avatar
EthioTube
@ethiotube
10.04.2026 01:10
ህወሓት የጄነራል ታደሠ ወረደ ሥልጣን ለተጨማሪ አንድ ዓመት መራዘሙን እንደማይቀበል አስታወቀ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለአንድ ዓመት የመሩት ሌ/ጄነራል ታደሠ ወረደ፤ የሥልጣን ጊዜያቸው ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም መደረጉ “የፕሪቶሪያውን ስምምነት የጣሰና እውቅና የሌለው ነው” ሲል ህወሓት ውሳኔውን ውድቅ አድርጎታል።

ጀነራል ታደሠ ከትላንት በስቲያ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ማቅረባቸው ይታወሳል። መጋቢት 30/2018 ዓ.ም. የሥልጣን ጊዜያቸው የሚጠናቀቀው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ለተጨማሪ አንድ ዓመት ክልሉን እንዲመሩ በፌደራል መንግሥቱ ተወስኗል።

ሆኖም ይህ ውሳኔ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት፤ በህወሓት እና በፌደራል መንግሥት መካከል መደረግ እንደነበረበት ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የጄነራሉ የሥልጣን ጊዜ የተራዘመው “በተናጠል ውሳኔ” መሆኑን በመጠቆም እንደማይቀበለው አሳውቋል።

#Ethiopia #Tigray #TPLF #TadesseWorede #AbiyAhmed #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 2 2.1K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram