avatar
EthioTube
@ethiotube
28.03.2026 17:23
አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ ሠራዊት ፍቅሬ፣ ይገረም ደጀኔን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ

“በሕገወጥ መንገድ ከተገኘዉ ገንዘብ እያንዳንዳቸዉ አሁን ባለዉ የገበያ ዋጋ ስምንት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መኪና ተቀብለዋል” ፌደራል ፖሊስ

በዜጎች ላይ የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት አድርሷል የተባለውን ፊንቴክ ኢንቨስትመንት የተሰኘ ድርጅትን ባልተገባና በተጋነነ መልኩ በማስተዋወቅ በሕገወጥ መንገድ ከተሰበሰበው ገንዘብ ተጋሪ በመሆን የተጠረጠሩ አርቲስቶችና የማስታወቂያ ባለሙያዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ።

የፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ፍርድቤት በማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸው ግለሰቦች አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ አብርሃም ግዛው፣ ይገረም ደጀኔ፣ መንሱር ጀማል እና ካሊድ ናስር የተባሉ ታዋቂ አርቲስቶችና የማስታወቂያ ባለሙያዎች ናቸው።

እነዚህ ታዋቂ ግለሰቦች በኀብረተሰቡ ዘንድ ያላቸዉን ዕውቅናና ተቀባይነት በመጠቀም ሆነ ብለው የተጋነነ ማስታወቂያ በመንገር እና በተለያዩ ማኀበራዊ ሚዲያ የሐሰት መረጃዎችን ለኀብረተሰቡ በማሰራጨት ዜጎችን እንዲጭበረበሩ አድርገዋል መባሉን ሰምተናል።

በተጨማሪ በሕገወጥ መንገድ ከተገኘዉ ገንዘብ እያንዳንዳቸዉ አሁን ባለዉ የገበያ ዋጋ ስምንት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቢ.ዋይ.ዲ ሶንግ ፕላስ የመኪና ስጦታ ተቀብለዋልም ተብሏል።

ፊንቴክ ኢንቨስትመንት የግል ድርጅት መሥራችና ባለቤቶች የሆኑት ዳንኤል ዮሃንስ ኢየሱስ እና ግርማይ ገ/ሚካኤል ይህደጎ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በመጠቀም ከ1200 በላይ ዜጎችን በማጭበርበር የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል ተብሏል።

#Ethiopia #AddisAbaba #EthiopianCelebrities #EthiopianNews #EthioTube #Africa
2 1 1.4K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram