avatar
EthioTube
@ethiotube
01.04.2026 21:27
ሲኖትራክ የጭነት መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ በ2 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደረሰ

በአዲስ አበባ ልዩ ቦታው ቅድስት ሰዓሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ሲኖትራክ የጭነት መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

አደጋው የደረሰው ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም.ከቀኑ 5፡55 ሠዓት መሆኑ ተመላክቷል።

ንብረትነቱ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበር የሆነ የሠሌዳ ቁጥሩ 5-82D11-2 የሆነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከላምበረት ወደ ጃክሮስ አድርጎ በሚጓዝበት ወቅት ከአያት ወደ መገናኛ ሲጓዝ ከነበረ ባቡር ጋር በመጋጨት በባቡሩ ውስጥ ተሳፍረው በነበሩ ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

ፖሊስ የአደጋውን ምክንያት እያጣራ ሲሆን በሲኖትራክ ተሽከርካሪው ላይ የተጫነውን ከፍተኛ ክብደት ያለው ጭነት በማንቀሳቀስ መንገዱን ለትራፊክ ፍሰቱ ክፍት ለማድረግ ጥረት እያደረገ ነው ተብሏል፡፡

አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት የመኪናቸውን ፍጥነት በአግባቡ ሊቆጣጠሩ በሚችሉበት ሁኔታና የመንገዱን አቀማመጥ ከግምት ባስገባ መልኩ ሊሆን እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

#Ethiopia #AddisAbaba #CarAccident #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
3 1.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram