avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
31.01.2026 23:53
#FactCheck ይህ ምስል በቅርቡ ደቡባዊ ትግራይ ላይ ተጠምዶ የሚታይ መድፍን አያሳይም

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ከሰሞኑ በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ሀይሎች መሀል በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ ውጥረት እና ግጭት መንገሱን ተከትሎ በርካታ ያልተረጋገጡ እና የተሳሳቱ መረጃዎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሰሞኑን የትግራይ ሀይሎች ደቡባዊ ትግራይ ላይ ጠመዱት የተባለ የመድፍ ምስል ይገኝበታል።

መረጃውን ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መካከል ''Mahari T Hagos'' የሚል ስም ያለው እና ከ20 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ ይገኝበታል። ገፁ ''ደቡባዊ ትግራይ ጨርጨር ወረዳ የገበሬ ቤት ግቢ ውስጥ ተተክሎ ያለ መድፍ ነው'' ብሎ ጠቅሷል።

በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጃ 22 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 59 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል። 

በተመሳሳይ መልኩ ከ6,400 በላይ ተከታዮች ያሉት እና ''Hujira Press'' የሚል ስም ያለው የፌስቡክ ገፅም ምስሉን እና መረጃውን አጋርቷል። 

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሉ ሰሞኑን ደቡባዊ ትግራይ ዞን ጨርጨር ወረዳ ላይ የተጠመደ መድፍ እንደማያሳይ አረጋግጧል።

የጉግልን ምስልን በምልሰት መፈለጊያ (Google Reverse Image Search) በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሉ ከአራት አመት በላይ በፊት በማህበራዊ ትስስር ገፆች ተጋርቶ እንደነበር ተመለክተናል።

በወቅቱ የመድፉን ምስል ያጋሩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች የትግራይ ሀይሎች መድፉን ማርከው ሲጠቀሙበት የነበረ እንደሆነ በመጥቀስ ምስሉን አጋርተው ነበር: https://www.facebook*.com/share/p/1C4eoJBJq3/

ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ በሆነ መልክ የሚጋሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ
25
👍 4
🙏 2
2 4 13.7K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram