avatar
EthioTube
@ethiotube
06.04.2026 18:16
“የመሬት ወረራ ሊደረግ ነው በሚል ሕዝባዊ ተቃውሞ ወደ ሥልጣን የመጣ መሪ፤ የእስራኤል የምትፈጽመውን የመሬት ወረራ አለመቃወም እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነው” ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያስተላለፉት የቅሬታ መልዕክት

ከሰሞኑ በጄኔቫ በተካሄደው 61ኛው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እስራኤል በፍልስጤም ግዛቶች ላይ እያደረገች ነው የተባለውን “ሕገ-ወጥ የሰፈራ ግንባታና ወረራን” ኢትዮጵያ በመደገፍ ድምፅ ሰጥታለች መባሉን ተከትሎ መነጋገሪያ ሆኗል።

የእስልምና መምሕር እና የታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰማቸውን ቅሬታ አስመልክተው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን የመጡት “በማስተር ፕላን ስም የመሬት ወረራ ሊደረግ ነው በሚል ተቃውሞ መነሻነት በፈነዳ ሕዝባዊ ተቃውሞ” መሆኑን በማኀበራዊ ገፃቸው በፃፉት መልዕክት አስታውሰዋል።

በዚህ መንገድ ወደ ሥልጣን የመጣ መሪ “በሌላ ሕዝብ መሬት ላይ የሚፈጸመውን የሰፈራ ወረራ በጄኔቫ መድረክ ተቃውሞን አለማሳየት እጅግ የሚቆረቁር የታሪክ ተቃርኖ ሆኖ አግኝቼዋለሁ” ሲሉ ኡስታዝ አሕመዲን ተችተዋል።

እስራኤል በፍልስጤም ላይ እያደረገች ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እና ወረራ ኢትዮጵያ አለመቃወሟ “ከሀገራችን ታሪካዊ ሥነ-ልቦና፣ ከዲፕሎማሲያዊ እሴቶቻችን እና ከገዛ ሕዝባችን ቀኝ አልገዛም በሚል ሲፋለም ካሳለፋቸው የመከራ ጋር ፍጹም የሚጋጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" በማለትም ወቅሰዋል።

#ኢትዮጵያ #Ethiopia #AhmedinJebel #Israel #Gaza #MiddleEast #Iran #AbiyAhmed #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 4 2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram