avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
10.04.2026 20:41
ባሕር ዳር ከተማ ወደ ድል ተመለሰ።

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ አዳማ ከተማን አሸንፏል።

ባሕር ዳር ከተማ አዳማ ከተማን 2ለ1 ነው ያሸነፈው።

የባሕር ዳር ከተማን ግብ ከእረፍት በፊት በ17ኛው ደቂቃ ብሩክ ሰሙ እና ከእረፍት መልስ በ63ኛው ደቂቃ አንተነህ ተፈራ አስቆጥረዋል።

አዳማ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ከእረፍት በፊት በ26ኛው ደቂቃ ቢንያም አይተን አስቅጥሯል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
1 393
avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
10.04.2026 18:07
በዓለ ስቅለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከበረ ነው።

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ)በዓለ ስቅለት በአዲስ አበባ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከበረ ነው።

በበዓሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
5
👍 3
2 1.1K
avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
10.04.2026 14:13
" በዓልን በባዶ ቤት እንዳንውል ኾነናል" ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰለሞን መንደር የባሕል ሕክምና እና የምርምር ማዕከል በባሕር ዳር ከተማ ለ500 ወገኖች ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ ዶሮ፣ ዘይት እና ሽንኩርት ነው።
የሰለሞን መንደር የባሕል ሕክምና እና የምርምር ማዕከል ባለቤት ክንፈ ሩፋኤል ፈንታሁን ክርስቶስን መምሰል የሚቻለው የተቸገሩትን በመርዳት የተራቡትን በማብላት፤ ያዘኑትን በማጽናናት እና ሰዎችን ከልብ በመውደድ ነው ብለዋል። ተቋሙ በየ ዓመቱ የተቸገሩትን እየደገፈ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ለትንሣኤ በዓል የባሕር ዳር ከተማን ጨምሮ በክልሉ ተቋሙ በሚገኝበት ከተሞች ላይ ለ800 ወገኖች ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በበዓል ወቅት በባዶ ቤት ይውሉ እንደነበር አስታውሰዋል። የተደረገላቸው ድጋፍ "በዓሉን በደስታ ያለ ችግር ከሰው ጋር እኩል ኾነው እንዲያሳልፉ እንደሚያስችላቸውም" አንስተዋል።
ለተደረገላቸው ድጋፍም አመስግነዋል። በበዓል ወቅት ድጋፍ ለተቸገሩ ሰዎች ሀሴት የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
4
👍 1
1 1.5K
avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
10.04.2026 14:07
የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬን በኢትዮጵያ የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሰሉ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬን በኢትዮጵያ የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀቀው ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።
ፕሬዝዳንቱ ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬን ከሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝታቸው በኋላ በቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ሸኝተዋቸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
👍 1
1.2K

Amhara Media Corporation

48.7K
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Открыть в Telegram