avatar
EthioTube
@ethiotube
29.03.2026 16:43
በነዳጅ እጥረት ሳቢያ የተወሰኑ የመንግሥት ሠራተኞች የዓመት ፈቃድ እንዲሰጣቸው ተወሰነ

በሀገሪቱ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ ሳቢያ ሁሉም የመንግሥት ተቋማትና የልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ሠራተኞች የዓመት ፈቃድ እንዲሰጣቸው ተወስኗል ሲል ዘሪፖርተር በዛሬው እትሙ አስነብቧል። መንግሥት አስተላልፎታል የተባለው ይህ ውሳኔ በነዳጅ እጥረት ምክንያት የተፈጠረውን የትራንስፖርት መጨናነቅ ለማቃለል የታሰበ መሆኑም ተመላክቷል።

የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ በኢራን ከተዘጋ በኋላ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ነዳጅ ከውጭ ገዝተው የሚያስገቡ ሀገራት ተጎጂ ሆነዋል። ይህን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ረዣዥም የተሽከርካሪ ሰልፎች ተስተውለዋል። በተለያዩ የክልል ከተማዎች ደግሞ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት ከ 3 ቀናት በላይ ተሰልፈው እንደቆዩ ተዘግቧል።

በዚህ ሳምንት በተላለፈው ውሳኔ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ለተወሰኑ ሠራተኞቻቸው የዓመት ፈቃድ እንዲሰጡ ተነግሯቸውዋል ሲል ዘገባው አመላክቷል። ይህን ተከትሎ ተቋማቱ ፈቃዱን ለመሥጠት የሠራተኛ ልየታ የማድረግ ሒደት ውስጥ ናቸው ተብሏል። አንዳንዶቹ ተቋማት ደግሞ ለተወሰኑ ሰራተኞቻቸው አስገዳጅ ፈቃድ መስጠት ጀምረዋል። ከእነዚህም መካከል የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (Ethio Engineering Group) አንዱ ሲል ዘገባው አስታውቋል።

ተቋሙ በውስጥ ማስታወቂያ ለሠራተኞቹ ባስተላለፈው መልዕክት የተከሰተው የነዳጅ እጥረት በሕዝብ አውቶቡስ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረ ይገልፃል።

#Ethiopia #AddisAbaba #PublicServants #Fuel #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
5 2.3K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram