avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
05.03.2026 03:00
#FactCheck እጃቸውን የሰጡ የኤርትራ ወታደሮችን ያሳያል ተብለው የተለቀቁት ምስሎች የተሳሳቱ ናቸው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በቅርብ ግዜያት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሀል እየተካረረ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ በርካታ መልእክቶች በፅሁፍ፣ በቪዲዮ፣ በምስል እንዲሁም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በታገዙ ምርቶች በደጋፊዎቻቸው አማካኝነት እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ከነዚህም መሀል 'ፍፁም ተስፋዬ' በሚል ስም የተከፈተ ከ33,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ 318 የኤርትራ ወታደሮች ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን መስጠታቸውን በመጥቀስ መረጃ አጋርቷል። በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጀ 58 ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን  211 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል።

በተመሳሳይ መልኩ 'ዲጂታል ኢትዮጵያ' የተባለ ከ26,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅም ምስሉን እና መረጃውን አጋርቷል። በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጃ ደግሞ 67 ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 192 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል።

በተጨማሪም 'Betty Gullele' በሚል ስም የተከፈተ ከ55,000 በላይ ተከታዮች ያለው የፌስቡክ ገፅ መረጃውን አጋርቷል። በዚህ ገፅ የተጋራውን መረጃ አራት ተጠቃሚዎች መልሰው ያጋሩት ሲሆን 18 የሚሆኑት አስተያየቶች ሰጥተውበታል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ መከላከያ እጃቸውን የሰጡ የኤርትራ ሰራዊት አባላት እንደማያሳይ አረጋግጧል።

የጉግልን ምስልን በምልሰት መፈለጊያ (Google Lens) በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ የኤርትራ ጦር ከሶስት አመት በፊት ከትግራይ ክልል አካባቢዎች ሲወጣ የሚያሳይ መሆኑን አረጋግጠናል (ማስረጃ https://x.com/i/status/1616523677885169666

https://www.tghat.com/2023/01/21/%E1%88%9D%E1%8B%8D%E1%8D%83%E1%8A%A5-%E1%88%B0%E1%88%AB%E1%8B%8A%E1%89%B5-%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%89%B5%E1%88%AB-%E1%8A%AB%E1%89%A5-%E1%8C%88%E1%88%88-%E1%8A%A8%E1%89%A3%E1%89%A5%E1%89%B3%E1%89%B5/?noamp=mobile)

ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ በሆነ መልክ የሚጋሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ!
22
👍 18
2 3 11.4K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram