avatar
EthioTube
@ethiotube
27.03.2026 17:56
ነዳጅ ለመቅዳት ከ 3 ቀናት በላይ የተሰለፉት አሽከርካሪዎች

“አንድ ሊትር ነዳጅ እስከ 500 ብር እየተሸጠ ነው”

በሀገሪቱ የነዳጅ እጥረት መፈጠሩን ተከትሎ ከፍተኛ ተግዳሮት እንዳጋጠማቸው አሽከርካሪዎች ገልጸዋል። ሪፖርተር በጉዳዩ ላይ በሠራው ዘገባ በኦሮሚያ፣ደቡብ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ክልል የሚገኙ አሽከርካሪዎችን አነጋግሯል።

በክልሎቹ “ነዳጅ የለም” በሚል ምክንያት ከመደበኛ ዋጋው አምስት እጥፍ ከፍ ባለ ዋጋ ነዳጅ እየገዙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በሻሸመኔ እና ሐዋሳ ከተማ በርካታ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት ከ 3 ቀናት በላይ ተሰልፈው መቆየታቸውን ተናግረዋል።

በሻሸመኔ ከተማ ያሉ ማደያዎች አገልግሎት የሚሰጡት ከ ለሊት 6 ሰዓት በኋላ በትላልቅ ጄሪካን በማስቀዳት ወይም በጥቁር ገበያ ነው ተብሏል። በዚህ ግብይት አንድ ሊትር ነዳጅ ከ 350 ብር እስከ 500 ብር እንደሚሸጥ ዘገባው አመላክቷል። በዚህ ምክንያት 20 ብር የነበረ የመጓጓዣ ዋጋ 30 ብር ጨምሮ 50 ብር መግባቱንም አሽከርካሪዎቹ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ማደያዎች የነዳጅ ዋጋ ጨምረው በጄሪካን ይሸጠሉ ቢባሉም ይህን ክስ አስተባብለዋል። ማደያዎቹ በፊት በአራት እና አምስት ቀናት ውስጥ ነዳጅ ይቀርብላቸው እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ግን ነዳጅ ከተረከቡ ከ 15 ቀናት በላይ እንደሆናቸው ጠቁማዋል። በነዳጅ እጥረቱ ምክንያት ከጅቡቲ የአፈር ማዳበሪያ ጭነው ወደ ቦረና ዞን ሲጓዙ የነበሩ አንድ አሽከርካሪ ደግሞ ከጉዟቸው መስተጓጎላቸውን አመልክተዋል።

እኒህ አሽከርካሪ ከዚህ ቀደም ከጅቡቲ አዲስ አበባ ለመጓዝ 3 ቀናት እንደሚፈጅባቸው ተናግረው አሁን ላይ ነዳጅ ባለመኖሩ ከ 10 ቀን በላይ በመንገድ እንደሚቆዩ አስረድተዋል።

#Ethiopia #Fuel #FuelShortage #EthiopianNews #EthioTube #Africa
1 1 1.8K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram