተጨማሪም የስክሪን ቅጂዉ ዋና ይዘት ጽሁፍም በተመሳሳይ መልኩ የተለያዩ ግድፈቶች ያሉበት ሲሆን ይህም በቅንብር የተሰራ እንደሆነ የሚጠቁም ነው።

በመጨረሻም፣ መረጃው በተለጠፈ በ14 ደቂቃ ውስጥ 44,500 ግዜ ሪአክሽን እንዳገኘ ማሳየቱ በጠ/ሚሩ የፌስቡክ ገፅ ላይ ያለውን መስተጋብር እንደማያሳይ አይተናል።

በሌላ በኩል ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ኢራን በኩዌት ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ከኩዌት ልዑል አልጋ ወራሽ ጋር በስልክ መወያየታቸው እንዲሁም በአገሪቱ ላይ የሚፈጸም ጥቃትን በጽኑ ማውገዛቸውን የኩዌት የዜና ወኪል ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ቼክ
😁 22
9
👍 4
2 7 9.9K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
18.02.2026 05:10
#FactCheck የኤርትራን ዋና ከተማ አስመራን ያሳያል በሚል ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተሰራጨው ይህ ምስል የተሳሳተ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በቅርብ ግዜያት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሀል እየተካረረ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ በርካታ መልዕክቶች በፅሁፍ፣ በቪድዮ፣ በምስል እንዲሁም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በታገዙ ምርቶች በደጋፊዎቻቸው አማካኝነት እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ከእነዚህም መሀል 'ታዬ ቦጋለ አረጋ' በመባል የሚታወቁት ግለሰብ 'እነ እንቶኔ የሚናፍቋት ኤርትራ፤ የድሮዋ አራት ኪሎ እህት ከተማ' ከሚል ፅሁፍ ጋር አስመራ ከተማን እንደሚያሳይ ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ የገለፁበትን ፅሁፍ አስተያየት መስጫ ላይ ለጥፈው ተመልክተናል።

ይሁንና ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሉ ኤርትራ ውስጥ የተነሳ እንዳልሆነ አረጋግጧል።

ምስሉ በመጀመርያ የተጋራው ልክ የዛሬ አመት ገደማ 'African' በተባለ እና ከ480 ሺህ በላይ ተከታታዮች ባሉት የትዊተር (ኤክስ) አካውንት ነበር (ሊንክ: https://x.com/i/status/2018940069969555640)

በተመሳሳይ ናይጄሪያዊው አክቲቪስት 'Awoko Kwara' ምስሉ በናይጄርያዋ ዮሩባላንድ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ኢባዳን ከተማ ውስጥ ባለፈው አመት የተነሳ መሆኑን ጠቅሷል (ሊንክ: https://www.facebook*.com/share/p/1C7UxJUYwC/)

በተመሳሳይ በርካታ የናይጄርያ ታዋቂ ግለሰቦች እና ፖለቲከኞች ምስሉን በማጋራት እና ምስሉ ኢባዳን ውስጥ እንደሆነ በመግለፅ ከተማዋ ልማት እና ፅዳት እንደሚያስፈልጋት አስተያየት ሲሰጡ ተመልክተናል።

ከሌላ ቦታ ተወስደው ካለማረጋገጫ የሚለጠፉ ምስሎች ለሀሰተኛ መረጃ ስለሚያጋልጡን ጥንቃቄ እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
32
👍 12
😁 5
👏 3
4 3 12K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
17.02.2026 22:41
#FactCheck የጣልያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የስንዴ ነዶ ይዘው የሚታዩበት ምስል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በቅንብር የተሰራ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በቅርቡ ለጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ ኢትዮጵያን የጎበኙት የጣልያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የሆነውን እና በቅርቡ ይፋ የሆነውን የስንዴ ነዶ ይዘው የሚያሳይ ምስል እና ቪዲዮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል።

በምስሉ እና ቪዲዮው ጠቅላይ ሚንስትሯ የስንዴ ነዶዉን ይዘው ከጠቅላይ ሚንስትር ዓቢይ አህመድ ጎን ቆመው ይታያል።

ይህን ምስል/ቪዲዮ ካጋሩ የፌስቡክ ገጾች መካከል ‘Ethiopian Voice’ የሚል ስም እና ከ493 ሺህ በላይ ከታዮች ያሉት ገጽ አንዱ ነው። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገዉ ማጣራት ምስሉ በቅንብር የተሰራ መሆኑን አረጋግጧል።

ይህ ምስል ሁለቱ መሪዎች እጅ ለእጅ ተጨባብጠው የተነሱትን ፎቶ ይዘት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መተግበርያዎች መቀየር የተሰራ ሲሆን ትክክለኛው ምስልም በጠቅላይ ሚንስትር ዓቢይ አህመድ የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ ላይ ተጋርቶ ነበር፡ https://www.facebook*.com/share/p/1ReKaaYatu/?mibextid=wwXIfr

ኢትዮጵያ ቼክ ምስሉን ‘SynthID Detector’ የተሰኘዉን የጉግል መሳሪያዎችን በመጠቀም የተፈበረኩ እና የተቀናበሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች መመርመሪያ መሳሪያ በመጠቀም ባደረገዉ ማጣራት ምስሉ ጉግል ኤአይ (Google AI) በመጠቀም የተቀናበረ እንደሆነ ተመልክቷል።

‘Fake Image Detector’ የተሰኘው የተቀናበሩ ምስሎች መመርመሪያ ድረ-ገጽም ምስሉ የተፈበረከ ወይም ይዘቱ የተለወጠ እንደሆነ አረጋግጧል።

በተጨማሪም የምስሉን የተለያዩ ክፍሎች ላይ ባደረግነዉ ጥልቅ ምልከታ ምስሉ የተቀናበረ መሆኑን የሚያመላክቱ ስህተቶችን ተመልክተናል።

ብልጽግና ፓርቲ የቀጣዩ ምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱ የስንዴ ነዶ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

በሌላ በኩል የጣልያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጊያ ሜሎኒን የኢትዮጵያ ቆይታ በተመለከተ ጠ/ሚ ዓቢያ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “የጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ጉብኝት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በኢነርጂ፣ በመሠረተ ልማት፣ በግብርና እና በፈጠራ ዘርፎች የቀጠለውን ትብብራችን ለማጠናከር  ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው” ብለዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ
😁 28
18
👍 1
🙏 1
7 10.3K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
13.02.2026 05:55
#FactCheck ትናንት ምሽት መቀሌ ከተማ ውስጥ የተሰማውን የፍንዳታ ድምፅ ተከትሎ የተሰራጨው ምስል አሳሳች ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ትናንት ምሽት 3:30 ገደማ መቀሌ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ መሰማቱን ተከትሎ በርካታ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

አንዳንዶች ፍንዳታው የድሮን ጥቃት እንደሆነ ሲገልፁ ሌሎች ደግሞ የፈንጂ ድምፅ እንደነበር መላምት ሲያስቀምጡ ታይተዋል።

'Gamo ArbaMinch' የተባለ እና ከ144 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ በዚህ ዙርያ በሰበር ዜና መረጃ ያሰራጨ ሲሆን "በመቀሌ፣ ትግራይ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል፣ የፍንዳታው ምክንያት እስካሁን አልተረጋገጠም፣ የተጎዱ ሰዎች ወይም የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩም የተረጋገጠ መረጃ የለም" ብሏል።

በተመሳሳይ 'East African Insider' የተባለ እና መረጃዎቹን በእንግሊዝኛ የሚያቀርብ ከ53 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ይህንኑ ምስል በፅሁፍ አቀናብሮ በመልቀቅ በርካታ ግብረ-መልስ አግኝቷል።

ገፁ ከዚህ መረጃ ጋር አንድ ከፍተኛ ፍንዳታን የሚያሳይ ምስል የተጠቀመ ሲሆን ምስሉ ብዙዎች ዘንድ ስጋትን እና ጥርጣሬን ጭሯል።

ሚድያችን በዚህ ዙርያ ባደረገው ማጣራት የተባለው ፍንዳታ መከሰቱን ያረጋገጠ ሲሆን ምስሉ ግን ከሌላ ሀገር የተወሰደ መሆኑን ተመልክተናል። ምስሉ ከአመት በፊት እስራኤል ጋዛ ላይ ጥቃት ስታደርስ እንደሚያሳይ መረጃዎች ያሳያሉ።

በቢዝነስ ካምፓስ አጥር አቅራቢይ የተከሰተው ፍንዳታ ምክንያቱ ምን እንደሆነ የመቀሌ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን የሚገልፁ መረጃዎች ወጥተዋል። ፍንዳታው በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አለማድረሱን የከተማው ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ለመቐለ ኤፍ ኤም ተናግሯል።

ኢትዮጵያ ቼክ
👍 28
12
🙏 1
3 5 12.6K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
04.02.2026 00:12
#FactCheck ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አይ ኤም ኤፍ (IMF) ስለ ኢትዮጵያ የ2026 የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ አስቀምጧል ብለው ያቀረቡት አሀዝ የተሳሳተ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የአለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ኢትዮጵያ በያዝነው የአውሮፓውያኑ 2026 ዓ.ም ዘጠኝ ነጥብ ሶስት ፐርሰንት (9.3%) ታስመዘግባለች ብሎ ተንብዩዋል ብለው ለፓርላማ አባላት ገለፃ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮ የበጀት አመት የስድስት ወር አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ውሎ በያዝነው የፈረንጆች አመት ኢትዮጵያ 10 ፐርሰንት እድገት እንደሚኖራት መንግስታቸው እንደተነበየ አሳውቀዋል።

''አይ ኤም ኤፍ ምን አለ? የኛ ኦሪጅናል እቅድ 9.2 (ፐርሰንት) ነው፣ አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያ 2026 እድገት 9.3 ፐርሰንት ይሆናል ብሎ ተንብይዋል፣ ኦሪጅናል ካቀድነው በ0.1 ፐርሰንት የተሻለ ማለት ነው። አሁን ካሰብነው 10.2 (ፐርሰንት) አንድ ፐርሰንት በታች በኛና በአይኤምኤፍ መካከል የትንበያ ልዩነት አለ'' ብለው ጠ/ሚር አብይ ለፓርላማ አባሎች አስረድተዋል።

ይሁንና ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙሪያ ባደረገው ማጣራት መረጃው የተሳሳተ መሆኑን አረጋግጧል።

የአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቱ በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ እንዲሁም በድረ-ገፁ ላይ ባለፈው ጥቅምት ያጋራው መረጃ እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተያዘው 2026 የፈረንጆቹ አቆጣጠር 7.1 ፐርሰንት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል (ማስረጃ: https://www.facebook*.com/share/p/1BnQq4J4m7/)

በተጨማሪም ተቋሙ ከዘጠኝ ቀን በፊት ባወጣው አዲስ ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት 7.1 ፐርሰንት እንደሚሆን እንደሚጠብቅ በድጋሜ አረጋግጧል (ማስረጃ: https://www.imf.org/en/countries/eth)

ተቋሙ ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሰረት ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት የአማካኝ እድገት 4.6 ፐርሰንት እንደሚሆን በፌስቡክ ገፁ ላይ ባጋራው መረጃ ላይ አስቀምጧል (ሊንክ: https://www.facebook*.com/share/p/1Ap8J5xwPn/)

የመንግስት መረጃዎች ለህዝብ ሲቀርቡ ትክክለኛ ካልሆኑ በህብረተሰቡ ዘንድ ግርታን ሊፈጥር ስለሚችል ጥንቃቄ ይሻሉ።

የአይ ኤም ኤፍ ኦፊሴላዊ ትንበያ ምስል ተያይዞ ቀርቧል።

ኢትዮጵያ ቼክ
49
👍 31
😁 30
👏 4
🙏 4
14 22 14.9K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
31.01.2026 23:53
#FactCheck ይህ ምስል በቅርቡ ደቡባዊ ትግራይ ላይ ተጠምዶ የሚታይ መድፍን አያሳይም

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ከሰሞኑ በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ሀይሎች መሀል በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ ውጥረት እና ግጭት መንገሱን ተከትሎ በርካታ ያልተረጋገጡ እና የተሳሳቱ መረጃዎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሰሞኑን የትግራይ ሀይሎች ደቡባዊ ትግራይ ላይ ጠመዱት የተባለ የመድፍ ምስል ይገኝበታል።

መረጃውን ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መካከል ''Mahari T Hagos'' የሚል ስም ያለው እና ከ20 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ ይገኝበታል። ገፁ ''ደቡባዊ ትግራይ ጨርጨር ወረዳ የገበሬ ቤት ግቢ ውስጥ ተተክሎ ያለ መድፍ ነው'' ብሎ ጠቅሷል።

በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጃ 22 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 59 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል። 

በተመሳሳይ መልኩ ከ6,400 በላይ ተከታዮች ያሉት እና ''Hujira Press'' የሚል ስም ያለው የፌስቡክ ገፅም ምስሉን እና መረጃውን አጋርቷል። 

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሉ ሰሞኑን ደቡባዊ ትግራይ ዞን ጨርጨር ወረዳ ላይ የተጠመደ መድፍ እንደማያሳይ አረጋግጧል።

የጉግልን ምስልን በምልሰት መፈለጊያ (Google Reverse Image Search) በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሉ ከአራት አመት በላይ በፊት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ተጋርቶ እንደነበር ተመለክተናል።

በወቅቱ የመድፉን ምስል ያጋሩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች የትግራይ ሀይሎች መድፉን ማርከው ሲጠቀሙበት የነበረ እንደሆነ በመጥቀስ ምስሉን አጋርተው ነበር: https://www.facebook*.com/share/p/1C4eoJBJq3/

ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ በሆነ መልክ የሚጋሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
25
👍 4
🙏 2
2 4 13.7K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
31.01.2026 00:03
#FakeNewsAlert ወደ ትግራይ ክልል ተቋርጠው የሚገኙ የአየር በረራዎች በነገው እለት ይጀምራሉ በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ መደበኛ የአየር በረራዎች ከባለፈው እሮብ ማለትም ከጥር 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጠው እንደሚገኙ ይታወቃል።

"ከበላይ አካል በመጣ ትዕዛዝ ነው" በተባለለት በዚህ የበረራ ስረዛ በርካቶች ከጉዞ እንደተስተጓጎሉ መረጃውን ቀድሞ ይዞ የወጣው መሠረት ሚድያ የዘገበ ሲሆን አንዳንድ ነዋሪዎች እና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ሰራተኞች ከክልሉ ለመውጣት ጥድፊያ ላይ እንዳሉ ታውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች እና አካውንቶች የተቋረጠው በረራ ከነገ ቅዳሜ ጀምሮ እንደሚቀጥል መረጃ ለህዝብ እያጋሩ እንደሆነ ተመልክተናል።

ለምሳሌ 'Angesom Abreha' በሚል ስም የሚታወቅ እና ከ92 ሺህ በላይ ተከታታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ ከጋዜጠኛ እንደሰማው በመግለፅ ያጋራው ይህ የተሳሳተ መረጃ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብረ-መልሶችን እና አስተያየቶችን አስተናግዷል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የመንግስት ምንጮቹን ያነጋገረ ሲሆን በነገው እለት ወደ ትግራይ ክልል የሚደረግ በረራ እንደሌለ አረጋግጠዋል።

"ነገ ቅዳሜ በረራ እንደሌለ ማረጋገጥ እችላለሁ፣ እሁድ ወይም ከዛ በኋላ ስላሉት ቀናት አሁን ላይ በእርግጠኝነት መናገር ባልችልም በቅርብ ቀናት ይጀመራል የሚል ግምት የለኝም" በማለት ስሜ አይጠቀስ ያሉት ምንጫችን ተናግረዋል።

ሌላ አንድ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ ያጋሩ የመንግስት ሀላፊም በረራው በነገው ዕለት እንደሌለ አረጋግጠዋል።

ነገ እና ከነገ ወዲያ ለሚደረጉ በረራዎች እስከ ቅርብ ሰአታት ድረስ ትኬት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ-ገፅ ሲሸጥ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤ ኤፍ ፒ (AFP) ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች የተሰረዙት በክልሉ አዲስ በተቀሰቀሰ ግጭት እና የፀጥታ ስጋት መሆኑን መስማቱን በትናንትናው ዕለት ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ቼክ!
22
👍 3
🥰 1
6 11.4K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
28.01.2026 05:07
#EthiopiaCheck በዲጂታል ዘመን የሚካሄድ ምርጫ እና ፈተናዎቹ!

/ኢትዮጵያ ቼክ/- መንግስት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሰዎችን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ለመገደብ ሲሰሩ አልፎ አልፎ ይታያሉ፣ በተለይ ደግሞ በምርጫ ወቅት።

ከነዚህም ውስጥ:

1. የኢንተርኔት መዘጋት
በርከት ያሉ መንግስታት ኢንተርኔትን በመዝጋት እና ቴሌኮሚኒኬሽን በማቋረጥ የፍትሃዊ የምርጫ ስርዓቱን ሲያስተጓጉሉ ይታያሉ። ኔትወርክን ማቋረጥ ሰዎች ማግኘት ያለባቸውን መረጃ ሆን ተብሎ በማቋረጥ የሰዎችን የሰብዓዊ መብትን መጋፋት ነው። ኔትወርክን ማቋረጥ የዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት
አንቀጽ 19(3) ጋር በግልፅ ይቃረናል።

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ እንዳስቀመጠው ከሆነ በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የኔትወርክ  ማቋረጥ ተገቢ ሊሆን አይችልም ይላል። ለህብረተሰቡ ደህንነት በሚልም ሆነ ለብሄራዊ ደህንነት ሲባል የኔትወርክ መቋረጥን እንደተገቢ እርምጃ መውሰድ አይቻልም። የኔትወርክ መቋረጥ የተለያየ መልክ ሊይዝ ይችላል እነሱም  ኢንተርኔትን መዘጋት፣ የስልክ ኔትወርክን ማቋረጥ፣ የአጭር የስልክ መልዕክትን መዘጋት፣ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ መዘጋት ሊሆኑ ይችላል። በተለይ በምርጫ ወቅት የኔትወርክ መቋረጥ ከፍተኛ ጉዳትን ይዞ ይመጣል።

ስለምርጫው አጠቃላይ ስለሚወጡ መረጃዎች፣ ስለ እጩ ተወዳዳሪዎች አቋም፣ በምርጫው ቀን ደግሞ ስለምርጫ ጣቢያዎች እና የመሳሳሰሉትን መረጃዎች ሰዎች እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል። ይህም ደግሞ በተዘዋዋሪ የዜጎችን በነፃ እና በግልፅ የፓለቲካ ምህዳር ውስጥ ተሳትፎ ያግዳል። 

2. የሀሰተኛ መረጃን የመከላከል ስራ
በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስታት የሀሰተኛ መረጃን ስርጭት ለመቀነስ/ለመቆጣጠር ሲባል የተለያዩ ህጎችን እና መመሪያዎች ሲያፀድቁ አይተናል። የሀሰተኛ መረጃዎች መሰራጨት በመራጮች ላይ እንዲሁም በአጠቃላይ በዴሞክራሲ አውዱ ላይ ብዙ ተፅዕኖ እንደሚያመጣ ምንም ጥርጥር የለም።

ሆኖም ግን መንግስታት የዚህን የሀሰተኛ መረጃ መበራከትን ተገን በማድረግ በሰዎች ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በሚያግዱ መልኩ የተለያዩ ህጎች እና መመሪያዎች ሲወጡ ይስተዋላል። በአብዛኛው ጊዜ እነዚህ ህጎች ስለ ሀሰተኛ መረጃ ምንነት በደንብ ባልገለፀ መልኩ ይወጣሉ። ይህም ሲሆን ለአስፈፃሚ አካላት ህጉን እንደሚፈልጉት እንዲተረጉሙት ክፍተትን ይፈጥርላቸዋል።

3. አገልግሎትን መከልከል
በምርጫ ወቅት መንግስታት የማይፈልጉት/እነሱን የሚጎዳ ሀሳቦች እንዳይንሸራሸሩ ሲገድቡ ይስተዋላሉ። በዚህ በዲጂታል ዘመን ላይ ደግሞ የዚህን ሀሳብን የመገደብን አካሄድ ዘርፈ ብዙ አድርገውታል።

የተሰራጨ አገልግሎትን መከልከል (Distributed Denial of Service) ብዛት ያላቸው እና በኔትወርክ የተያያዙ ሌላን ሲስተም, በይነመረብ, ማህበራዊ ገፅን በተመሳሳይ ሰዓት በመጠቀም እና በማጨናነቅ ያንን ድህረገፅ ወይም ማህበራዊ ሚዲያ የሚፈልገው ሰው ማግኘት እንዳይችል ሜድረግ ነው::

በብዛት የሚታየው የተሰራጨ የአገልግሎት ክልከላ (Distributed Denial of Service) የተመራጡ ድረ ገጾች፣ ማሕበራዊ ሚዲያዎች ወይም ኮምፒተርን በብዛት በማጥለቅለቅ ወይም በማበላሸት በአዘውታሪዎቹ እንዳይገኝ ማድረግ ማለት ነው፡፡

4. በመራጮች መዝገብ እና በመራጮች መረጃ ላይ ጣልቃ መግባት
በምርጫሂደት ላይ ሌላው ችግር የሚፈጥረው ነገር በመራጮች መዝገብ እና በመራጮች መረጃ ላይ ጣልቃ መግባት ነው።በተለያዩ መንገዶች የመራጮች መረጃ አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያሉ የሰዎች መረጃዎችም አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ።

በምርጫ ወቅት በዚህ የቴክኖሎዎጂ ዘመን ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች አይነታቸው ዘርፈ ብዙ ነው። ማየት እንደቻልነው ከሆነ የኔትወርክ መቋረጥ የሰዎችን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ሲጋፋ የሀሰተኛ መረጃ መዛባት ደግሞ በምርጫ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ያመጣል በዚህም ምክንያት መንግስታት ይህን እንደ ምክንያትነት በመጠቀም የሰዎችን መረጃ የማግኘት መብትን ሲጋፉ እናያለን።

የመንግስት አካላት ኔትወርክን ከመዝጋት ይልቅ የተለያዩ የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ስለምርጫ እና ስለሀሰተኛ መረጃ መዛባት ዙሪያ ጥናቶችን ማካሄድ፤የነዚህ የመረጃ ማሰራጫ ድርጅቶች ደግሞ ሀላፊነትን ወስደው እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው።

ምንጭ- OHCHR

@EthiopiaCheck
13
👍 6
1 7 12.1K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
09.01.2026 03:31
#FactCheck ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ሴናተር ክሩዝ የኢትዮጵያን ካርታ ሲያነቡ የሚያሳየው ምስል በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረከ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ሴናተር ቴድ ክሩዝ የኢትዮጵያን ካርታ ሲያነቡ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል። በምስሉ ላይ ሴናተሩ ከኢትዮጵያ ካርታ ላይ የሶማሊ ክልልን በእጃቸው እየነኩ ለፕሬዝዳንቱ ሲያሳዩ ይታያል።

ይህን ምስል ያጋሩ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች ምስሉን ከሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና እንዲሁም ሰሞኑን በአሜሪካ እና ቬኔዙዌላ መካከል ከተፈጠረዉ ሁኔታ ጋር በማያያዝ አጋርተዋል።

በርካታ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎችም ምስሉን በተመለከተ የተለያዩ ሀሳብ እና አስተያየቶችን እየሰጡ መሆኑንም ተመልክተናል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገዉ ማጣራት ምስሉ ትክክለኛ እንዳልሆነ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ እንደሆነ አረጋግጧል።

የምስሉን ትክክኛነት ለማጣራት የጉግል ምርት የሆነዉን ሲንት አይዲ ዲቴክተር (SynthID Detector) የተጠቀምን ሲሆን ምስሉ በጉግል ኤአይ (Google AI) የተሰራ እንደሆነ ተመልክተናል።

በተጨማሪም ምስሉ የሀገራት እና የባህረ ሰላጤ ስም ጽሁፍ ግድፈቶች ያሉበት መሆኑ እንዲሁም በካርታዉ ቀኝ የታችኛዉ ክፍል የሚገኘው የካርታዉ ቁልፍ (map key/legend) ላይ ያለው ጽሁፍ ትርጉም አልባ እና በAI ምስሎች ላይ በስፋት የሚታይ ስህተት በመሆኑ ምስሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ ስለመሆኑ ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው።

ይህ ምስል በአንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ከመሰራጨቱ ውጪ በሌሎች አለም አቀፍ ሚድያዎች ወይም በመንግስታዊ  ተቋማት በየትኛውም ግዜ ቀርበው እንደማይገኙም ተመልክተናል፣ ይህም ምስሉ በቅንብር የተሰራ እና እውነታን የማያሳይ ሌላ ጠቋሚ ምልክት ሆኗል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ እንዲሁም ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
38
👍 13
🙏 6
😁 1
6 4 13K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
07.01.2026 06:16
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
22
🙏 10
2 2 12K
avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
23.12.2025 21:36
3
👍 1
14 4 15.1K

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram