avatar
EthioTube
@ethiotube
03.04.2026 17:22
“የነዳጅ ዋጋ ላይ ድጎማ ባላደርግ የአንድ ሊትር ናፍጣ ዋጋ 234 ብር ከ17 ሳንቲም ነበር የሚሸጠው” መንግሥት

መንግሥት ከትናንት ወዲያ ያደረገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ድጎማ ባላደረግ ኑሮ የናፍጣ ዋጋ በሊትር 234ብር ከ 17 ሳንቲም እንዲሁም የቤንዚን ዋጋ 174 ብር 40 ብር ይደርስ ነበር ሲል ገለፀ።

በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ ከየካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተመላክቷል፡፡ ሁኔታው ከቀን ወደ ቀን ይሻሻላል ተብሎ ቢጠበቅም ነገሮች በመካረራቸው ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ እጥረት ከመፈጠሩም በላይ የአንዳንድ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ መጠን ሊጨምር እንደቻለ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

የዓለም አንድ አምስተኛ ድፍድፍ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በመዘጋቱ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የነበረ 120 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ እና 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅ የጫኑ ሶስት መርከቦች በአረብ ባሕረ ሰላጤ ላይ ቆመው እንደሚገኙ በመግለጫው ጠቁሟል። ሆኖም መንግሥት መደበኛ አቅርቦቱ እንዳይቋረጥ ከተባራሪ ገበያ ወይም spot market በከፍተኛ ዋጋ ነዳጅ በመግዛት ለማቅረብ ጥረት እያደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡

መንግስት አሁንም ቢሆን በአንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ ላይ 71 ብር እንዲሁም በቤንዚን ላይ 32 ብር ድጎማ እያደረገ ያለው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፤ ይህ ድጎማ ባይኖር ኖሮ የናፍጣ ዋጋ 234 ብር ከ 17 ሳንቲም እንዲሁም የቤንዚን ዋጋ 174ከ 40 ሳንቲም ይደርስ ነበር ብሏል። በዚህ ምክንያት በመንግስት ላይ ያለው የድጎማ ጫና ከ272 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

#Ethiopia #AddisAbaba
3 2 2.5K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram