avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
10.04.2026 20:44
ETV መዝናኛ በግሪክ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ሕግ ተግባራዊ ሊሆን ነው ********************** በቴክኖሎጂ ዕድገትና በማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ምክንያት የዓለም ወጣቶችና ሕፃናት ለአዕምሮ ጤና መታወክና ለተለያዩ ማኅበራዊ ጫናዎች መጋለጣቸው አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። ይህን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ሀገራት ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን እየወሰዱ ሲሆን፣ ግሪክ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል አዲስ አዋጅ ለማውጣት መዘጋጀቷን አስታውቃለች። የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሪያኮስ ሚትሶታኪስ እንደገለጹት፣ እገዳው ከ2027 የአውሮፓውያን ዓመት መባቻ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። መንግሥት እንዲህ ያለውን ውሳኔ ለመወሰን የተገደደው በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ምክንያት በሕፃናት ላይ እየጨመረ የመጣውን ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባትና የአዕምሮ ጤና ችግሮችን ለመከላከል በማሰብ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ልጆቻቸው በደንብ እንደማይተኙ፣ በቀላሉ እንደሚጨነቁና በስልካቸው ላይ ረጅም ሰዓት እንደሚያሳልፉ የገለጹልኝ ወላጆች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሕጻናት እና ታዳጊዎች በየጊዜው ከሌሎች ጋር በሚደረግ ንፅፅርና በኦንላይን በሚሰነዘሩ አሉታዊ አስተያየቶች ምክንያት ለከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እየተጋለጡ እንደሆነ ተናግረዋል። የግሪክ መንግሥት ውሳኔ በሀገሪቱ ሕዝብ ዘንድ ሰፊ ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተገልጿል። በሕዝብ አስተያየት ጥናት መሠረት ከግሪክ ወላጆች መካከል 80 በመቶ ያህሉ እገዳውን እንደሚደግፉት ገልጸዋል። አውስትራሊያ ባለፈው ዓመት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ማኅበራዊ ሚዲያን በመከልከል በዓለም ቀዳሚዋ አገር መሆኗ ይታወሳል። እንደ ብሪታንያ፣ ስሎቬንያ፣ ኦስትሪያ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይና ዴንማርክ ያሉ ሀገራትም ተመሳሳይ ሕጎችን ለማውጣት በዝግጅት ላይ ናቸው ተብሏል። በላሉ ኢታላ #Greece #under15 #socialmedia #screenaddiction #ban #EBC
2 1.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

ETV መዝናኛ

4.7K
ይህ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ትክክለኛው "የኢቲቪ መዝናኛ" የቴሌግራም ቻናል ነው!!
@etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
Открыть в Telegram