avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
04.10.2024 22:21
የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. ግዙፉ የቴክኖሎጅ ኩባንያ ሜታ በቀላሉ ቪዲዮና ድምጽ መስራት የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት መገለገያን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል። ይህ ሙቪ ጄን (Movie Gen) የሚል ስያሜ የተሰጠው መገልገያ በጽሁፍ የቀረበን ሀሳብ በፍጥነት ወደ ተንቀሳቃሽ ምስል መቀየር የሚችል ሲሆን ማጀቢያ ሙዚቃና ድምጽም ማምረት ይችላል ተብሏል። መገልገያው ለሲኒማ ኢንዱስትሪ በእጅጉ እንደሚጠቅም የተነገረ ቢሆንም ለሀሠተኛ መረጃ ስርጭት የመዋል ዕድሉ ሰፊ መሆኑን የተመለከቱ አስተያየቶችም በመሰጠት ላይ ናቸው።

2. በመጭው ታህሳስ በጋና የሚደረገው ምርጫ በሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ተጽኖ ስር እናዳይወድቅ ጋዜጠኞች ከፍተኛ ሀላፊነት አለባችሁ ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት አሳስበዋል። በ28ኛው የጋና ጋዜጠኞች ዓመታዊ የሽልማት መርሐግብር ላይ የተገኙት ፕሬዝደንት አኩፎ-አዶ ሀሠተኛና የተዛባ መረጃ በዴሞክራሲ ምርጫ ስርዐት ላይ የደቀነውን ስጋት አስታውሰው ጋዜጠኞች “የዕውነት ዘብ” እንዲሆኑ መክረዋል።

3. ሜታ በማህበራዊ ፕላትፎርሞቹ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመቀነስ ከባንኮች ጋር በሙከራ ደረጃ የጀመረው መረጃ የመለዋወጥ አሰራር ውጤት እንዳመጣለት በሳምንቱ አጋማሽ ባስነበበው መግለጫ አስታውቋል። ካምፓኒው የሙከራ አሰራሩን ከስድስት ወራት በፊት በዩኬ ከሚገኙ ባንኮች ጋር መጀመሩን ገልጾ በዚህም በማጭበርበር ድርጊት ላይ ተሰማርተው ነበር ያላቸውን ከ20,000 በላይ አካውንቶችን ማስወገድ መቻሉን አብራርቷል። በሜታ ስር የሚተዳደሩት ፌስቡክና ዋትስአፕ የማጭበርበር ድርጊት በስፋት ከሚፈጸምባቸው የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ከቀዳሚዎቹ እንደሚመደቡ ጥናቶች ያሳያሉ።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥

-በሰው ሰራሽ አስተዉሎት የተፈበረኩ ምስሎች የፈጠሩትን ስጋት የሚዳስስ ጽሁፍ አቅርበናል:
@ethiopiacheck2462

-የግብጽ ሚዲያዎች በታላቁ የሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ በማለት ያሰራጩትን መረጃ ፈትሸናል:
@ethiopiacheck2463

-በአርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ ህልፈት ዙርያ የተሰራጨን ሀሠተኛ መረጃ አጣርተናል:
@ethiopiacheck2464

-ተመሳስለው የሚከፈቱ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ለመለየት የሚረዱ ነጥቦችን አቅርበናል:
@ethiopiacheck2465

-ታዋቂውን ሲኒማቶግራፈርና ዳይሬክተር ሰውመሆን ይስማውን (ሶሚክ) ስምና ፎቶ በመጠቀም የተከፈተ ሀሠተኛ የፌስቡክ አካውንት ያሰራጨውን የማጭበርበር ድርጊት አጋልጠናል:
@ethiopiacheck2466
-ከቪዲዮ ጌም ተወስዶ የተጋራን ቪድዮም ፈትሸናል:
@ethiopiacheck2467

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
Telegram
Ethiopia Check
#Monitoring ከአሳሳች የፕሮፋይል ምስሎች እስከ ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት: በሰው ሰራሽ አስተዉሎት (AI) የተፈበረኩ ምስሎች የፈጠሩት ስጋት በሰው ሰራሽ አስተዉሎት (AI) የሚፈበረኩ እና ከትክክለኛ የሰው ምስል ለመለየት አዳጋች የሆኑ ምስሎች ብዛት እና ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል። እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ ሰው መሰል ፊቶች ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር አካውንቶችን እና ገጾችን ለመክፈት፤ ሀሰተኛ መረጃን ለማሰራጨት፤ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመፈጸም፤ ግለሰቦች እና ተቛማት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን ለመፈጸም እንዲሁም የተቀናጁ የመረጃ ዘመቻዎችን ለማካሄድም ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ። ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/the-threat-of-ai-generated-images-%e1%88%b0%e1%8b%8d-%e1%88%b0%e1%88%ab%e1%88%bd-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%8b%89%e1%88%8e%e1%89%b5/
👍 16
2
👏 1
1 8.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram