avatar
EthioTube
@ethiotube
09.04.2026 01:28
በኢትዮጵያ አማራ ክልል በአንድ ቀን 3 የጤና ባለሙያዎች መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ መጋቢት 24/2018 ዓ.ም. ሦስት የጤና ባለሙያዎች በጥይት መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናገሩ። ዳይሬክተሩ በአማርኛ ቋንቋ ባሰራጩት ጽሑፋቸው፤ የተገደሉት የጤና ባለሙያዎች አቢዮት ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ የሚሠሩ ናቸው ብለዋል።

ግድያው የተፈጸመው በአማራ ክልል በኢትዮጵያ መንግስት እና በክልል ኃይሎች መካከል ግጭት እየተስፋፋ ባለበት ወቅት መሆኑንም አመላክተዋል። በዚህ ምክንያት ነርስን ጨምሮ ሁለቱ የጤና ባለሙያዎች ተገድለዋል ሲሉ ገልጸዋል። ሆኖም ግድያውን የፈጸሙትን አካላት በግልጽ አላሳወቁም።

የጤና ባለሙያዎች በማንኛውም ጊዜ ሊጠበቁ ይገባል ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ የሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት በሕክምና ባለሙያዎቹ ላይ የተፈፀመው ግድያ በገልተኛ አካል እንዲመረመር ጠይቋል።

#Ethiopia #Amhara #HealthWorkers #TedrosAdhanomGhebreyesus #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram