avatar
EthioTube
@ethiotube
30.03.2026 17:33
ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ዘፈን አቆመ

በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል:
-----

#ከዚበኋላዘፈኑዓለምየለሁም

እናንተ ስለኔ በፀሎታችሁ የደከማችሁ መጋቢዎች ዘማሪዎች
ፀሎታችሁ በከንቱ አልቀረም የጠፋው ልጅ ተገኝቷል! ዓለም ቆሻሻ ናት የዘፈኑ አለም እጅግ በውስብስብ አጋንታዊ አሰራር የተያዘ ነው ምንቀን ነው የገባሁበት እያልኩ ሳለቅስ አምላኬን ስማጠን አንዴ ከ2005 - 2007 ሁለት ዓመት ገደማ ሳቆም መጋቢ ቸሬ ጋር ቃል ስካፈል ጥቤ ቀድሞ አመለጠ እኔ አንዴ ወደዘፈኑ አለም ስመለስ በሀጥያት ስረክስ ደሞ ፊቱን ስፈልግ ሳመነታ ጌታ ሲገስጠኝ አስቸግሬው ቆየሁ ሰይጣን ዘመኔን ሊበላው ሲያባብለኝ ጌታ የልጅነቴ አምላክ ደረሰልኝ ዓለም ውሸት ነው ዝናም ከንቱ ቆሻሻ ነው የውሸት መልክ የውሸት ፈገግታ ብቻ!

“ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፦ የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።”
— 2ኛ ጴጥሮስ 2፥22
ይህ ቃል ለኔ ነው ስንቴ ስወጣ ስንቴ ስገባ ዛሬ ቀኑ ቆረጠ አመለጥኩኝ ታደገኝ አዳነኝ ሸክሜ ወደቀ #እሰይ አልኩት ጌታዬን በጨለማ የነበርኩትን ወንድማችሁን ደጉ አባቴ አባታችሁ እሮጦ ተቀበለኝ ጌታን ባርኩልኝ ስሙን ከፍ አድርጉልኝ።

“ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።”
ዕብራውያን 10፥38

ከዚ በኋላ ዘፈኑ ዓለም የለሁም ዳግም ዞር ብዬ አላየውም ስሙ ይባረክ! ኢየሱስ ጌታ ነው! በዘፈኑ ያላችሁ ወዳጆቼ አሁን ሽንገላ የለኝም ዘፋኝነት ከስካር ጋ ተነጣጥለው አያውቁም እኔን የታደገኝ አምላክ አምናለሁ እናንተንም ይታደጋችሁ!

አቤል ሙሉጌታ

#Ethiopia #EthiopianMusic #AbelMulugeta #EthiopianNews #EthioTube #Africa
3 3 2.1K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram