avatar
Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
@aradaFmdigital
10.04.2026 13:39
የስቅለት በዓል እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 2፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመላው የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች እየተከበረ ነው።

በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት÷ በስግደት፣ በጾም፣ በጸሎት እና በዝማሬ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚነበቡ ሲሆን፥ በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበም የስግደት ስርዓት ይከናወናል።

የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ

Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1

Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical

Telegram:-@Arada_Fm 

Telegram:-@aradaFmdigital

Facebook*:-https://web.facebook*.com/aradafm

@Arada_Fm
105
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
avatar
Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
@aradaFmdigital
09.04.2026 17:12
ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሀዲያን እሴት "ሴሌ-ሜን" ለዓለም በማስተዋወቁ እውቅና ተሰጠው

ሚያዝያ 1፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሀዲያ ብሔር ዝነኛ የባህል እሴት የሆነውን "ሴሌሜ" በማቀንቀንና ለዓለም በማስተዋወቅ ላበረከተው አስተዋጽኦ የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል።

ይህ እውቅና የተሰጠው የሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ባዘጋጀው "ሴሌሜ ለሰላም" ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ ነው።

"ሴሌሜ" የተሰኘው ባህላዊ ጭፈራ በቅርቡ "ረጅሙ የጎዳና ላይ ትርዒት" በሚል በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ መመዝገቡ ይታወሳል።

ቴዎድሮስ ካሳሁን በቅርቡ አዲስ አልበሙን በዳግማዊ ትንሳኤ ለማድረስ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ተመስገን ኡካሬ

የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ

Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1

Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical

Telegram:-@Arada_Fm

Telegram:-@aradaFmdigital

Facebook*:-https://web.facebook*.com/aradafm

@Arada_Fm
👍 1
1 179
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
avatar
Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
@aradaFmdigital
09.04.2026 14:54
የፈጣን መንገድ የአገልግሎት ክፍያን በቴሌብር ማከናወን የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

ሚያዝያ 1፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) ኢትዮ ቴሌኮም ከኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር ዘመናዊ የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ተግባራዊ አድርጓል።

የክፍያ ሥርዓቱ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ቁልፍ ሚና ባለው የአዲስ አበባ - አዳማ የፈጣን መንገድ ላይ የሚሰጡ አገልግሎቶችን፤ የመንገድ አገልግሎት ክፍያዎችን፣ የቅጣት ክፍያዎችን እና ቶሎ (TOLO) የተሰኘና በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ የተመሠረተ የሂሳብ መሙያ ሚኒ አፕ ቶሎ (TOLO) የተሰኘና በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ የተመሠረተ የሂሳብ መሙያ ሚኒ አፕ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ በማቀናጀት የተጠቃሚዎችን ተሞክሮ ለማላቅ የሚያስችል ነው።

ይህም የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂን ከማሳካት ባለፈ ኢትዮ ቴሌኮም ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የመንግሥት አገልግሎቶችን በማዘመን ግልጽነት፣ የአሠራር ቅልጥፍና እና አካታችነት የሰፈነበት የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ተጨማሪ ለማንበብ https://web.facebook*.com/share/p/1Hnm4vp7ek/

የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ

Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1

Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical

Telegram:-@Arada_Fm

Telegram:-@aradaFmdigital

Facebook*:-https://web.facebook*.com/aradafm

@Arada_Fm
147
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ

Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

52.3K
YouTube channel -https://www.youtube.com/@aradafm95.1

Facebook* page -https://web.facebook*.com/aradafm

Website - aradafm.com
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram