avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
30.08.2024 21:25
የኢትዮጵያ ቼክ የአርብ ሳምንታዊ ዳሰሳ

1. በሀሠተኛ መረጃ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዌን ዎልቭስ ክራይ (When the Wolves Cry) የተሰኘ ፊልም በትናንትናው ዕለት በናይጄሪያ አቡጃ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ግቢ መመረቁን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ከናይጀሪያ፣ ቶጎ፣ ካሜሩን እና ቤኒን የተውጣጡ እውቅ ተዋኒያን የተሳተፉበት ይህ ፊልም ናይጄሪያንና ካሜሮንን ወደ ጦርነት ጫፍ አድርሶ የነበረን ሀሠተኛ መረጃ የታሪኩ ማዕከል ያደረገ ነው ተብሏል። በሀሠተኛ መረጃ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተሰራው ዌን ዎልቭስ ክራይ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም እውቅ በሆኑ የፊልም ፌስቲቫሎች እደሚታይም ተገልጿል።

2. ባሳለፍነው ዕሁድ በፈረንሳይ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው የቴሌግራም መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፓቬል ድሮቭ ከእስር በገንዘብ ዋስ መለቀቁን ቢቢሲ ዘግቧል። የፈረንሳይ ፖሊስ ቴሌግራምን በመጠቀም የተደራጁ ወንጀለኞች የሚያደርጉትን የገንዘብ ዝውውር ችላ በማለት፣ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ባለመተባበር እና በተደራጁ የወንጀለኛ ቡድኖች የሚሰራጩ የህጻናት ወሲብ ነክ ምስሎችን ባለመቆጣጠር ወንጀሎች ፓቬል ድሮቭ ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ በዘገባው ላይ ተገልጿል። በ5 ሚሊዮን ዩሮ ዋስትና ከዕስር ቤት የወጣው ፓቬል ድሮቭ ጉዳዩ እልባት እስከሚያገኝ ከፈረንሳይ መውጣት እንደማይችልም ተገልጿል።

3. ብራዚል ኤክስ/ትዊተር የተሰኘውን የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም ልትዘጋ እንደምትችል አለም አቀፍ ሚዲያዎች በመዘግብ ላይ ይገኛሉ። ብራዚል እርምጃውን የምትወስድው ኤክስ በሀገሪቱ መመደብ የነበረበትን የህግ ተወካይ (legal representative) ማቅረብ ባለመቻሉ መሆኑ ተገልጿል። የብራዚል ህግ ማነኛውም የማህበራዊ ሚዲያ ኣአገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ የህግ ተወካይ እንዲኖረው ይደነግ ጋል። ኤክ ባለፈው ወር የህግ ተወካዩን ከብራዚል ካሰወጣ በኅላ ከሀገሪቱ መንግስት ጋር የከረረ ጸብ ውስጥ መግባቱ ይታወቃል።

በሳምንቱ ያቀረብናቸው መረጃዎች የቴሌግራም ሊንኮች፥
-የጥላቻ ንግግርን የተመልከተ መልዕክት በአፋን ኦሮሞ አስነብበናል:
@ethiopiacheck2427

-በማህበራዊ ሚዲያ በሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሰለባ ላለመሆን የሚረዱ ነጥቦችን አጋርተናል:
@ethiopiacheck2428

-በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨን አንድ ሰነድ በተመለከተ የሚዲያ ዳሰሳ አቅርበናል: @ethiopiacheck2430

-የተጣራ መረጃን በቀላሉ ለማግኘት እና መረጃ ለማጣራት የሚጠቅሙ የጎግል መገልገያዎች የሚያስተዋውቅ ጽሁፍም አጋተናል: @ethiopiacheck2431

@EthiopiaCheck
3
👍 1
8.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram