avatar
EthioTube
@ethiotube
01.04.2026 22:44
መንግሥት ከፍተኛ የአቅርቦት እጥረት ባጋጠመው የነዳጅ ምርት ላይ በሊትር እስከ 24 ብር የሚደረስ የዋጋ ጭማሪ አደረገ

በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ከፍተኛ አጥረት ባጋጠመው የነዳጅ ምርት ላይ መንግሥት በድጋሚ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉ ታውቋል።ዛሬ ይፋ የሆነው የዋጋ ጭማሪ በተያዘው የመጋቢት ወር ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገ ነው። የተሻሻለው ዋጋ ከዛሬ መጋቢት 23/2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን ኢትዮቲዩብ ሰምቷል።

ከዚህ ቀደም መጋቢት 01/2018 ላይ በተደረገ ጭማሪ አንድ ሊትር ቤንዚን 132 ብር ከ 18 ሳንቲም ነበር። ዛሬ በተደረገው ጭማሪ 10 ብር ከ 23 ሳንቲም ጨምሮ 142 ብር ከ 41 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል። ከ ሦስት ሳምንት በፊት 146 ብር ከ 14 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው ኪሮሲን 6 ብር ከ 25 ሳንቲም ጨምሮ 152 ብር ከ 39 ሳንቲም ገብቷል።

139 ብር ከ 84 ሳንቲም የነበረው ነጭ ናፍጣ በሊትር 24 ብር ጨምሮ 163 ብር ከ 98 ሳንቲም ገብቷል። 133 ከ 45 ሳንቲም የነበረው ከባድ ጥቁር ናፍጣ 27 ብር ጨምሮ 160ብር ከ 68 ሳንቲም እንዲሸጥ የተወሰነ ሲሆን የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ 5 ብር ጨምሮ በሊትር 150 ብር ከ 48 ሳንቲም ሆኗል።

#Ethiopia #AddisAbaba #FuelPrice #EthiopianEconomy #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 3 2.4K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram