avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
23.08.2024 19:45
የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. ቲክቶክ ከሳህራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገሮች ለሚሰራቸው ስራዎች የመጀመሪያውን የደህንነት አማካሪ ምክር ቤት (Safety Advisory Council) ማቋቋሙን ቬንቸር አፍሪካ አስነብቧል። ስምንት አባላት ካሉት አማካሪ ምክርቤት መካከል ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው። አማካሪ ምክርቤቱ ቲክቶክ ቀጠናውን በተመለከተ በሚያወጣቸው ፖሊሲዎች እንዲሁም ፕላትፎርሙን ጤናማ የማድረግ እንቅስቃሴዎች ላይ የማማከር ስራ እንደሚሰራ ተገጿል።

2. በመጭው ጥቅምት ወር በሞዛምቢክ በሚደረገው ምርጫ የሚሳተፉ ፖለቲከኞች ከጥላቻ ንግግር እንዲታቀቡ አንድ የሀገሪቱ ትልቅ ሊቀጳጳስ ጥሪ ማቅረባቸውን ቫቲካን ኒውስ ዘግቧል። ሊቀጳጳስ ክላውዲዎ ዳላ ዙዋና ባቀረቡት ጥሪ ፖለቲከኞች ከተንኳሽና ከጥላቻ ንግግር ይልቅ በፖሊሲ ጉዳዮች እና በፓርቲ ማኒፌስቶ ላይ እንዲያተኩር ተማጽኖ አቅርበዋል። ሊቀጳጳሱ የተማጽኖ ጥሪውን ያቀረቡ በነገው ዕለት በይፋ ከሚጀመረው የምርጫ ቅስቀሳ ዋዜማ ላይ ሁነው ነው።

3.በዩናይትድ ኪንግደም እያሻቀበ የመጣው የጥላቻ ንግግር እና ጥላቻ ወለድ ወንጅል በእጅጉ እንዳሳሰበብው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘር መድሎ አስወጋጅ ኮሚቴ ገልጿል። ኮሚቴው ባወጣው ረዘም ያለ መግለጫ የዩናይትድ ኪንግደም ፖለቲከኞችን ጨምሮ የቀኝ ዘመም አክራሪዎች እያፋፋሙት ካሉት የጥላቻ ንግግር አንጻር ሀገሪቱ ተጨባጭ እርምጃ እንድትወስድ አሳስቧል። ዩናይትድ ኪንግደም በተለይም አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ማህበረሰቦችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መባባሱን የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች:

- በማህበራዊ ሚዲያ በሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሰለባ ላለመሆን የሚረዱ ነጥቦችን አሰንብበናል:
@ethiopiacheck2422

-አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናገሩት ተብሎ የተሰራጨ መረጃን አጣርተን በአማርኛና በትግርኛ አቅርበናል:
@ethiopiacheck2419
@ethiopiacheck2418
-በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ስም እየተሰራጩ ያሉ ሀሰተኛ ደብዳቤዎችንም አጋልጠናል:
@ethiopiacheck2421

@EthiopiaCheck
Telegram
Ethiopia Check
#MondayMessage በማህበራዊ ሚዲያ በሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሰለባ ላለመሆን የሚረዱ ነጥቦች በማህበራዊ ሚዲያ ከምናያቸው አሉታዊ ክንውኖች መካከል የማጭበርበር ድርጊት ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚመደብ ነው። ብዙ ሰዎችም የዚህ አሉታዊ ድርጊት ሰለባ በመሆን ገንዘባቸውን አጥተዋል። ሙሉ መልዕክቱን ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/tips-to-stay-safe-from-social-media-scams-%e1%88%9a%e1%8b%b2%e1%8b%ab/
👍 13
2
👏 1
4 8.4K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram