avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
10.04.2026 14:13
" በዓልን በባዶ ቤት እንዳንውል ኾነናል" ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰለሞን መንደር የባሕል ሕክምና እና የምርምር ማዕከል በባሕር ዳር ከተማ ለ500 ወገኖች ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ ዶሮ፣ ዘይት እና ሽንኩርት ነው።
የሰለሞን መንደር የባሕል ሕክምና እና የምርምር ማዕከል ባለቤት ክንፈ ሩፋኤል ፈንታሁን ክርስቶስን መምሰል የሚቻለው የተቸገሩትን በመርዳት የተራቡትን በማብላት፤ ያዘኑትን በማጽናናት እና ሰዎችን ከልብ በመውደድ ነው ብለዋል። ተቋሙ በየ ዓመቱ የተቸገሩትን እየደገፈ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ለትንሣኤ በዓል የባሕር ዳር ከተማን ጨምሮ በክልሉ ተቋሙ በሚገኝበት ከተሞች ላይ ለ800 ወገኖች ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በበዓል ወቅት በባዶ ቤት ይውሉ እንደነበር አስታውሰዋል። የተደረገላቸው ድጋፍ "በዓሉን በደስታ ያለ ችግር ከሰው ጋር እኩል ኾነው እንዲያሳልፉ እንደሚያስችላቸውም" አንስተዋል።
ለተደረገላቸው ድጋፍም አመስግነዋል። በበዓል ወቅት ድጋፍ ለተቸገሩ ሰዎች ሀሴት የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
4
👍 1
1 1.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Amhara Media Corporation

48.7K
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Открыть в Telegram