#FactCheck አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናገሩት ተብሎ የተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ “የእነ ደብረፅዮን ቡድን ሻዕብያ ደጀን ይሆነናል ብለው ተማምነው እያደረጉት ያለ ጉባኤ ነው ነገር ግን ወዳልተፈለገ ችግር እንዳያስባን እሰጋለሁ” ብለው ተናግረዋል ብሎ ግዕዝ ሚድያ የተባለ ፌስቡክ ላይ ከ260,000 በላይ ተከታታይ ያለው ገፅ መረጃ አጋርቷል።
አቶ ጌታቸው በክልሉ ለሚገኙ መገናኛ ብዙኅን በሰጡት በዚህ ማብራሪያ ላይ በትግራይ ስላሉ ወቅታዊ ጉዳዮች አንስተዋል።
በተለይ እራሳቸውን ስላገለሉበት የህወሐት 14ኛ ጉባኤ በሚመለከት በሰጡት ቃል በዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው "ቡድን" በማለት የገለጹት የህወሐት አመራር ከ"ሻዕብያ ጋር እየሰራ ነው" ግን አላላሉም።
“ከጀርባችን ደጀን ይሆነናል፣ ይደግፈናል በሚሉት ባልታወቀ የውጭ ኃይል ተማምነው አራት የድርጅቱ አመራሮች እንዲካሄድ የወሰኑት ጉባኤ ወደ አልተፈለገ ችግር ሊመራን ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ህወሐት በምርጫ ቦርድ የተሰጠውን እውቅና አለመቀበሉን ተከትሎ ጉባኤው በቦርዱ ተቀባይነት ባያገኝም ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በመቐለ እየተካሄደ ይገኛል።
ድርጅቱ አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በጉባኤው ያልተሳተፉ አባላት ከማእከላይ ኮሚቴ አባልነታቸው ማንሳቱንም አሳውቆ ነበር።
ኢትዮጵያ ቼክ
@EthiopiaCheck
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram