ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሀዲያን እሴት "ሴሌ-ሜን" ለዓለም በማስተዋወቁ እውቅና ተሰጠው
ሚያዝያ 1፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሀዲያ ብሔር ዝነኛ የባህል እሴት የሆነውን "ሴሌሜ" በማቀንቀንና ለዓለም በማስተዋወቅ ላበረከተው አስተዋጽኦ የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል።
ይህ እውቅና የተሰጠው የሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ባዘጋጀው "ሴሌሜ ለሰላም" ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ ነው።
"ሴሌሜ" የተሰኘው ባህላዊ ጭፈራ በቅርቡ "ረጅሙ የጎዳና ላይ ትርዒት" በሚል በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ መመዝገቡ ይታወሳል።
ቴዎድሮስ ካሳሁን በቅርቡ አዲስ አልበሙን በዳግማዊ ትንሳኤ ለማድረስ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ተመስገን ኡካሬ
የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ
Youtube:
https://www.youtube.com/@aradafm95.1
Tiktok:
https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical
Telegram:-
@Arada_Fm
Telegram:-
@aradaFmdigital
Facebook*:-
https://web.facebook*.com/aradafm
@Arada_Fm
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram