avatar
EthioTube
@ethiotube
12.04.2026 23:27
በአዲስ አበባ የ59 ዓመት አዛውንት በበሬ ተወግተው መሞታቸውን ፖሊስ አስታወቀ

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጆኒ ጋራዥ አካባቢ የ59 ዓመት ግለሰብ በበሬ ተወግተው መሞታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

በዛሬው እለት የተከበረውን የፋሲካ በዓል አስመልክቶ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ፤ የአዛውንቱ ሕይወት ያለፈው ትላንት ሚያዚያ 3/2018 ዓ.ም. በዕለተ ዋዜማው መሆኑን ገልጿል። በዚህ አደጋ ሌላ ሰው ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱንም አመልክቷል።

በእለቱ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ በሬው ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ ሊያዝ እንደቻለ በመግለጫው አመላክቷል። ከዚህ አደጋ ውጭ የተለየ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ በበዓሉ ዋዜማ ሆነ በበዓሉ ዕለት አለማጋጠሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቋል፡፡

#Ethiopia #AddisAbaba #AddisAbabaPolice #Fasika #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
2 2 2.2K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram