avatar
EthioTube
@ethiotube
07.04.2026 17:46
የሥልጣን ጊዜያቸው በነገው ዕለት የሚጠናቀቀው ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቀረቡ

መጋቢት 30/2017 ዓ.ም. የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በመሆን የተሾሙት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ በነገው እለት የአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታቸው ይጠናቀቃል። ይህን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ማቅረባቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ከተለያዩ የካቢኔ አባሎቻቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ ይመጡ የነበሩት ጀነራል ታደሰ፤ ዛሬ ባቀረቡት ሪፖርት ከእሳቸው ውጭ ከትግራይ ክልል የመጣ ሌላ የሥራ ኃላፊ አልተገኘም። በዚህ ውይይት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤልም በዛሬው ውይይት ላይ እንደተሳተፉ ተመላክቷል። ጀነራል ታደሠ ጌታቸው ረዳን ተክተው ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ሥልጣን ሲመጡ ማሳካት ያለባቸው 8 ኃላፊነቶች ተሰጥቷቸው ነበር።

ከነዚህ ኃላፊነቶች ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው መመለስ፣የቀድሞ ታጣቂዎችን የሟቋቋም ተግባር እንዲጠናቀቅ ማድረግ እና ትጥቅ መፍታት፣ ከሀገር ሉዐላዊነትና ከፕሪቶሪያው ስምነት ያፈነገጡ ግንኙነቶችን እንዲቆሙ ማድረግ የሚሉ ይገኝባቸዋል።


#Ethiopia #Tigray
2 1 2.1K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram