avatar
EthioTube
@ethiotube
08.04.2026 23:40
ኢትዮጵያ የአሳማ ስጋ ጨምሮ ሌሎች የስጋ ምርቶችን ከብራዚል ማስገባት ልትጀምር ነው

ኢትዮጵያ የአሳማ፣የበሬ እና የዶሮ ስጋን ጨምሮ 17 ምርቶችን ከብራዚል ማስገባት ልትጀምር ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ብራዚል የተጠቀሱትን ምርቶች ለማስገባት ከኢትዮጵያ መንግስት ፍቃድ ማግኘቷ ተገልጿል።

የሀገሪቱ የግብርና ሚኒስቴር፤ የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር 130 ሚሊዮን እንደሚገመት ጠቅሶ ይህ መሆኑ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላት መዳረሻ ያደርጋታል ማለቱ በዘገባው ተመላክቷል።

ብራዚል በ2025 የ3.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የስጋ ምርቶችን በመላክ 18 ቢሊዮን ዶላር በማግኘት የዓለማችን ቀዳሚ ሥጋ ላኪ ሀገር ሆናለች።

ወደ አፍሪካ ገበያ መስፋፋቷ ደግሞ 48 በመቶ የሚሆነውን የወጪ ንግዷን ከምትሸፍነው ቻይና ጋር ያላትን ጥገኝነት ጥገኝነት ይቀንስላታል ተብሏል።

#Ethiopia #Brazil #Meat #Beef #Pork #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram