avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
09.01.2026 03:31
#FactCheck ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ሴናተር ክሩዝ የኢትዮጵያን ካርታ ሲያነቡ የሚያሳየው ምስል በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረከ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ሴናተር ቴድ ክሩዝ የኢትዮጵያን ካርታ ሲያነቡ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል። በምስሉ ላይ ሴናተሩ ከኢትዮጵያ ካርታ ላይ የሶማሊ ክልልን በእጃቸው እየነኩ ለፕሬዝዳንቱ ሲያሳዩ ይታያል።

ይህን ምስል ያጋሩ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች ምስሉን ከሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና እንዲሁም ሰሞኑን በአሜሪካ እና ቬኔዙዌላ መካከል ከተፈጠረዉ ሁኔታ ጋር በማያያዝ አጋርተዋል።

በርካታ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎችም ምስሉን በተመለከተ የተለያዩ ሀሳብ እና አስተያየቶችን እየሰጡ መሆኑንም ተመልክተናል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገዉ ማጣራት ምስሉ ትክክለኛ እንዳልሆነ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ እንደሆነ አረጋግጧል።

የምስሉን ትክክኛነት ለማጣራት የጉግል ምርት የሆነዉን ሲንት አይዲ ዲቴክተር (SynthID Detector) የተጠቀምን ሲሆን ምስሉ በጉግል ኤአይ (Google AI) የተሰራ እንደሆነ ተመልክተናል።

በተጨማሪም ምስሉ የሀገራት እና የባህረ ሰላጤ ስም ጽሁፍ ግድፈቶች ያሉበት መሆኑ እንዲሁም በካርታዉ ቀኝ የታችኛዉ ክፍል የሚገኘው የካርታዉ ቁልፍ (map key/legend) ላይ ያለው ጽሁፍ ትርጉም አልባ እና በAI ምስሎች ላይ በስፋት የሚታይ ስህተት በመሆኑ ምስሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰራ ስለመሆኑ ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው።

ይህ ምስል በአንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ከመሰራጨቱ ውጪ በሌሎች አለም አቀፍ ሚድያዎች ወይም በመንግስታዊ  ተቋማት በየትኛውም ግዜ ቀርበው እንደማይገኙም ተመልክተናል፣ ይህም ምስሉ በቅንብር የተሰራ እና እውነታን የማያሳይ ሌላ ጠቋሚ ምልክት ሆኗል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ እንዲሁም ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
38
👍 13
🙏 6
😁 1
6 4 13K

Обсуждение 6

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram