avatar
EthioTube
@ethiotube
14.04.2026 17:44
ኢትዮጵያ በጅቡቲ በሚገኘው የታጁራ ወደብ ላይ የ60 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖራት የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች

​የጅቡቲ መንግስት፤ ኢትዮጵያ በታጁራ ወደብ ላይ 60 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖራት ቢፈቅድም ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተገልጿል።

​የጅቡቲ ወደቦችና ነፃ የንግድ ቀጠና ባለሥልጣን እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያ የባለቤትነት ድርሻውን ከመውሰድ ይልቅ "የኮሪደር ስምምነት" እንዲታከልበት በመጠየቋ ድርድሩ ሳይሳካ መቅረቱን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

የባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ኋላፊ አቡበከር ኦማር ሃዲ፤ ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን አፅንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

"ወደቦቻችንን ለመጠቀም የሚያስፈልጓቸውን መገልገያዎች ሁሉ እያቀረብን  ነው። ለኢትዮጵያ በራችን ክፍት ነው" በማለት የጅቡቲን አቋም ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በታጁራ ወደብ ላይ ከጅቡቲ የበለጠ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖራት ጥያቄ ቢቀርብላትም ሳትቀበለው መቅረቱን ኃላፊው መናገራቸውን ዘገባው አመላክቷል።

“እኛ ግልጽነት የተሞላበት አቋም አለን፤ ያቀረብነው ጥያቄ በታጁራ ወደብ ላይ የ60 በመቶ ድርሻ እንዲኖራቸው ነበር” ብለዋል።

ሃዲ አክለውም “የኢትዮጵያ መንግሥት ከባለቤትነት ድርሻው በተጨማሪ ኮሪደር ስምምነት (የየብስ መተላለፊያ) በመፈለጉ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል” በማለት ተናግረዋል።

#Ethiopia #PortofTadjourah #Djibouti #HornOfAfrica #Port #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 5 1.8K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram