avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
29.05.2026 14:41
ሪያል ማድሪድ ጆዜ ሞሪንሆን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
****************
ፖርቹጋላዊው አወዛጋቢ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ሪያል ማድሪድን በድጋሚ ለማሰልጠን ተስማምተዋል።
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ሪያል ማድሪድን ለሚቀጥሉት ለሶስት አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን አኑረዋል።
ጆዜ ሞሪንሆን አ ከዚህ ቀደም ከ 2010 እስከ 2013 ሪያል ማድሪድን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ሲሆን በ2012 የላሊጋ ዋንጫን ከሪያል ማድሪድ ጋር ማሳካት ችለዋል።
@EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #ሞሪንሆ #ማድሪድ
1
😁 1
1 669
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
16.04.2026 20:06
የአንድ ዶሮ ዕድሜ ምን ያህል ነው?
*******************

በአሜሪካ የተገኘችው ዶሮ 15 ዓመት ከ100 ቀናት ዕድሜ ላይ መገኘቷ በዓለም ላይ በሕይወት ያለች በዕድሜ ትልቋ ዶሮ አስብሏታል።

እንዲህ ያሉትን ያልተለመዱ እና አስደናቂ ጉዳዮችን የሚመዘግበው የዓለም ድንቃድንቆች መዝገብም ይህችን ዶሮ በመዝገቡ ላይ አስፍሯታል።

‘ጌርቲ’ በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ይህች ዶሮ በአሜሪካ፣ ቴክሳስ የምትኖረው እና ‘ፐርል’ በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ዶሮ ከዚህ ቀደም ይዛው የቆየችውን ክብረ ወሰን በ6 ወራት ማሻሻሏ ተገልጿል።

ባለፉት 15 ዓመታት አራት የዶሮ ትውልዶች ሲያልፉ፣ በቡናማና ጥቁር ነጠብጣብ ላባዎች የደመቀችው ‘ጌርቲ’ ግን ረጅም እድሜ በሕይወት መቆየት የቻለች ብቸኛዋ ዶሮ ሆናለች።

‘ጌርቲ’ አሁን ላይ እንቁላል መጣል ማቆሟን እንዲሁም ዓይኖቿ መታወራቸው በሌሎች ዶሮዎች እንድትጠቃ እንዳደረጋት የዶሮዋ ባለንብረት ፍራንክ ቱሬክ ተናግሯል።

በሀና ምንዳሁን

#GuinnessWorldRecords #oldestchicken #USA #EBC
7
👍 4
🤣 3
2 7 1.5K
avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
16.04.2026 17:47
በአንድ ደቂቃ ውስጥ የአልዛይመር ቅድመ-ምልክቶችን የሚለየው ሰው ሠራሽ አስተውሎት
************************

በአሜሪካ ተመራማሪዎች ባካሄዱት ጥናት ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የአልዛይመር ሕመም ቅድመ-ምልክቶችን በአንድ ደቂቃ ውስጥ መለየት እንደሚቻል ተገልጿል።

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ፥ ቴክኖሎጂው ሰዎች በቃላት ምርጫቸው፣ በንግግር ፍሰታቸው እና በዓረፍተ ነገር አወቃቀራቸው ላይ የሚያሳዩዋቸውን ለውጦች መሠረት በማድረግ የመለየት አቅም አለው።

በተለምዷዊው መንገድ የሚካሄዱ የአልዛይመር ቅድመ-ምልክት ምርመራዎችን ይተካል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ይህ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ እጅግ ቀላል፣ ፈጣን እና ለአጠቃቀም ምቹ መሆኑም ተነግሮለታል።

እስካሁን በሕክምናው ዘርፍ ለአገልግሎት እየዋሉ ያሉ የአልዛይመር መመርመሪያ ዘዴዎች ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ከመሆናቸውም በላይ፣ አልፎ አልፎ በባለሙያዎች የግል ምልከታ ላይ የሚመሠረቱ መሆናቸውን ጥናቱ አመልክቷል።

አልዛይመር ቀስ በቀስ የሰውን ልጅ የማስታወስና የማሰብ ችሎታ በመቀነስ የዕለት ተዕለት የሕይወት ዘይቤን የሚያዛባና በተለይም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የሚስተዋል ሕመም ነው።

አዲሱ ቴክኖሎጂ በሽታው አስቀድሞ እንዲታወቅ እና አስፈላጊው ሕክምና በወቅቱ እንዲጀመር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር የሳይቴክ መረጃ ያመላክታል።

በዓለም ዙሪያ በዚህ ሕመም የሚጠቁ ሰዎች ቁጥራቸው ከፍተኛ እንደሆነ የሚገመት ሲሆን፣ በአሜሪካ ብቻ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሕሙማን እንዳሉ ጥናቱ ጠቁሟል።

በልዩ እሸቱ

#EBC #AlzheimersDetection #AI #HealthInnovation #MedicalTechnology
👍 2
1
1 1.1K
avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
10.04.2026 20:44
ETV መዝናኛ በግሪክ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ሕግ ተግባራዊ ሊሆን ነው ********************** በቴክኖሎጂ ዕድገትና በማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ምክንያት የዓለም ወጣቶችና ሕፃናት ለአዕምሮ ጤና መታወክና ለተለያዩ ማኅበራዊ ጫናዎች መጋለጣቸው አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። ይህን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ሀገራት ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን እየወሰዱ ሲሆን፣ ግሪክ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል አዲስ አዋጅ ለማውጣት መዘጋጀቷን አስታውቃለች። የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሪያኮስ ሚትሶታኪስ እንደገለጹት፣ እገዳው ከ2027 የአውሮፓውያን ዓመት መባቻ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል። መንግሥት እንዲህ ያለውን ውሳኔ ለመወሰን የተገደደው በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ምክንያት በሕፃናት ላይ እየጨመረ የመጣውን ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባትና የአዕምሮ ጤና ችግሮችን ለመከላከል በማሰብ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ልጆቻቸው በደንብ እንደማይተኙ፣ በቀላሉ እንደሚጨነቁና በስልካቸው ላይ ረጅም ሰዓት እንደሚያሳልፉ የገለጹልኝ ወላጆች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሕጻናት እና ታዳጊዎች በየጊዜው ከሌሎች ጋር በሚደረግ ንፅፅርና በኦንላይን በሚሰነዘሩ አሉታዊ አስተያየቶች ምክንያት ለከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እየተጋለጡ እንደሆነ ተናግረዋል። የግሪክ መንግሥት ውሳኔ በሀገሪቱ ሕዝብ ዘንድ ሰፊ ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተገልጿል። በሕዝብ አስተያየት ጥናት መሠረት ከግሪክ ወላጆች መካከል 80 በመቶ ያህሉ እገዳውን እንደሚደግፉት ገልጸዋል። አውስትራሊያ ባለፈው ዓመት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ማኅበራዊ ሚዲያን በመከልከል በዓለም ቀዳሚዋ አገር መሆኗ ይታወሳል። እንደ ብሪታንያ፣ ስሎቬንያ፣ ኦስትሪያ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይና ዴንማርክ ያሉ ሀገራትም ተመሳሳይ ሕጎችን ለማውጣት በዝግጅት ላይ ናቸው ተብሏል። በላሉ ኢታላ #Greece #under15 #socialmedia #screenaddiction #ban #EBC
2 1.6K
avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
10.04.2026 20:44
በግሪክ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ሕግ ተግባራዊ ሊሆን ነው
**********************

በቴክኖሎጂ ዕድገትና በማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ምክንያት የዓለም ወጣቶችና ሕፃናት ለአዕምሮ ጤና መታወክና ለተለያዩ ማኅበራዊ ጫናዎች መጋለጣቸው አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል።

ይህን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ሀገራት ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን እየወሰዱ ሲሆን፣ ግሪክ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል አዲስ አዋጅ ለማውጣት መዘጋጀቷን አስታውቃለች።

የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሪያኮስ ሚትሶታኪስ እንደገለጹት፣ እገዳው ከ2027 የአውሮፓውያን ዓመት መባቻ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

መንግሥት እንዲህ ያለውን ውሳኔ ለመወሰን የተገደደው በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ምክንያት በሕፃናት ላይ እየጨመረ የመጣውን ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባትና የአዕምሮ ጤና ችግሮችን ለመከላከል በማሰብ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

ልጆቻቸው በደንብ እንደማይተኙ፣ በቀላሉ እንደሚጨነቁና በስልካቸው ላይ ረጅም ሰዓት እንደሚያሳልፉ የገለጹልኝ ወላጆች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሕጻናት እና ታዳጊዎች በየጊዜው ከሌሎች ጋር በሚደረግ ንፅፅርና በኦንላይን በሚሰነዘሩ አሉታዊ አስተያየቶች ምክንያት ለከፍተኛ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እየተጋለጡ እንደሆነ ተናግረዋል።

የግሪክ መንግሥት ውሳኔ በሀገሪቱ ሕዝብ ዘንድ ሰፊ ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተገልጿል። በሕዝብ አስተያየት ጥናት መሠረት ከግሪክ ወላጆች መካከል 80 በመቶ ያህሉ እገዳውን እንደሚደግፉት ገልጸዋል።

አውስትራሊያ ባለፈው ዓመት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ማኅበራዊ ሚዲያን በመከልከል በዓለም ቀዳሚዋ አገር መሆኗ ይታወሳል።

እንደ ብሪታንያ፣ ስሎቬንያ፣ ኦስትሪያ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይና ዴንማርክ ያሉ ሀገራትም ተመሳሳይ ሕጎችን ለማውጣት በዝግጅት ላይ ናቸው ተብሏል።

በላሉ ኢታላ

#Greece #under15 #socialmedia #screenaddiction #ban #EBC
1
2 1.8K
avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
17.02.2026 20:57
3 3K
avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
14.02.2026 11:40
ቤት ለእንግዳ
የፓን አፍሪካኒስቱ ከተማ ይፍሩ ልጅ መኮንን ከተማ ይፍሩ በእሑድ ቤት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አመሰራረት አቶ ከተማ እንደ አባት እና ሌሎች ሃሳቦችን በእሑድ ቤት
#ebcdotstream #እሑድቤት #EBC #etventertainment #EbcEntertainment #Ethiopian
2
2.7K
avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
18.01.2026 12:20
3
1 3.2K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
avatar
ETV መዝናኛ
@etventertainment1
18.01.2026 11:41
እንኳን ለ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ!
#ebcdotstream #etv #ጥምቀት #Ethiopia #Epiphany
👏 1
2.7K

ETV መዝናኛ

4.7K
ይህ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ትክክለኛው "የኢቲቪ መዝናኛ" የቴሌግራም ቻናል ነው!!
@etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
Открыть в Telegram